Connect with us
Express news


Football

ብሬንትፎርድ እግር ኳስ ቡድን ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን እና የፕሪሚየር ሊግ ዕድሎቻቸው

Brentford FC, Leeds United and Brighton and Hove Albion and their Premier League Chances
https://www.90min.com/

በ 2015-16 የውድድር ዘመን ሌስተር ሲቲ እንዳደረጉት ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ ትልልቅ ቡድኖችን የሚገዳደር ይኖር ይሆን?  ወይም ምናልባት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑት የወራጅነት እጣ ይደርሳቸው ይሆን ።

ብሬንትፎርድ እግር ኳስ ቡድን

ብሬንትፎርድ በፕሪሚየር ሊጉ የ 2021/22 ተሳትፎ ከ 1947 የውድድር ዘመን በኋላ በእንግሊዝ እግር ኳስ ከፍተኛ ደረጃ የመጀመሪያቸው ይሆናል። ትናንት ማንቸስተር ዩናይትድን በቅድመ-ውድድር የወዳጅነት ጨዋታ በኦልድትራፎርድ ገጥመው 2-2 አቻ ተለያይተዋል።  በብሬንትፎርድ ኮሚኒቲ ስታዲየም ፣ በአንጻራዊ ሁኔታ ኃይለኛ ቡድን ከሆነው አርሰናል ጋር የውድድር ዓመቱ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ የሚገናኙ ይሆናል ።  ያ ጨዋታ ለአዲሱ ብሬንትፎርድ ከባድ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም ፣ ነገር ግን በቀጣይ ጨዋታዎች ከክሪስታል ፓላስ ፣ ከአስቶን ቪላ ፣ ከብራይተን እና ከወልቭስ ጋር የተወሰኑ ነጥቦችን የመሰብሰብ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል።  ብዙውን ጊዜ ፣ በ ኢፒኤል ውስጥ ተስፋ አስቆራጭ በሚመስል ሁኔታ የሚደራረቡባቸው ከባድ ጨዋታዎች የላቸውም።  ሆኖም ከክሪስታል ፓላስ እና መሰሎቻቸውን ከገጠሙ በኋላ ማንችስተር ሲቲን በ 6 ሳምንታት ውስጥ ሁለት ጊዜ እና በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሊቨርፑልን መግጠም አለባቸው። በእነዚህ ጨዋታዎች ውስጥ ሊያገኟቸው የሚችሏቸው ነጥቦች ካሉ ፣ በውድድር አመቱ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ሊያሳድሩላቸው ይችላሉ።

brentfordfc.com

መታየት ያለባቸው ተጫዋቾች

ኢቫን ቱኒ የብሬንትፎርድ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው።  ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 33 ጊዜ ኳስን ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን የየተለያዩ ቡድኖችም ፍላጎት እየሳበ ይመስላል።  ብሬንትፎርድ በበኩላቸው በበጋው ወቅት የዝውውር መስኮት እንደማይሸጥ አጥብቀው ተናግረዋል። ምናልባት ብሬንትፎርድ እምቢ ማለት የሚከብድ ገንዘብ ቀርቦላቸው እሱን በሆነ መንገድ ካጡት ፣ ክለቡ ወደ ሌሎች ክለቦች በሄዱ ተጫዋቾች የሚፈጠሩትን ክፍተቶች ለመሙላት ድንቅ ፊርማዎችን በማድረግ ጥሩ ሪከርድ አለው።

ታሪክ ፎሱ በብሬንትፎርድ ቡድን ውስጥ መመልከት ያለብን ሌላ ተጫዋች ነው።  የብሬንትፎርድ አካዳሚ ያፈራው ተጫዋች ነው።  ፈጣን እግር ያለው እና ኳስ መምታት የሚወድ የግራ ክንፍ ተጫዋች ነው።  ባሳለፍነው የውድድር ዘመን 4 ግቦችን ሲያስቆጥር 4 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።  በዚህ ሂደት ውስጥ ለዋናው የጋና ብሔራዊ ቡድን ጥሪ አግኝቷል።

ሊድስ ዩናይትድ

ሊድስ ዩናይትድ ባለፈው የውድድር ዘመን በሻምፒዮንሺፑ የደረጃ አናት ላይ ሆኖ አጠናቋል ፣ ስለዚህ ቢያንስ አብሯቸው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደጉ ቡድኖች የተሻለ የራስ መተማመን እንደሚኖራቸው ግልጽ ነው።  እንዲሁም በማርኮ ቢኤልሳ እየተመሩም ጥሩ የኳስ ፍሰት ያሳያሉ።  በቶተንሃም ሆትስፐር ውስጥ ምንም ዓይነት ዋንጫ ባያሸንፍም ፣ የአርጀንቲናዉ ሞሪሺዮ ፖቼቲኖ በተመሳሳይ መንገድ በመጫወት የተወሰነ ስኬት አግኝቷል ፣ ሆኖም ግን ፖቼቲኖ የተሻለ ተጫዋቾች ነበሩት።  በአሁኑ ሰአት ሊድስ ዩናይትድ ባልተረጋገጠ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት።  በደጋፊዎቹ መካከል ብዙ ጉግት ይታያል።  የጭንቀት ስሜትም አላቸው ፣ ግን ቡድኑ ነጩን መስመር ሲያቋርጡ እና ቢኤልሳ በትንሽ ሰማያዊ አከባቢው ውስጥ ሆኖ በሚያሰጣቸው ታክቲኮች ቀጣይ ምን ሊከሰት እንደሚችል መተንበይ አይቻልም።  ከሼፊልድ ዩናይትድ ጋር ይስተካከላሉ ወይስ በኖርዊቾች ላይ የተከሰተው በሊድስ ዩናይትድ ላይ የመከሰት ትልቅ እድል አለው?

ft.com

መታየት ያለባቸው ተጫዋቾች

ሊድስ በ 27 ሚሊዮን ፓውንድ የመጀመሪያ ክፍያ ሮድሪጎን ከቫሌንሲያ በማስፈረም የዝውውር ሪከርዳቸውን ሰበረዋል።  ይህ በ 2000 ሪዮ ፈርዲናንድ ከዌስትሃም ለማስፈረም የከፈሉትን 20 ሚሊዮን የበለጠ ነው። አሁን በክለቡ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛው ተከፋይ ተጫዋች ሆኗል።  አጥቂው/ክንፉ ያንን ኢንቨስትመንት በተቻለ ፍጥነት በችሎታው አማካኝነት ለመካስ ይፈልጋል ፣ አለበለዚያ እንደ አብዛኞቹ ተጫዋቾች የዋጋው ብዛት የአንገት መልህቅ ሊሆነው ይችላል።

ለሊድስ ሌላ ተስፈኛ ወጣት ተጫዋች ሳም ግሪንዉድ ነው።  የ 18 አመቱ ወጣት ከአርሰናል የፈረመ አጥቂ ነው።  የሰንደርላንድ እግር ኳስ ቡድን የወጣቶች አካዳሚ ውጤት ሲሆን የኤሲ ሚላን እና የማንቸስተር ዩናይትድ እስካውቶች እየተከታተሉት ይገኛሉ።  ትልቅ የወደፊት እድል ሊኖረው ይችላል ፣ የመሰለፍ ዕድል ካገኘ ለሊድስ ዩናይትድ ብቃቱን ማሳየት አለበት።

ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን

ብራይተን ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ በመራራ ተቀናቃኞቻቸው ክሪስታል ፓላስን ገጥመው በጨዋታው 23 የግብ ሙከራ ቢያስመዘግቡም ሽንፈት ገጥሟቸው ወደ መውረድ የሚያቀኑ ይመስል ነበር።  ከማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ 11 ግቦችን በሜዳቸው ቢያስተናግዱም ፣ በ ኮቪድ ወቅት በአርሴናል ላይ ያገኙት የሜዳቸው ድል ፣ጥሩ አበረታች ነበር ። የብራይተን ተከላካዮች ዘንድሮ ጠንካራ ቢሆኑም ዋናው ችግራቸው ግብ ማስቆጠር ይሆናል። አሰልጣኝ ግራሃም ፖተር ምናልባት የጀርባ መስመሩን አጥብቆ ለማቆየት ይፈልግ ይሆናል እና በመልሶ ማጥቃት ወይም ከቆሙ ኳሶች ላይ ግቦችን ለማግኘት ይሞክራል። በሊጉ ውስጥ በጣም ማራኪ ወይም አጥቅቶ መጫወት አስፈላጊ አይመስልም ፣ ዋናው ነገር ነጥቦችን ማግኘት ነው ፣ ጥሩ አጥቂዎች ለእንደ ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን ላሉት ክለቦች በጣም ውድ ናቸው።

https://www.brightonandhovealbion.com/

መታየት ያለባቸው ተጫዋቾች

የሚያስገርመው ነገር አብዛኛዎቹ ጥሩ አቋም የሚያሳዩ ተጫዋቾች መከላከል ክፍል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ይህ የተከላካይ መስመር በሉዊስ ደንክ የሚመራ ሲሆን ማት ራያን ጥሩ ግብ ጠባቂ ይመስላል ፣ ግን በእውነቱ አሁን መመልከት ያለብን ወደ በ4 ሚሊዮን ፓውንድ ከቼልሲ የፈረመው ታሪክ ላምፓቴይ ነው። የ 20 አመቱ ወጣት በቀኝ በኩል ከፊቱ ለሚገኙት አጥቂዎች ጥሩ እገዛ የሚያደርግ ይሆናል።

በአጥቂ ክፍል ውስጥ ኒል ማፓይ አለ። አጥቂው ከተቀናቃኛቸው ብሬንትፎርድ ባለፈው የውድድር ዘመን ነው የተቀላቀለው። ለብራይተን 10 ግቦችን ያስቆጥረ ሲሆን አሁንም እንደሚያሻሽል እና ብዙ ተጨማሪ ግቦች ማስቆጠር እንደሚችል ምልክቶች አሉ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football