Connect with us
Express news


Football

የወንዶች ኦሎምፒክ እግር ኳስ ውድድር

Men’s Olympic Football Competition
https://www.sportsadda.com/

የአውሮፓ ዋንጫ እና ኮፓ አሜሪካ አልቀው ሊሆን ይችላል ፣ ግን የዓለም አቀፉ የክረምት እግር ኳስ ገና አላበቃም! አሁንም የወንዶች ኦሎምፒክ የእግር ኳስ ውድድር አጓጒ ሆኖ ቀጥሏል እና አሁንም ጨዋታዎች እየተደረጉ ነው!

በእያንዳንዱ የበጋ ኦሎምፒክ ውስጥ ማለት ይቻላል የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ሲካሄድ ቆይቷል። ያልተኪያሄደባቸው ብቸኛ አመቶች በ 1896 እና በ 1932 ነበሩ። የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ገና ስላልተቋቋመ በ 1896 ጨዋታዎች ውስጥ እግር ኳስ አልተካተተም።  እ.ኤ.አ. በ 1896 ዓለም አቀፍ እግር ኳስ ገና በጨቅላነቱ ነበር ስለሆነም ስፖርቱ እስከ 1900 የበጋ ኦሎምፒክ በፓሪስ እስኪደረግ አልተካተተም ነበር።  ፊፋ አዲስ ውድድርን ለማስተዋወቅ በመሞከር ውድድሩን ለማቋረጥ በመወሰኑ በሎስ አንጀለስ 1932 ውድድሮች ላይም አልተካተተም ።  የአሁኑ ሻምፒዮን ብራዚል ነው ፣ ግን በታሪክ ስንሄድ ይህ ውድድር እያንዳንዳቸው 3 ጊዜ በማሸነፍ በሃንጋሪ እና በታላቋ ብሪታንያ የበላይነት ተይዟል።  ብራዚል ሻምፒዮን የሆነችው አንድ ጊዜ ብቻ ነው እሱም ባለፈው የበጋ ኦሎምፒክ ላይ ነበር።

የዚህ ዓመት ውድድር

በወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ውስጥ 16 ቡድኖች ለወርቅ ሜዳሊያ ይወዳደራሉ። የተለመዱ ተጠባቂ ጨዋታዎች በቅድመ ውድድር ተወዳጆች ነበሩ። ፈረንሣይ ፣ ስፔን እና ጀርመንን ጨምሮ ከአውሮፓ የመጡ ትላልቅ ቡድኖች እንዲሁም እንደ አርጀንቲና እና ብራዚል ያሉ የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ቲታኖች ውድድር ገና ከመጀመራቸው በፊት እንደ ተወዳጅ ውድድር ይቆጠሩ ነበር ። ይህ እንዳለ ሆኖ ፣ አንዳንድ ቡድኖች ያልተጠበቁ ውጤቶች ካጋጠማቸው በኋላ ችግር ውስጥ ገብተዋል ። በተለይም ሜክሲኮ የወቅቱ የዓለም ሻምፒዮና ፈረንሣይን በውድድሩ የመጀመሪያ ጨዋታቸው  4-1 በሆነ ሰፊ ልዩነት ማሸነፋቸው ነው ።

ውድድሩ በ 22/07/21 ፣ በ 25/07/21 እና በ 28/07/21 በሚደረግ የዙር ደረጃ ጨዋታዎች ተጀምሯል።  በዚህ ደረጃ እያንዳንዱ ቡድን በምድባቸው ውስጥ እያንዳንዱን ቡድን ይጫወታሉ።  ቡድኖች ለማሸነፍ 3 ነጥቦችን ፣ 1 ነጥብ ለአቻ እና 0 ነጥብ ለሽንፈት ይሰበስባሉ።  ከእያንዳንዱ ምድብ ከፍተኛዎቹ ሁለት ቡድኖች ለሩብ ፍፃሜ ያልፋሉ።

መታየት ያለባቸው ተጫዋቾች

በተለምዶ እያንዳንዱ ቡድን ዕድሜያቸው ከ 23 ዓመት በታች የሆኑ የተጫዋቾች ቡድን መምረጥ አለበት ፣ 3 በዕድሜ የገፉ ተጫዋቾችም መካተት ይችላሉ።  በዚህ ዓመት ግን በኮቪድ እና በአንድ ዓመት መዘግየት ምክንያት በዚህ ዓመት ከ 24 ዓመት በታች ያሉ ተጫዋቾች አብዛኞቹን ቡድኖችን እንዲይዙ ደንቦቹ ተለውጠዋል።  ይህ ለአለም ዋንጫ በተመረጡት ቡድኖች ውስጥ የማይገቡትን ወጣት ተጫዋቾችን ለመመልከት የበለጠ ዕድል እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።  በትኩረት መከታተል ካለብን ወጣት ተስፈኞች ውስጥ ሦስቱ እነዚህ ናቸው ።

  • አንቶኒዮ

የ 21 አመቱ ብራዚላዊ የክንፍ ተጫዋች አሁን የአያክስ አምስተርዳም ሪከርድ ፈራሚ ነው። ልዩ በሆነ እና በሚማርክ ስልት የሚጫወት ሲሆን በብራዚል እግር ኳስ ውስጥ ‹ቀጣዩ ትልቅ ነገር› ተብሎ እየተመሰከረለት ነው። ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ወደ ኤሪዲቪሲ ከተዘዋወረ በኋላ ለኔዘርላንዱ ክለብ ብዙ ግቦችን ሲያስቆጥር ብዙ ለጎል እሚሆኑ ኳሶችም አመቻችቶ አቀብሏል ። ሆኖም ፣ በአያክስ የሊጉ መጨረሻ ጨዋራዎች ላይ ትንሽ የብቃት መውረድ ቢታይበትም ፣ ወደ ቀድሞ ብቃቱ ተመልሶ በአጃክስ የመጀመርያው የውድድር ዘመን ያሳየው ብቃት ሲደግም ማየት አስደሳች ይሆናል ።

thesun.com
  • ኢንዞ ላ ፌ

የ 21 ዓመቱ ላ ፈይ በአሁኑ ጊዜ በፈረንሣይ ሎሪየን ውስጥ የሚጫወት ተወዳጅ ወጣት ፈረንሳዊ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ነው።  ረዥም የሚባል ተጫዋች አይደለም ነገር ግን አጠር ያለ ቁመቱን ተጠቅሞ ከተቃዋሚዎች ጥፋቶችን ለማግኘት ይሞክራል።  ጠመዝማዛ ሩጫ እንቅስቃሴ ማድረግ ላይ አይታማም እናም የቅርብ ኳስ ቁጥጥሩ እንከን የለሽ ነው።

 ሆኖም በፈረንሣይ የተጫዋች ሀብት ብዛት ምክንያት እናም ይህ ውድድር የወጣት ውድድር በመሆኑ እሱ ሲጫወት ለማየት ካሉ ጥቂት ዕድሎች አንዱ ሊሆን ይችላል።

https://fclweb.fr/
  • ጋብሪኤል ማርቲኔሊ

ሌላ ብራዚላዊው የ21 ዓመት ግራ ክንፍ ተጫዋች ማርቲኔሊ ልክ እንደ ቡካዮ ሳካ ለአርሴናል ይጫወታል ፣ እናም በክለቡ ለምርጥ ታዳጊ ተጫዋች ይወዳደራሉ ። እንደ አለመታደል ሆኖ ባለፈው ዓመት እሱን ብዙ ግዜ ሜዳ ውስጥ አላየውም። የክንፍ አጥቂው በኮረና ወቅት (ሎክ ዳውን) የቀዶ ጥገና አድርጓል እና አርሴናል እስካሁን ድረስ ከዋናው ቡድን ጋር በመደበኛነት ለማሰለፍ የማይፈልግ ይመስላል። ተስፋ እናደርጋለን ፣ የዚህ ዓመት ኦሎምፒክ ለተመልካቾች (ምናልባትም ከቤት ቢሆንም) ድንቅ የእግር ኳስ ተሰጥኦ እና ችሎታ በተግባር እና በጥሩ ሁኔታ ለማየት እድል ይሰጣቸዋል።

arsenal.com

የወርቅ ሜዳልያ ማን ያሸንፋል ?

በአሁን ስአት ስፔኖች የወርቅ ሜዳሊያውን ለመውሰድ ተጠባቂ ቡድን ናቸው።  ስፔንን በውድድሩ ሌሎች አራት ታላላቅ ስም ያላቸው ቡድኖች ይከተሏታል እነዚህም ብራዚል ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን እና አርጀንቲና ናቸው።  በቅርቡ በዩሮ የተጫወቱ 6 ተጫዋቾች ስላሏቸው ስፔኖች የተሻለ እድል አላቸው።

ሊያስገርሙን የሚችሉ ቡድኖች ?

ሜክሲኮ በውድድሩ መጀመሪያ ላይ አልተጠበቀችም ነበር ፣ ግን ፈረንሳይን 4-1 ካሸነፈች በኋላ በዚያ ቡድን ውስጥ ያለው የራስ መተማመን ከፍተኛ መሆን አለበት።

as.com

ሜክሲኮ አሁን ከምድባቸው ማለፍ ከቻሉ ፣ አዝማሚያውም እንደዛ ነው ቢያንስ ቢያንስ ወደ ግማሽ ፍፃሜው የመድረስ ዕድል ይኖራቸዋል።  ሌላ ሊሆን የሚችል ያልተጠበቀ ቡድን አይቮሪ ኮስት ነው።  በኤሲ ሚላን ኮከብ ፍራንክ ኬሴ እና በኃይለኛ የጨዋታ ዘይቤያቸው ተመርተው ፣ ከአንዳንድ የላቀ ችሎታ ጋር ተዳምሮ ማንንም ለማስጨነቅ በቂ ሊሆን ይችላል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football