Connect with us
Express news


EURO 2020

Turkey, is it you? The real dark horse of EURO 2021.

Turkey, is it you? The real dark horse of EURO 2021.
theanalyst.com

በዘንድሮው ዩሮ በርካታ ብዙም የማይጠበቁ ግን የማሸነፉ ብቃት ያላቸው ቡድኖች አሉ። ይሁን እንጂ ቱርኮች በተለየ መልኩ ጎላ ብለው የሚታዩ የውርርድ አማራጮች ናቸው።

በመጀመሪያ ቱርኮች ጠንካራ ተከላካዮች አሏቸው እናም ብዙ ግዜ አሪፍ ቡድኖች ከወደኋላ በኩል በጠንካራ መሰረት ነው የሚጀምሩት። ቱርኮች ማጣሪያውን በጣም በአሪፍ ሁኔታ ነበር ያለፉት። በአለም ሻምፒዮኖቹ በፈረንሳዮች  ብቻ በመቀደም ከምድባቸው 2ኛ ሆነው ነው የጨረሱት። ጠንካራው የቱርክ ቡድን በአለም 2ኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ቡድን 4 ነጥብ ሊወስዱ ችለዋል እናም ምድባቸው ውስጥ የአንደኝነቱን ቦታ ለትንሽ ነው ያጡት። ለዚህ ውድድር(ቶርናመንት) ለማለፍ በተደረጉት ጫዋታዎች ውስጥ 3 ጎል ብቻ ተቆጥሮባቸው 8 ጨዋታዎች ላይ ደግሞ ምንም አይነት ጎሎቶችን ሳያስተናግዱ ጨርሰዋል። ክላጋር ሶዩንኩ በጣም ጠንካራ ተከላካይ ነው። ሌላኛው አሪፍ ተከላካይ ደግሞ ጥሩ የሸርታቴ ታክል መግባት የሚወደው ሜሪዝ ፌሞራል ነው። ከወደኋላ በቀኝ በኩል ደግሞ መህመት ዘኪ ሴሊክ ለሊሌ  በዚህ የውድድር ወቅት በአሪፉ ሲጫወት ነበር። በተከላካዮች በኩል ሊኖር የሚችለው ብቸኛ ድክመት ከወደኋላ በግራ በኩል ነው፤ እዚህ ጋር ደግሞ አሰልጣኝ ሴኖል ጉንስ ልምድ የሊላቸው ተጫዋቾች ብቻ ነው ከስሩ ለምርጫ ያሉት። ሆኖም ግን እነዚህ ወጣቶች በዚህ አመት ስማቸውን ለማስጠራት ጥሩ እድል አላቸው።

dailysabah.com

ቱርኮች በተጨማሪም ደህና የሚባሉ የአማካኝ ተጫዋቾች አሏቸው። በማጥቃትም በመከላከልም የሚጫወተው ተጫዋች ኦዛን ቱፋን የተከላካይ አማካኝ  ከሆነው ብዙም ካልተዘመረለት ጀግና ኦኬይ ዮኩሱሉ ጋር ጠንካራ ወዳጅነት ለመፍጠር ይሞክራል። ዩሱፍ ያዚቺ በሊሌ በጣም አሪፍ የጨዋታ ወቅት ነበረው፤ የአጥቂ አማካይ ሆኖ ነው የሚጫወተው። ሆኖም ግን ሀካን ካልሀኖግሉ እና ሴንዲዝ አንደር በውድድር እና በችሎታ ለተሞላው የአማካኝ ቦታ በጥብቅ ይፎካከራሉ።

ከፊት ለፊት አጥቂዎቹ በዚህ ውድድር ወቅት በጣም ጥሩ አቋም ላይ ነው ያሉት። ቡራክ ይልማዝ እድሜው እየጨመረ በመጣ ቁጥር እሱም እየተሻሻለ የሚሄድ ነው የሚመስለው እናም በዚህ የውድድር ወቅት ለሊሌ ኳስን ከመረብ ማገናኘት ሊያቆም አልቻለም፤ እንደ ኬናን ካማራን ችሎታ ባላቸው የወጣት አጥቂዎች ስብስብ ድጋፍን ያገኛል።

ቱርኮች ውድድሩ(ቶርናመንቱ) ለአንድ አመት በመራዘሙም ደስተኛ ሆነዋል። ደስተኛ የሆኑበት ምክንያትም መሪህ ደሚራል፣ ዩሱፍ ያዚቺ እና ኦዛን ካባክ ያለፈው አመት በጉዳት ምክንያት ሁሉም ከውድድር ውጪ ስለነበሩ ነው። ሁሉም ተጫዋቾች አሁን አገግመው አሪፍ የሆነ የጨዋታ ወቅት ከቡድኖቻቸው ጋር አሳልፈዋል። ሆኖም ግን ምንም እንኳን ካባክ ድጋሚ ጉዳት ቢደርስበትም ቱርኮች ከአምናው ይበልጥ አሁን ጠንካራ ይመስላሉ።

ሌላ ብዙም የማይጠበቁት ግን የማሸነፉ ብቃት ካላቸው ቡድኖች የሚካተቱት ከአለም አደገኛውን አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶውስኪን የያዙት ፖላንዶች እና ጣልያን ናቸው። አስካሁን ድረስ ጣልያኖች ብዙም ከማይጠበቁ ቡድኖች ጋር አይካተቱም ነበር ነገር ግን በዚህ አመት ስብስባቸው እንደሌላው ግዜ ጠንካራ አይመስልም። 

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EURO 2020

 • Italy! The Champions! The summary of the whole tournament. Italy! The Champions! The summary of the whole tournament.

  ጣሊያን! ሻምፒዮናዎቹ! የውድድሩ ማጠቃለያ

  የምድብ ድልድል የዚህ አመት አውሮፓ ዋንጫ ቅርጽ ይዞ ማለፍ ችሏል። ለማለፍ ሲጠበቁ የነበሩት ቡድኖችም...

 • Who will be the next Champion? Who will be the next Champion?

  Who will be the next Champion?

  ጣሊያኖች የመጀመሪያውን ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት ተስጥቷችው የገቡ ሲሆን በጨዋታውም አስገራሚ እና ከፍተኛ...

 • EURO: Semi-Finals Preview EURO: Semi-Finals Preview

  EURO: Semi-Finals Preview

  Italy will face Spain የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በጣሊያን እና ስፔን መካከል ይደረጋል። በሃሳብ...

 • Last 16 Teams Preview Last 16 Teams Preview

  Last 16 Teams Preview

  Wales against Denmark ዌልሶች የምድብ ደረጃ ድልደላ ከስዊዘርላንዶች ጋር በነበራቸው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት...