Connect with us
Express news


European Leagues

የቼክ ሪፐብሊክ የመጀመሪያ ሊግ (ፎርቱና ሊጋ); ቅድመ -እይታ

The Czech Republic First League (Fortuna Liga) Preview
https://sparta.cz/

በዚህ ዓመት አዲስ ሻምፒዮን ይኖራል ወይስ ስላቪያ ዋንጫውን ያስጠብቃሉ?  እንዲሁም ፣ የመውረድ እድል ያለው ማን ነው?

የቼክ አንደኛ ሊግ ፣ ፎርቱና ሊጋ በመባልም የሚታወቀው በ 1993 ከተቋቋመ በኋላ አሁን በ 29 ኛው ዓመቱ ነው። ስለዚህ ልንጠብቃቸው የሚገቡ ቡድኖች እነማን ናቸው እና ወደ ታችኛው ሊግ የመውረድ እድል የሚገጥማቸውስ?

ሊጉን ማን ሊያሸንፍ ይችላል ?

ስላቪያ ፕራግ

https://www.slavia.cz/

በአስደናቂ እና ምናልባትም በጣም በሚገርም ጋዜጣዊ መግለጫ ስላቪያ አዳዲስ ተጫዋቾችን እና አዲስ ማልያ አስተዋውቋል። ይህ ከመጠን በላይ ነበር ፣ የሽልማት ሥነ-ሥርዓትን የሚመስል ነገር ነበረው።  ይህ ተገቢ ነበር ፣ ምክንያቱም ቀደም ሲል በተከናወነው በእውነተኛ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ስላቪያ ለ 3 ኛው ተከታታይ ዓመት ለጄንድሪክ ትሪፕሶቭስኪ  ምርጥ አሰልጣኝ ጨምሮ ብዙ የግል እና የቡድን ሽልማቶችን አግኝተዋል ።  ስላቭያ ዋንጫውን አስጠብቆ አያቆይም ብሎ መወራረድ መድፋር ነው እሚሆነው።

ስፓርታ ፕራግ

news.nike.com

ስፓርታ ፕራግ ባለፈው ዓመት ከስላቪያ ስር 2 ኛ ሆነው አጠናቀዋል ። በዚህ ዓመት አንድ ከፍ ብለው ግዙፍ ተፎካካሪዎቻቸውን ለመገልበጥ ተስፋ አድርገዋል።  ቫክላቭ ኮታል በኮከብ ተጫዋቻቸው እና በካፒቴኑ ቦረክ ዶካል አማካይነት በመካከለኛው ሜዳ በሚገባ የተደራጀ አስደሳች ቡድን ሰብስቧል።

ቪክቶሪያ ፕሌዘን

betarena.com

ቪክቶሪያ ፕልዘን የስላቪያን የበላይነት ለማስቆም ያለመ ሌላ ቡድን ነው።  ክለቡ ባለፈው ዓመት ውድድር 5 ኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ቢሆንም ግን በቼክ አንደኛ ሊግ ውስጥ ጥሩ ታሪክ አላቸው።  ሊጉን በ 2010-11 ፣ 2012-13 ፣ 2014-15 ፣ 2016-17 እና 2017-18 አሸንፈዋል። በ 2019-2020 ሁለተኛ ሆነውም ጨርሰዋል ።  ዋና አሰልጣኝ ሚካል ቢልክ የክብር ቀናትን መመለስ እና በሂደቱም ስላቪያን ቅር ሊያሰኟቸው ይፈልጋሉ።

ማን ሊወርድ ይችላል?

በርካታ ቡድኖች በ 2021-2022 የውድድር ዘመን ሊወርዱ የሚችሉ ይመስላሉ።  ቴፕሊስ ፣ ዚሊን እና ኤስ.ኬ ዲናሞ ባለፈው አመት ከመውረድ ለትንሽ ነው የተረፉት እና በዚህ ዓመት ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ።  ራዴክ ክራሎቭ እንዲሁ በከፍተኛ ሊግ ውስጥ ለመቆየት መላመድ አለባቸው አዲስ ባደጉ ቡድኖች ላይ እንደምንመለከተው ችግሮች ሊገጥሙት ይችላል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in European Leagues