Connect with us
Express news


EURO 2020

ጣሊያን! ሻምፒዮናዎቹ! የውድድሩ ማጠቃለያ

Italy! The Champions! The summary of the whole tournament.
eurosport.com

የምድብ ድልድል

የዚህ አመት አውሮፓ ዋንጫ ቅርጽ ይዞ ማለፍ ችሏል። ለማለፍ ሲጠበቁ የነበሩት ቡድኖችም አብዛኛዎቹ ማለፍ ችለዋል። ይህም ማለት ወደ ጥሎ ማልፉ መቀጠል የቻሉት ጣሊያን፣ዌልስ፣ስዊዘርላንድ፣ቤልጄም፣ዴንማርክ፣ኔዘርላንድ፣አውስትሪያ፣ዩክሬን፣እንግሊዝ፣ክሮሺያ፣ቼክ ሪፐብሊክ፣ስዊድን፣ስፔን፣ፈረንሳይ፣ጀርመን እና ፖርቹጋል ናቸው።

ጥሎ ማለፍ

ዴንማርክ ዌልስን በጥሎ ማለፍ መክፈቻ ጨወታ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፈዋል ። 2 ጎል ከዶልበርግ ፣ 1 ከማህለና እንዲሁም 1 ከ ብሬዝዋይት የተገኙ ጎሎች ዴንማርክ ምድቡን ስታልፍ የዌልሶችን ልብ ግን ሰብረዋል ።

ጣልያን አውስትርያን 2-1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ። በአወስትርያው ካላድዚች ከረፈደ ያስገባት ግብ ቺሳ እና ፐሲና ቀድመው የተስቆጠሩትን ጎል ለማሸነፍ በቂ አልነበረም።

በቀጣይም 2 ለ 0 የተጠናቀቀው ጨዋታ የጃሮስላቭ ሲልሃቪ ቼክ ሪፐብሊክ ኔዘርላንድን ወደሃገራቸውን በመላክ የተሰጣቸውን የማሸነፍ እድል መገልበጥ ችለዋል ።

በ42ተኛው ደቂቃ በቲ ሃዛርድ በተቆጠረችው ግብ ቤልጅየም ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ አልፈዋል።

በውድድሩ ብዙ ጎል የተቆጠረበት ጨዋታ ስፔን ክሮሽያን 5 ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፋለች ። ስፔን ወደ ቀጣዩ ዙር ስታልፍ ክሮሽያ ሃገሯ ሸኝታታለች ።

ምናልባትም ቀጣዩ ጨዋታ በውድድሩ በጣም አስከፊ ነበር ። የአለም ሻምፒዮን ፈረንሳይዮች በስዊዘርላንድ በመለያ ቅጣት ምት ተሸንፈዋል ። 

እንግሊዞች ወደ ሩብ ፍጻሜው ለማልፍ በስተርሊግ እና በኬን ግቦች አማካኝነት የሉካስትሬን ጀርመንን አሽንፈዋል።

በመጨረሻም የአንድሪ ሼቭሼንኮ ብድን ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍ ዩክሬኖች ስዊድንን 2 ለ 1 በሆነ ውጠት አሸንፈዋል ።

ሩብ ፍጽሜ

የሩብ ፍጻሜ መክፈቻ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ከስፔኖች ጋር ያደረጉት ግጥሚያ ነበር። ቡድኖቹ ከ120 ደቂቃ በኋላ ግቦችን ማስቆጠር ስላልቻሉ ጨዋታው ወደ መለያ ቅጣት ምት ሊያመራ ችሏል። ስዊዘርላንዶች ከፈረንሳይ ጋር በነበራችው ጨዋታ ላይ በመለያ ምት አስገራሚ የሆነ አቋማቸውን መድገም ተስኗቸው የነበር ሲሆን 3-1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

በቀጣዩ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ ቤልጄም ጣሊያኖችን ገጥመዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ባሬላ እና ኢንሴግኒ ግብ ሲያስቆጥሩ በተጨማሪ ደቂቃዎች ላይ ሉካኩ ያገባት ግብ ለማሸነፍ በቂ አልነበረም። ቤልጄሞች 2-1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የሩብ ፉጻሜ ማጠናቀቂያ ጨዋታ ላይ ዴንማርኮች ለቼክ ሪፐብሊክ ፈታኝ ነበሩ። በመጀመሪያው አጋማሽ ዴላኒ እና ዶልበርግ ግብ ማግባት የቻሉ ሲሆን ቼክ ሪፐብሊኮችም 49ኛው ደቂቃ ላይ በሺክ አማካኝነት 1 ግብ ማስቆጠር ቢችሉም በቂ አልነበረም።

የመጨረሻውም የሩብ ፍጻሜ ከእንግሊዝ ጋር የነበራቸው ጨዋታ ለአንድሬ ሼቭሼንኮ ዮክሬኖች አስከፊ ነበር። ኬን 2 እንዲሁም መጓየር እና ሄንደርሰን እያንዳዳቸው 1 ግቦች በማስቆጠር ዩኬኖችን ለመርታት ከበቂ በላይ ነበር።

ግማሽ ፍጻሜ

በመጀመርያው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ጣልያን ስፔንን ገጥማለች። ቺሳ በ60ኛ ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል የማንቺኒ ጣልያኖች መምራት ችለው የነበረ ሲሆን ፣ የሉዊስ ኢንሪኬ ስፔኖች ተቀይሮ በገባው አልቫሮ ሞራታ በ80ኛ ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል አቻ መሆን ችለዋል። ተጨማሪ ግብ ባለማስቆጠራቸው ጨዋታው ወደ ቅጣት ምት ማምራት ችሏል። ጣልያኖች ቅጣት ምቱን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ፍጻሜ አልፋዋል ።

ሁለተኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በኢንግሊዝ እና በዴንማርክ መካከል ነበር የተካሄደው። ዴንማርካዊው ሁጁልማንድ ለከባድ ፈተና ተዘጋጅቶ ነበር። በዳምስጋርድ አማካኝነት በ30ኛው ደቂቃ በተቆጠረው ግብ ኢንግሊዞች 1 ለ 0 እየተመሩ ነበር ። ሆኖም የሳውዝ ጌት ኢንግሊዞች ተጭነው በመጫወት ዴንማርክን 2 ለ 1 መርታት ችለዋል።

ፍጻሜ

በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ውስጥ የሚገኘው ዌምብሌ ስታዲየም እንግሊዞች ከጣሊያን ጋር የፍጻሜ ጨዋታ አድርገዋል። ይህም ማለት እንግሊዞች ጨዋታው በሃገራቸው በመደረጉ ጠቅሟቸው ነበር። በ2ኛው ደቂቃ ሾው የመክፈቻ ግቡ ቢያስቆጥርም ጣሊያኖች ግን ቀስ በቀስ ጨዋታው ላይ ማገገም ችለዋል። ቦኑቺ በ67ኛው ደቂቃ ላይ የአቻውን ግብ ካስቆጠረ በኋላ ጨዋታው መቀየሩ ግልጽ ነበር። ሆኖም ግን በተጨማሪውም ድቂቃ ላይ ምንም ግብ ባላመቆጠሩ ወደ መለያ ቅጣት ማምራት ችለዋል። በምቱም ጣሊያኖች ሲያሸንፉ ከ1968 ወዲህ የመጀምሪያቸውን አውሮፓ ዋንጫ ማንሳት ችለዋል። ስታቲክሱም እንደሚያሳየው ጣሊያኖች ኳስ በማቀበል፣ ውደግብ በመምታት እንዲሁም ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል የበላይነቱን ይዘው ነበር። እነሱም የሰሩት ጥፋት በእጥፍም ሊጨምር ነበር ቢሆንም ግን ጣሊያኖች የዚህ አመት የአውሮፓ ዋንጭ ማሸነፍቸው ይገባቸዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EURO 2020

 • Who will be the next Champion? Who will be the next Champion?

  Who will be the next Champion?

  ጣሊያኖች የመጀመሪያውን ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት ተስጥቷችው የገቡ ሲሆን በጨዋታውም አስገራሚ እና ከፍተኛ...

 • EURO: Semi-Finals Preview EURO: Semi-Finals Preview

  EURO: Semi-Finals Preview

  Italy will face Spain የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በጣሊያን እና ስፔን መካከል ይደረጋል። በሃሳብ...

 • Last 16 Teams Preview Last 16 Teams Preview

  Last 16 Teams Preview

  Wales against Denmark ዌልሶች የምድብ ደረጃ ድልደላ ከስዊዘርላንዶች ጋር በነበራቸው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት...

 • Group Stage Review Group Stage Review

  Group Stage Review

  Group A ከጅማሬው አንስቶ በአውሮፓ ዋንጫ ጣልያኖች ፈታኝ እና ከባድ ቡድን እንደሆኑ አስታይተዋል። ሁለቱንም...