Connect with us
Express news


EURO 2020

Last 16 Teams Preview

Last 16 Teams Preview
https://www.mysportdab.com/

Wales against Denmark

ዌልሶች የምድብ ደረጃ ድልደላ ከስዊዘርላንዶች ጋር በነበራቸው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት ተጋርተው ሲወጡ ቱርኮችን ደግሞ 2-0 ማሸነፍ ችለዋል በመጨረሻ ጨዋታቸውም በጣልያኖች 1-0 ቢረቱም ከምድብ A በማለፍ አጠናቀዋል።

በአሮን ራምሴ እና በጋሪዝ ቤል መካከል የነበረው ጥምረት ለዌልሶች እድል ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።

ዴንማርኮች የአውሮፓ ዋንጫ ጅማሬያቸውን በክርስቲያን ኤሪክሰን ድንገተኛ አደጋ ጀምረዋል። የመክፈቻ ጨዋታቸውን በፊንላንድ 1-0 እንዲሁም ቀጣይ ጨዋታቸውም በቤልጄም 2-1 ቢሸነፉም በመጨረሻም ከሩሲያዎችጋር በነበራቸው ጨዋታ 4-1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስተኛነት ደረጃን ይዘው ከምድብ B ማጠናቀቅ ችለዋል። በቅርቡ ዴንማርኮች ዩሱፍ ፖልሰንን አጥተዋል። ይህ ክስተት የካስፐር ሂጁልማድንን ቡድን ሊረዳው ይችላል ወይስ በፊት መስመሩ ድክመት ሊጎዱ ይችላሉ?

Italy versus Austria

ጣልያኖች ቱርኮችን (3-0)፣ስዊዘርላንዶችን (3-0) እንዲሁም ዌልሶችን 1-0 በሆነ ውጤት በመርታት ከምድብ A በበላይነት ማለፍ ችለዋል።

አሰልጣኝ ሮበርቶ ማንቺን የፊት መስመር ተጫዋች የሆነውን ሲሮ ኢሞቢሌ ላይ አሁንም ጥሩ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል እና ጆርጂኖ የአማካኝ መስመሩን እንድሚራ ተስፋ ጥሎባቸዋል።
የፍራንኮ ፎዳ ኦስትሪያዎቹ ከምድብ C ያለፉ ሲሆን ሰሜን መቄዶኒያን 3-1 እና ዩክሬኖችን 3-1 ሲያሸንፉ ሆኖም ግን በኔዘርላንዶች 2-0 በሆነ ውጤት ተረተዋል።

ዴቪድ አላባ ኦስትሪያዎች ምርጥ ተጫዋች ቢሆንም ግን ማርሴል ሳቢትዘር እና ክሪስቶፈር ቧምጋርትነር የተለዋዋጭ አማካኝ መሰመር ተጫዋቾች ለማርኮ አንርናቶቪች ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ቢያቀብሉትም እራሳቸውም ማግባት ይችላሉ።

Netherlands against Czech Republic

ኔዘርላንዶች ከዩክሬኖች ጋር (3-2)፣ ኦስትሪያዎችን (2-0) እንዲሁም ሰሜን መቄዶንያንዎችን (3-0) በሆነ ውጤት በማሸፍ ከምድብ c የበላይ ሆነው ማለፍ ችለዋል።

ሁሉም የኔዘርላንዶች ጨዋታ በሃገራቸው ሜዳ ላይ ተደርጓል። ሲለዚህም አሰልጣኝ ፍራንክ ዲቦየር እንደ ሜንፊስ ዲፓይ ያሉ ኮከብ ተጫዋቾች በሚንጓጓዙበት ጊዜ ያሉበትን አቋም እንዳይቀይሩ ተስፋ አለው።

ቼክ ሪፐብሊኮች ሶስተኛነት ደረጃን በመያዝ ከሚድብ D ማጠናቀቅ ችለዋል። ስኮትላንዶችን 2-0 ሲያሸንፉ ከክሮሺያዎች ጋር 1-1 በሆነ ውጤት አቻ ወተዋል። በመጨረሻቸውም ጨዋታ በእንግሊዞች 1-0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

Belgium versus Portugal

ቤልጄሞች ከምድብ B ምንም አይነት ችግር አልገጠማቸውም። ሩሲያዎችን 3-0 ዴንማርኮችን 2-1 እንዲሁም ፊንላንዶችን 2-0 በሆነ ውጤት ተጋጣሚያቸውን መርታት ችለዋል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከኬቨን ዲቡሬይኒ እና ከሮሜሉ ሉካኩ አይነት ተጫዋቾች ይበልጡኑ ይጠብቃሉ።

ፖርቱጋሎች ከምድብ F በሶስተኛነት አጠናቀዋል። ሃንጋሪን 3-0 ሲረቱ ከፈረንሳዮች ጋር 2-2 በሆነ ውጤት አቻ ወተዋል ሆኖም ግን በጀርመኖች 2-4 ተሸንፈዋል።

የፖርቹጋሎች አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ ለማንኛውም ቡድን ስጋትን መፍጠር የሚችሉ እናም በቂ የሆነ የማጥቃት ጥበብ ያለችውን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዲያጎ ጆታ እና ቡሩኖ ፈርናንዴስ አይነት ተጫዋቾች በስብስቡ ይገኛሉ።

cnn.com

Crotia will compete with Spain

የዚላትኮ ዳሊች ክሮሺያዎች የምድብ D መክፈቻ ጨዋታቸውን በእንግሊዞች 1-0 በመሸነፍ ጀምረዋል። ክሮሺያዎች ከ ከቼክ ሪፐብሊኮች ጋር 1-1 አቻ በመውጣት እና ስኮትላንዶችን 3-1 በማሸነፍ ምድቡን ማለፍ ችለዋል።

ከስኮትላንዶች ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ ሉካ ሞድሪች ምን ያህል ብቃት እንዳለው ሁሉም እንዲታዘቡ አድርጎ ነበር። በቀጣዩም ዙር ሌሎች ቡድኖች እሱን እና ኢቫን ፐርሲችን መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል።

ስፔን በሁለት አቻ ውጤቶች (ከስዊድኖች ጋር 0-0 እና ከፖላንዶች ጋር 1-1 ) በቀስታ ሲጀሚሩ ህኖም ስሎቫኪያዎችን 5-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በሁለተኛነት ደረጃ ከምድብ E ማለፍ ችለዋል።

ከስሎቫኪያ ጋር በሚያደርጉት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋት ላይ አሰልጣኝ ሉዊስ እንሪኬ ከእረፍት ወዲህ በማንሰራራት ወደፊት ማጥቃት ይኖርበታል።  ፔድሪን በትኩረት ሊመለከቱት ይገባል።

France versus Switzerland

ከምድብ F በአንደኝነት ያጠናቀቁት ፈረንሳዮች ጀርመኖችን 1-0 በማሸነፍ እና ከሃንጋሪዎች ጋር 1-1 እንዲሁም ፈታኝ ጨዋት የነበረው ከፖርቹጋሎች ጋር 2-2 በሆነ ውጤት አቻ ውተዋል።

ፈረንሳዮች በዚህ አለም ዋንጫ ከመክፈቻ ጨዋታቸው ውጪ ማሸነፍ አልቻሉም። ፈረንሳዮች ተግባብተው መጫወት ከቻሉ ለሌሎች አስጊ ቡድን ይሆናሉ።

ከዌልሶች ጋር 1-1 በሆነ ውጤት አቻ ከወጡ በኋላ ከምድብ A ያልፉት ስዊዘርላንዶች በጣሊያን 3-0 ሲሸነፉ ቱርኮችን 3-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
ለስዌዘርላንዶች የቭላድሚር ፔትኮቪች ቁልፉ ተጫዋቾች እስካሁን ድርስ አዝነዋል። ዤርዳን ሻኪሪ ከቱርኮች ጋር በተደረገው ግጥሚያ ላይ 2 ግቦችን ቢያስቆጥርም በሌሎች

England will face Germany

እንግሊዞች ከክሮሽያ እና ከቼክ ሪፐብሊኮች ጋር 1-0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ ከ ስኮትላንዶች ጋር 0-0 በሆነ ውጤት አቻ በመውጣት ከምድብ D በአንደኝነት ማለፍ ችለዋል።

የጋሪዝ ሶውዝጌት ተጫዋቾች ከጎል መረብ ፊት ለፊት ፈጣን መሆን አለባቸው። ለኢንግሊዞች እስካሁን ድረስ ራሂም ስተርሊንግ ብቻ እያገባ ይገኛል። ሄሪ ኬን ግን ግብ ማስቆጠር አለበት።

ጀርመኖች በመጨረሻ ሰአት ሃንጋሪዎች ላይ ባስቆጠሩት የግብ አቻ በመውጣት ከምድብ F ማለፍ ችለዋል። ከዚ ጨዋት በፊትም በፈረንሳዮች 1-0 ሲሸነፉ ፖርቹጋሎችን ደግሞ 4-2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። አሰልጣኝ ጆአችም ሎው ወጥ የሆነ አቋም ይፈልጋሉ። ጃሽዋን ኪምች ሙሉ አቅሙን እንዲጠቀምም የእሱ ስራ ነው። ሎው ከቦት ቦታ እንዲጫወት ቢያደርገውም መለስ ብሎ ቢያስብበት ሳይሻል አይቀርም።

https://www.aljazeera.com/

Sweden against Ukraine

የጄን አንደርሰን ስዌድኖች ከስፔኖች ጋር 0-0 በሆነ ውጤት ሲጋሩ በመቀጠልም ስሎቫኪያዎችን 1-0 እና ፖላንዶችን 3-2 በማሸነፍ ከምድብ E በአንደኝነት አጠናቀዋል።

ወደ ቀጣዩ ጨዋታም ሲገቡ ስዊድኖች አስደናቂ ብቃት ካለው አሊክሳንደር ኢሳክ እና የኢሚል ፎርስበርግስ ሶስተኛ ጨዋታው ላይ ግብ እንዲያስቆጥሩ ይጠብቃሉ።

ዩክሬኖች በመክፈቻ ጨዋታቸው ላይ በኔዘርላንዶች 2-3 ቢሸነፉም የንድሬ ሼቭሼንኮ ተጫዋቾች ከምድብ  C ለማለፍ ሰሜን መቄዶንያንዎችን 2-0 እንዲሁም ኦስትሪያዎችን 1-0 አሸንፈዋል።

በያርሞለንኮ ከያሪምቹክ እና ማሊኖቪስኪ ባለው ትምረት የፊት መስመራቸው ቢያሰጋም የተከላካይ መስመራቸውን ማሻሻል ይኖርባቸዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EURO 2020

  • Italy! The Champions! The summary of the whole tournament. Italy! The Champions! The summary of the whole tournament.

    ጣሊያን! ሻምፒዮናዎቹ! የውድድሩ ማጠቃለያ

    የምድብ ድልድል የዚህ አመት አውሮፓ ዋንጫ ቅርጽ ይዞ ማለፍ ችሏል። ለማለፍ ሲጠበቁ የነበሩት ቡድኖችም...

  • Who will be the next Champion? Who will be the next Champion?

    Who will be the next Champion?

    ጣሊያኖች የመጀመሪያውን ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት ተስጥቷችው የገቡ ሲሆን በጨዋታውም አስገራሚ እና ከፍተኛ...

  • EURO: Semi-Finals Preview EURO: Semi-Finals Preview

    EURO: Semi-Finals Preview

    Italy will face Spain የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በጣሊያን እና ስፔን መካከል ይደረጋል። በሃሳብ...

  • Group Stage Review Group Stage Review

    Group Stage Review

    Group A ከጅማሬው አንስቶ በአውሮፓ ዋንጫ ጣልያኖች ፈታኝ እና ከባድ ቡድን እንደሆኑ አስታይተዋል። ሁለቱንም...