Connect with us
Express news


EURO 2020

Group C Preview

Group C Preview
UEFA.com

ምድብ C ዩክሬን፣ አውስትሪያ፣ ሰሜን ማኬዶኒያ እና ኔዘርላንድን ያካትታል። አራቱም ቡድኖች በዚህ ውድድር(ቶርናመንት) ላይ የተለያዩ አላማዎች ነው ያሏቸው፤ ግን ምድብ C ውስጥ ለውጥ ሊመጣ ይችላል?

ዩክሬኖች ተጫዋቾቻቸውን የሚያጎለብቱበትን መንገድ በመቀየር ተሰጥዖ እና ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾችን በብዛት ሊያደርሱ ችለዋል። የዚህ አዲስ አሰራር ጥሩ ምሳሌዎች ታራስ ስቴፓኔንኮ፣ ኦሌክሳንደር ዚንቼንኮ እና ራሽያዊው ማሊኖቭስኪ ናቸው። እውቁ የድሮ የኤሲ ሚላን ተጫዋች እንድሪይ  ሼቭቼንኮ የዚህ ቡድን አሰልጣኝ ነው እናም አምስት አመታትን በዋና አሰልጣኝነት ሲያስቆጥር የመጀመሪያውን ዋነኛ ውድድር(ቶርናመንት) የሚሳተፈው አሁን ነው። ሌላ መከታተል ያለቦት ተጫዋች እንድሪይ ያርሞሌንኮ ነው ፤ ዘንድሮ ዩክሬኖች ስኬታማ የሚሆኑ ከሆነ ያርሞሌንኮ  እስካሁን ለዩክሬን ያስቆጠራቸው 38 ግቦች ላይ እንዲጨምር ግድ ይለዋል።

በቅርብ ግዜያት አውስትሪያዎች  ያለፉት አመታት ላይ ከነበሩት በላይ አሁን ውደ መከላከሉ እያደሉ ነው። ፍራንኮ ፎዳ በሀገሩ ላይ ስኬታማ ሊሆን ችሏል ፤ ጀርመናዊው ከስተርም ግራዝ ጋር በመሆን  የአውስትሪያን ዋንጫ በ 2010 እና በ 2011 ደግሞ የአውስትሪያን ቡንደስሊጋ አሸንፏል። ነገር ግን ይሄ ውድድር ከነበረው ልምድ አንጻር ከፍታ ያለው ውድድር ነው። አውስትሪያ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ ጨዋታ አሸንፈው  አያውቁም፤ ይሄ ሂደት እንዲቆም በጥብቅ ይፈልጋሉ እናም ይሄንን ለማድረግ ባሉበት ምድብ ጥሩ እድል አላቸው። ዴቪድ አላባ ላይ አይኖትን ያኑሩ፤ አላባ ሁለገብ የሆነ ተጫዋች ነው። በቡድን ደረጃ ለባየርሙኒክ ተከላካይ ሆነ ተጫውቶ ነበር ፤ ለአውስትሪያ ደግሞ እንደ የአጥቂ አማካኝ ሆኖ ተጫውቷል። ጫና ፈጥሮ በመጫወት በአለምአቀፍ ደረጃ አቅሙን ማሳየት ይጠበቅበታል።

ሰሜን ማኬዶኒያ ለዚህ አመቱ አውሮፓ ዋንጫ ማለፋቸውን በሚወስነው ጨዋታ ለጥቂት ነበር ያለፉት። ስለዚህ እዚህ ላይ መሻሻልን መፈለጋቸው የማይቀር ነው። ኢጎር አንጄሎቭስኪ ሌላኛው ልምድ የሚያንሰው አሰልጣኝ ነው፤ በራቦትኒኪ ላይ ካሰለጠነ ቡሃላ ይሄ ሁለተኛው የዋና አሰልጣኝነት ቦታው ነው። ኤዝጃን አሊዮስኪን ይመልከቱ፤ ይሄ የአማካኝ ተጫዋች ለሊድስ ዩናይትድ ከሚያደርገው በላይ እዚህ ሲጫወት በጥቂቱ ወደ ማጥቃቱ ያመዝናል። ከሊድስ ጋርም ጥሩ የሆነ የጨዋታ ወቅት መድገም ያስባል።

ኔዘርላንዶች የማይቋረጥ ዝቅተኛ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ቡድኖች ናቸው፤ ላለፉት ሁለት ዋነኛ ውድድሮች እንኳን ሊያይልፉ አልቻሉም ነበር። ተሰጥዖ ያላቸው ብዙ ተጫዋቾች ካለው ሀገር ይህ የማይታሰብ ነው። ኔዘርላንድ እዚ ጠንካራ እንቅስቃሴ ለማሳየት ይጥራሉ፤ ይሄ ስራ በዋነኝነት የሚያርፈው የኔዘርላንድን ዝና ለማደስ እያጣረ ያለው አሰልጣኝ ፍራንክ ድቦየር ላይ ነው። ሜምፊስ ዴፓይ ላይ አይኖትን ያኑሩ፤ በዚህ ወር ስኮትላንድ ላይ 2 ጎል አስቆጥሯል። በትክክለኛው ሰአት አሪፍ አቋም ላይ ነው ያለው።

ማን ይሆን የሚያልፈው?

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EURO 2020

 • Italy! The Champions! The summary of the whole tournament. Italy! The Champions! The summary of the whole tournament.

  ጣሊያን! ሻምፒዮናዎቹ! የውድድሩ ማጠቃለያ

  የምድብ ድልድል የዚህ አመት አውሮፓ ዋንጫ ቅርጽ ይዞ ማለፍ ችሏል። ለማለፍ ሲጠበቁ የነበሩት ቡድኖችም...

 • Who will be the next Champion? Who will be the next Champion?

  Who will be the next Champion?

  ጣሊያኖች የመጀመሪያውን ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት ተስጥቷችው የገቡ ሲሆን በጨዋታውም አስገራሚ እና ከፍተኛ...

 • EURO: Semi-Finals Preview EURO: Semi-Finals Preview

  EURO: Semi-Finals Preview

  Italy will face Spain የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በጣሊያን እና ስፔን መካከል ይደረጋል። በሃሳብ...

 • Last 16 Teams Preview Last 16 Teams Preview

  Last 16 Teams Preview

  Wales against Denmark ዌልሶች የምድብ ደረጃ ድልደላ ከስዊዘርላንዶች ጋር በነበራቸው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት...