Connect with us
Express news


Football

የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፣ በአለም ላይ የተሻለው የሊግ ውድድር ?

https://todayuknews.com/

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል.) ለምን በዓለም ላይ ምርጥ ሊግ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ ብዙ አሳማኝ ክርክሮች አሉ ፡፡

ውድድር

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል) በአለማችን ከፍተኛ ፍክኩር የማይታይበት ሊግ ስለመሆነ መከራከር በጣም ይከብዳል ። በ 2105 -2016 የውድድር ዘመን በውድድሩ መጀመርያ ላይ በጣም ያልታወቁ የነበሩት ሌስስተር ሲቲዎች የሊጉ ዋንጫ ማንሳታቸው ለዚህ አንድ ጥሩ ማሳያ ነው ። ይህ ምናልባት ከብዙ ዘመናት አንድ ግዜ ብቻ የሚከሰት ልዩ ምሳሌ ነው ፣ እውነታው ግን ዘላቂ ነው ፣ ኢ.ፒ.ኤል.ን በሚመለከቱበት ጊዜ ማንኛውም ቡድን ሌላኛውን ቡድን ሊያሸንፍ ይችላል የሚል ስሜት ይሰማዎታል ፡፡

ኮከብ ተጫዋቾች

ከሌሎች የአውሮፓ ሊጎች በተለየ ፣ የማንም ቡዱን ደጋፊ ብትሆንም የአለማችን ከፍተኛ ኮከብ ተጫዋቾች የተለያዩ ግጥምያዎች ሲያረጉ የማየት እድል ታገኛለህ ። ለምሳሌ ፤ ኢ.ፒ.ኤል ለ2012ቱ የአውሮፓ ዋንጫ 74 ተጨዋቾች አስመርጧል ፣ ይህ ደግሞ ወደ 20 % ገደማ ነው ። የጀርመን ቡንደስሊጋ 48 ተጫዋቾች በማስመረጥ 2ኛ ደረጃ ሲይዝ ፣ ላሊጋ 32 እና ሰሪኤ 31 በማስመረጥ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል ።

https://bleacherreport.com/

ስታዲየም

በኢ.ኢ.ፒ. ውስጥ የሚገኙት 10ቱም ምጥ ክለቦች ሁሉም ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የቤት ሜዳ አሏቸው ። ኦልድ ትራፎርድ (ኤ ኬ ኤ የህመኛች ትያትር)፣ አንፊልድ እና ኢሚራተስ ሌሎች አገራት እሚያስቀና አገልግሎት መስጠት እሚችሉ ሜዳዎች ናቸው ። ሻምፒዮንስሊጉን ማለፍ ተስኑቸው አሁን በአውሮፓ እግርኳስ የኮንፈረንስ ሊግ በመሳተፍ እሚገኙት ቶትንሃሞች እንኳን አዲስ እና የጥበብ ስታዲየም አላቸው ። ወደ ሊጉ በደንብ ገብተን የታችኞቹ ብዱን ብንመለከት ፣ ትልቅ ዘመናዊ እና ጥሩ መጫወቻ ስታዲየም አላቸው ።

የቴሌቭዥን ሽፋን

ኢ.ፒ.ኤል. በዓለም አቀፍ ደረጃ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይመለከታሉ ፡፡ ወደ 200 እሚጠጉ አገራትም ግጥሚያዎችን በቀጥታ ያስተላልፋሉ ። ከነዚህ ቴሌቭዥኖች እሚገኘው ገቢ በጣም ትልቅ ነው ፤ ነገር ግን ኢ.ኤል.ፒ.ን ከአብዛኞቹ ሌሎች ሊጎች የሚለየው እነዚህ ገንዘቦች በሁሉም ክለቦች ውስጥ እኩል መሰራጨታቸው ነው ፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ አሰራር እሚከተል ቡንደስሊጋ ብቻ ነው ። በስፔን አብዛኛው ገንዘብ እሚወስዱት ብዙ ተመልካች ያገኙ ክለቦች ናቸው ። ዋነኞቹ ተጠቃሚዎች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ናቸው ብሎ መገመት ሽልማት አያሰጥም!

arsenal.com

ደረጃ

ከ 9 ዓመታት በኋላ ኢ.ፒ.ኤል ዩኢኤፍኤ መሠረት አሁን በዓለም ላይ ምርጥ ሊግ ደረጃ መሰጠቱ ይፋ ተደርጓል፡፡ ላሊጋ ይህንን ቦታ ለአስር ዓመታት ይዞ የቆየ ቢሆንም ግን ማንቸስተር ዩናይትድ በኤሮፓ ሊግ 6-2 ኤስ ሮማን ካሸነፈ በኋላ አሁን ላይ በአውሮፓ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል መሠረት ኢ.ፒ.ኤል ምርጡ ሊግ ሆንዋል ።

ድባብ

የኢ.ፒ.ኤል. ድባብ የማይነጻጸር ነው። ትናንሽ ቡድኖች ተብለው ከሚጠሩ ቡድኖች እንኳ በደጋፊዎቻቸው የተፈጠረው ጉልበት ፣ ጉጉት ሊታይ የሚችል ነው፡፡ ይህ በመላው አውሮፓ የማይታይ ነገር ነው እናም ኢ.ፒ.ኤልን ልዩ እና ምናልባትም በዓለም ላይ ምርጥ ሊግ ያደርገዋል።

https://www.goal.com/

ግቦች

ምንም እንኳን ኢ.ፒ.ኤል በአውሮፓ ውስጥ በአንድ የጨዋታ ጥምርታ ከፍተኛ ግቦች ባይኖሩትም (የደች ኤሪዲቪሲ ያንን ክብር ይወስዳል) ፣ ምናልባት በዚያ ምድብ ውስጥ ብዙ ግቦች እንዳይገቡ በመከላከል ብቃታቸው ነው ሊባል ይችላል፡፡ በጣም በቅርብ ጊዜያት ውስጥ 1,023 ግቦች በኢ.ፒ.ኤል ውስጥ የገቡ ሲሆን በአማካይ በአንድ ጨዋታ ላይ 2.69 ግቦች ተቆጥረዋል፡፡ በላሊጋ 942 የገቡ ሲሆን በአንድ ጨዋታ በአማካይ በ 2.48 መረብ ላይ ማገናኘት ችለዋል። ስለዚህ ምናልባትም ከኔዘርላንድ ቀጥሎ ኢ.ፒ.ኤል. ላይ ግቦችን የሚጠበቅበት ሊግ ነው ፡፡

በአውሮፓ ምርጡ ሊግ ነው?

የአውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ንጉስ የሆነውን ኢ.ፒ.ኤልን ለመሰየም አጸፋዊ ክርክሮች ነበሩ። መጀምሪያ በዚህ አለም አሪፉ ተጫዋች የሚባለው በኢ.ፒ.ኤል ውስጥ ይጫውታል ? ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆነው አይጫወትም እሚል ነው። በእርግጠኝነት ፣ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ብዙ ከፍተኛ ተጫዋቾች ከሳምንት ሳምንት በኢ.ፒ.ኤል. ይጫውታሉ። ሆኖም ፣ በዚህ ጊዜ ጨዋታ ላይ በሌሎች ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ውስጥ ክለቦች ለማስፈረም አዝማሚያ እንዳላቸው በቀላሉ ለመከራከር ይቻላል። ለዚህም ብዙ ምሳሌዎች አሉ። የዚህ ክፍለ ዘመን ከፍተኛ ተሰጥዖ ያለው ሊዮኔል ሜሲ ህይወቱን በሙሉ በባርሴሎና ለማሳለፍ መርጧል። ክሪስቲያኖ ሮናልዶ እንኳን ማንችስተር ዩናይትድን ለቆ በስፔን ውስጥ ለመጫወት መርጧል እንዲሁም ኔይማር በፓሪስ ከኪሊያን ምባፔ ጋር በመሆን ይጫወታል (ምንም እንኳን ወደ ሊቨርፑል ሊዛወር ይችላል የሚል ወሬ ቢኖርም)።

በተጨማሪም ፕሪሚየር ሊጉ ከመጠን በላይ የሚደነቅና ከመጠን በላይ ተዋውቋል የሚል ክርክር አለ። የአንዳንድ ሰው አስተያየት ሌሎች ሊጎች በእኩል በሆነ መጠን ለአለም ቢተዋወቁ እነሱም ‹የዓለም ምርጥ ሊጎች› ተብለው ሊወሰዱ ይችላሉ የሚል ነው፡፡ ይህንን እውነታ ጋር ያጣምሩ (ከጥቂት እውነታ በስተቀር) ብዙ የኢ.ፒ.ኤል ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግን ያላነሱ ሲሆኑ ምናልባትም እርስዎ ኢ.ፒ.ኤል በዓለም ላይ ምርጥ ሊግ አለመሆኑን የሚያሳይ የተወሰነ ሃሳብ ይኖርዎታል፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football