Connect with us
Express news


EURO 2020

Group Stage Review

Group Stage Review
vecteezy.com

Group A

ከጅማሬው አንስቶ በአውሮፓ ዋንጫ ጣልያኖች ፈታኝ እና ከባድ ቡድን እንደሆኑ አስታይተዋል። ሁለቱንም ቱርኮቸን እና ስዊዘርላንዶችን 3-0 ውጤት አሸንፈዋል። ዌሊሶችንም ጨምሮ ጣሊያኖች 3ቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ የምድብ ድልድላቸውን አጠናቀዋል።

ዌልሶች እና ስዊዘርላንዶች እኩል በሆን 4 ነጥብ ሲያገኙ በላቀ የጎል ለዩነት ዌልሶች በሁለተኛነት አጠናቀዋል። ተስፋ ቢስ የነበሩትን ቱርኮችን ከማሸንፍቸው በፊት ሁለቱም የመክፈቻ ጨዋታቸውን 1-1 አቻ በሆነ ውጤት ተጋርተው አልፈዋል።

Group B

ክርስቲያን ኤሪክሰን ሜዳ ላይ ከደረሰበት ድንገተኛ አደጋ በኋላ ዴንማርኮች የወደፊት የጨዋታ እንቅስቃሴያቸው እና አቋማችው አሳስቧቸው ነበር። በአስደሳች ሁኔታም እያገገው ይገኛል። በዛን ምሽት አወዛጋቢ ሁኔታ ላይ ሁነው ደንማርኮች ከፊንላንዶች ጋር በነበራችው ጨዋታ 0-1  በሆነ ውጤት ቢሸነፉም ከምድቡ ግን ማለፍ ችለዋል።

ውድድሩን የማሸነፍ ተስፋ ተጥሎባቸው የገቡት ቤልጄሞች በቀላሉ የምድብ ድልደላውን አልፈዋል። ባደረጉት ጨዋታ አንድ ግብ ብቻ ቢያስተናግዱም ሁሉንም ጨዋታዎች አሸንፈዋል። ሮሜሉ ሉካኩ አሪፍ የሚባል ብቃቱን ሲያሳይ ሶስት ግቦችም አስቆጥሯል።

ዴንማርኮች፣ፊንላንዶች እና ሩስያዎች ለማሸነፍ የቻሉት 1 ጊዜ ብቻ ነበር። ይህ ማለት ሶስቱም በጎል ልዩነት ነበር የተለያዩት። ፊንላንዶች ሶስተኛነት ደረጃን ቢያገኙም ለማለፍ ግን በቂ ነጥብ አልነበራቸውም። ዴንማርኮች ለማለፍ ቢቀናቸውም ሩሲያዎች ኝ የመጨረሻ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

https://english.aawsat.com/

Group C

ነዘርላንዶች 100 ፐርሰንት በሆነ ሪከርድ ውጤት ጣልያኖችን እና ቤልጄሞችን መቀላቀል ችለዋል። ኔዘርላንዶች ደካማ የጨዋታ እንቅስቃሴ ባሳዩት ዩክሬኖች እና ኦስትሪያዎችን በቀላሉ በማሸነፍ ጥለው ማለፍ ችለዋል። አምበል የሆነው ጆርጂኒዮ ዊናልደም አሁንም ለሃገሩ ጎል ማግባቱን  ሲቀጥል በምድብ ደረጃ ጨዋታ ላይ 3 ግቦችን አስቆጥሯል።

ኦስትሪያዎች በሶስተኛነት ሲያጠናቅቁ ይህንንም በማድረጋቸው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል።

ምንም እንኳን ከምድቡ መጨረሻ ሆነው ቢያጠናቅቁም ሰሜን ሜቄዶንያዎች የማይረሳ የውድድር ጊዜን አሳልፈዋል። ከምድቡ ማለፍ ባይችሉም ከውድድሩ ጠቃሚ የሆነ ተሞክሮ ውስደዋል።

ዩክሬን ከሰሜን መቄዶናያ ጋር በነበራት ጨዋታ ማሸነፍ ስትችል በሶስተኛነት ደረጃ ካሉት ምርጥ ቡድኖች አንዷ መሆን ችላለች።

Group D

እንግሊዞች ከምድብ D የበላይ ሆነው ሲያጠናቅቁ በምድቡም የ2018 የአለም ዋንጫ ሶስተኛነትን ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት ክሮሽያዎችን ያካተተ ነበር። እንግሊዞች በራሂም ስትርሊንግ ግብ አማካኝነት ከሮሽያ እና ከቼክ ሪፒብሊኮች ጋር በነበራቸው ግጥሚያ 1-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። እንግሊዞች በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታ ጀርመኖችን ይገጥማሉ።

ከ 1998 ወዲህ ስኮትላንዶች በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ሲሳተፉ የመጀመሪያቸው ነው። የውድድር ጊዜያቸውንም ባአሳዛኝ ሁኔታ አጠናቀዋል። ሃገራቸው ባደረጉት ጨዋታ ፓርትሪክ ሺክ ለቼክ ሪፑብሊኮች እንዲሁም ሉካ ሞድሪች ለክሮሺአዎች ባገቡት ግብ ተሸንፈዋል።

ክሮሺያ ከምድብ D በሁለተኛነት አጠናቀዋል። በሂደታቸውም ቼክ ሪፐብሊኮች የሶስተኛነት ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ቼኮች በፓትሪክ ሺክ አማካኝነት እስካሁ ድረስ በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከረጅም ርቀት ጎል አስቆጥረዋል።

https://en.africatopsports.com/

Group E

ምድብ E ለስፔኖች ቀላል ነው ተብሎ ቢገመትም እንደታሰበው ግን አልነበረም። የሁለት ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮኖቹ ከስዊድን እና ፖላንድ ጋር ባደረጉት ጨዋት ውጤት ተጋርተዋል ሆኖም ግን ከስሎቫኪያ ጋር ባደረጉት ጨዋት 5 ጎሎችን በማስቆጠር ማንሰራራት ሲችሉ በዚህ የአውሮፓ ዋንጫ በተደረጉት ጨዋታዎች ትለቁ ድል ሆኖ ተመዝግቧል።

ፖላንዶችም በደካማ አቋም ውድድሩን ቀጥለዋል። ልክ እንደ 2018 የአለም ዋንጫ በዚህም ውድድር ከምድባቸው የመጨረሻ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። በሮበርት ሊዋንዶዎስኪም በጣም ይተማመኑ ነበር።

ፖላንዶችን በአስገራሚ ሁኔታ ቢያሸንፉም የስሎቫኪያዎች አቋም ግን በቂ አልነበረም። እንቁ የሆነው ተጫዋቻቸው ማረክ ሃምሲክ ላይ በጣም ይተማመኑ ነበር። በስፔኖች በደረሰባቸው 5-0 ሽንፈት ግማሽ ፍጻሜው እንደማይገባቸው አሳይቷል።

ስዊድኖች ከምድብ ድልደላ ከተጠበቁት በላይ ሆነው ተገኝተዋል። ከምድቡ በብቸኛት የማሸነፍ ግምት ያልተሰጣቸው ስዊድኖች ቀሪ ሁለት ጨዋታቸውን ከማሸነፋቸው በፊት ከስፔን ጋር ባደረጉት ጨዋታ 0-0 በሆነ ውጤት አቻ የውጡ ሲሆን በጨዋታውም የኳስ ይዞታ እንቅስቃሴያቸውም 15 ፐርሰንት ብቻ ነበር። ሶስት ግቦችን ላስቆጠረው ኢሚል ፎርስበርግ ስዊድኖች ማመስገን ይችላሉ።

Group F

በሃሳብ ደረጃ ይህ በጣም ከባድ ምድብ ነበር። የአውሮፓ ዋንጫ በማሸነፍ መምራት ላይ የሚገኙት እና የቀድሞ የአውሮፓ ዋንጫ አንሸናፊዎች ሁሉም በምድብ F ውስጥ ይገኙ ነበሩ። ስለሆነም በተስጥኦ አነስተኛ የነበሩት ሃንጋሪያኖች ባሳዩት አቋም ሊኮሩ ይገባል። ፖርቹጋሎችን ለ 84 ደቂቃ ያልግብ ሲይዙ፤ ከፈረንሳዮች ጋር 1-1 በሆነ ውጤት አቻ ወተዋል ጀርመኖችን በሙኒክ ሁለቴ መምራት ችለውም ነበር። ሆኖም ግን ከምድቡ ድልደላ ማለፍ አልቻሉም።

ፈረንሳዮች ምድቡን የበላይ ሆነው ሲያጠናቅቁ የመክፈቻ ጨዋታቸው ላይ ጀርመኖችን 1-0 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ጠቅሟቸዋል። ሃንጋሪዎችን ለመርታት ቢከብዳቸውም ከፖርቹጋሎች ጋር የምድብ አንዱ መሻጭ እና አዝናኝ ጨዋታ አድርገው ነበር። ውጤት መጋራታቸውም በፖል ፖግባ እና በ ኒጎሎ ካንቴ መካከል ያልውን ግንኙነት በይበልጥ አጠንክሮታል። አንድላይ በመሆን 30 ጨዋታዎችን ያስጀመሩ ሲሆን ፈረንሳዮች በነዚህም ጨዋታ አልተሸነፉም።

ጀርመኖች ከትልቅ ውርደት ራሳቸውን ያተረፉ ሲሆን ሃናጋሪዎች ለማሸነፍ በተቃረቡበት ሰአት በሊዮን ጎሬትዝካ  ባገባት ግብ አማካኝነት ውጤት ተጋርተው መውጣት ችለዋል። በቀጣዩም ጨዋታ ፖርቹጋሎች ላይ 4 ግቦችን ማስቆጠርም ችለዋል። በዚህም እንቅስቃሴያቸው ይበልጡኑ እንዲጠበቁ አድርጓል።

ታሪክ ራሱን ይደግም ይሆን? ፖርቹጋሎች የ2016ቱ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ እንዳደረጉት አሁንም በተመሳሳይ ሁኔታ ከምድባቸው የሶስተኛነትን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። በሄዱበት በስጋት የሚንቀሳቀሱ ሲሆን አሁንም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ቁልፉ ተጫዋቻቸው ነው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EURO 2020

 • Italy! The Champions! The summary of the whole tournament. Italy! The Champions! The summary of the whole tournament.

  ጣሊያን! ሻምፒዮናዎቹ! የውድድሩ ማጠቃለያ

  የምድብ ድልድል የዚህ አመት አውሮፓ ዋንጫ ቅርጽ ይዞ ማለፍ ችሏል። ለማለፍ ሲጠበቁ የነበሩት ቡድኖችም...

 • Who will be the next Champion? Who will be the next Champion?

  Who will be the next Champion?

  ጣሊያኖች የመጀመሪያውን ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት ተስጥቷችው የገቡ ሲሆን በጨዋታውም አስገራሚ እና ከፍተኛ...

 • EURO: Semi-Finals Preview EURO: Semi-Finals Preview

  EURO: Semi-Finals Preview

  Italy will face Spain የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በጣሊያን እና ስፔን መካከል ይደረጋል። በሃሳብ...

 • Last 16 Teams Preview Last 16 Teams Preview

  Last 16 Teams Preview

  Wales against Denmark ዌልሶች የምድብ ደረጃ ድልደላ ከስዊዘርላንዶች ጋር በነበራቸው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት...