Connect with us
Express news


EURO 2020

Group A Preview

Group A, www.euro
UEFA.com

በዘንድሮ ዩሮ ውስጥ ምድብ A የሚያካትተው ቱርክ፣ ዌልስ ፣ ጣልያን እና ስዊዘርላንድን ነው።

ጣልያኖች በሮቤርቶ ማንቺኒ የሚመሩ ሲሆን በ2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ካገጠማቸው አሳፋሪ ሽንፈት በኋላ ነበር ብዙም ሳይቆይ ለአሰልጣጘነት የተሾመው። ሆኖም የማንቺኒ ቡድን በቀላሉ ነበር ለዚህ ውድድር (ቶርናመንት) ያለፉት። በትኩረት ሊያዩት የሚገባ ተጫዋች ሲሮ ኢሞቢሌ’ን ነው። ከላዚዮ ጋር አሪፍ የሚባል ግዜ ቢያሳልፍም በሃገሩ ቡድን ላይ ግን አስቸጋሪ በሚባል ሁኔታን አያሳለፈ የገኛል። ሌላው ተጫዋች ደግሞ ኒኮሎ ባሬላ ሲሆን ይህ የ24 አመቱ የአማካይ መስመር ተጫዋች በጣሊያን ሊግ ላይ አሪፍ የጨዋታ ጊዜ እያሳለፈ ሲሆን ኣሁንም በሀገሩ ቡድን ላይ ተመሳሳይ የሆነ ጊዜን አንደሚያሳልፍ ይጠብቃል።

https://www.90min.com

የዚህን አመት የሲዊዘርላንዶችን ቡድን የሚያሰለጥነው ቭላድሚር ፔትኮቪች ሲሆን ከ2014 ጀምሮ በሃላፊነት ቡድኑን ይዞ ይገኛል። እስካሁን በ2016 የአውሮፓ ዋንጫ እና በ2018 የአለም ዋንጫ ለመጨረሻ አስራስደስቱ ቡድኖች ሲዊዘርላንዶችን አድርሷቸዋል። በትኩረት ልናየው የሚገባ ተጫዋች ሪካርዶ ሮድሪጌዝ ነው፤ የግራ ኋላ (ሌፍት ባክ) ተጫዋቹ በቅርቡ ጎል አስቆጥሯል እናም ለየተኛውም አይነት ቡድን ሰዊዘርላንድ ላይ የኳስ ፍሰትን በማቅረብ በግራ በኩል አስጊ መሆኑ የማይቀር ነው። በተጨማሪም ግራኒት ዣካ አለ፤ በአርሰናል አሪፍ ግዜ ባያሳለፍም ለሲዊዘርላንዶች ቁልፍ ተጫዋጭ ሲሆን ቡድኑን በጥሩ ምሳሌ ይመራዋል ተብሎ ይጠበቃል።

[adsanity align=’alignnone’ id=276]

የቱርክን ቡድን በአሰልጣኝነት የሚመራው ሲኖል ጉንስ ሲሆን በ2002 በተካሄደው የአለም ዋንጫ 3ተኛ ደረጃን ይዘው እንዲያጠናቅቁ አድርጓአል። በተጨማሪም ሁለት የቱርክ ሱፐር ሊግ ዋንጫዎችን ከቤሲክታስ ጋር ሆኖ አሸንፏል። በትኩረት ልናየው የሚገባው የሊሌ ተጫዋች የሆነው ዘኪ ሲሌክ ሲሆን፤ በዚህ አመት በፈረንሳይ ሊግ ላይ አግራሞት የጫረ ተጫዋች ነበረ። ለማጣሪያ ጨዋታ ለጎል የሚሆን ኳስ ማቀበል ባይችልም ለቱርኮች በቀኝ መስመር አስጊ እንዲሆኑ እና በጣም አሪፍ የሚባል የመከላከል አቋሙን ሊያሳየን የሚችል ተጫዋች ነው። ሌላው በትኩረት ልናየው የሚገባ የሊሌ ተጫዋች የሆነው ቡራክ ይልማዝ ሲሆን እሱም በፈረንሳይ አሪፍ የሚባል ጊዜን አሳልፏል።

[adsanity align=’alignnone’ id=276]

ዌልሹ ክሪስ ኮልማን በ2016 የአውሮፓ ዋንጫ ላይ የዌልስን ቡድን ግማሽ ፍፃሜ አድርሶ ነበር። ይህም ለዚች ትንሽ ሀገር ትልቅ ስኬት ነበር ግን አሁን ይህን ስኬት ለመድገም አዳጋች ሊሆንባቸው ይችላል። ሮብ ፔጅ የዌልስ ግዜያዊ አሰልጣኝ ሲሆን በ2017 ኖቲንጋሃም ፎረስት ነበር ማሰልጠኑን የጀመረው። በዝቅተኛ እድሜ ቡድን ደረጃም ዌልስን የመምራት ልምድም አለው። በዚህ ቡድን  ልናየው የሚገባው ጋሪዝ ቤልን መሆኑ ግልጽ ነው፤ ይህ የመጨረሻ ውድድሩ እንደሆነ እና ጫማ ለመሰቅል እያስበ እንደሆነ የሚናፈሱ ወሬዎችም አሉ። ይህ እውነት ከሆነ በጥሩ እንቅስቃሴ መውጣት እንደሚፈልግ ጥርጥር የለውም።

[adsanity align=’alignnone’ id=276]

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EURO 2020

  • Italy! The Champions! The summary of the whole tournament. Italy! The Champions! The summary of the whole tournament.

    ጣሊያን! ሻምፒዮናዎቹ! የውድድሩ ማጠቃለያ

    የምድብ ድልድል የዚህ አመት አውሮፓ ዋንጫ ቅርጽ ይዞ ማለፍ ችሏል። ለማለፍ ሲጠበቁ የነበሩት ቡድኖችም...

  • Who will be the next Champion? Who will be the next Champion?

    Who will be the next Champion?

    ጣሊያኖች የመጀመሪያውን ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት ተስጥቷችው የገቡ ሲሆን በጨዋታውም አስገራሚ እና ከፍተኛ...

  • EURO: Semi-Finals Preview EURO: Semi-Finals Preview

    EURO: Semi-Finals Preview

    Italy will face Spain የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በጣሊያን እና ስፔን መካከል ይደረጋል። በሃሳብ...

  • Last 16 Teams Preview Last 16 Teams Preview

    Last 16 Teams Preview

    Wales against Denmark ዌልሶች የምድብ ደረጃ ድልደላ ከስዊዘርላንዶች ጋር በነበራቸው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት...