Connect with us
Express news


Football

ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል) ቅድመ -እይታ ; ወልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ፣ ዋትፎርድ እና ሳውዝሃምፕተን እግርኳስ ቡዱን

Premier League (EPL) Preview; Wolverhampton Wanderers, Watford and Southampton FC
https://sillyseason.com/

ትናንሽ ቡድኖች ተብለው እሚጠሩት ዘንድሮ ምን ማሳካት ይችላሉ ? ከወራጅ ቀጠና ይተርፋሉ ፣ ወይስ አንዳንዶቹ ያስደንቁናል ?

ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ

ዎልቭስ ይህንን የውድድር ዘመን የሚጀምሩት ከቀደሞቻቸው ሁለት አመታት በተመሳሳይ መንገድ ሲሆን ከሜዳቸው ውጭ ሌስተር ሲቲን በመግጠም ይሆናል ። ክለቡ ያለ አስደናቂው አሰልጣኝ ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶ መሪነት የመጀመሪያውን የውድድር ዘመኑን ይጫወታል ፡፡ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከሶስት ዓመታት ጥሩ የዘመቻ ቆይታ በኋላ ‘በጋራ ስምምነት’ ቡድኑን ለቀዋል ፡፡ ለምሳሌ በሞሊኔክስ የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ ቡድኑን ወደ ኢ.ፒ.ኤል እንዲያድግ አድርጓል ፣  በሁለተኛ እና በሦስተኛው የውድድር ዘመኑ ክለቡን ከፍተኛ ፉክክር በሚደረግበት ሊግ 7 ኛ ደረጃ እንዲይዝ አድርጓል፡፡ ያንን ስኬት ለመድገም ወይም ለማሻሻል የተመረጠው አሰልጣኝ የኑኖ የአገሩ ልጅ የሆነው ብሩኖ ሌጅ ነው ፡፡ ሌጅ ቤንፊካን ወደ ፖርቱጋል ዋንጫ በማድረስ ለራሱ ጥሩ ስም አትርፏል ፡፡ የቀድሞ ቡድኖቹ አጥቅቶ መጫወት ያስደስታቸው ነብር ይህ ደግሞ ለዎልቭሶች ምቹ ነው፡፡ ኑኖ በጀመረው መሠረት ላይ ለመገንባት ተስፋ ያደርጋል ፡፡

premierleague.com

መመልከት ያሉብን ተጫዋቾች

ከዎልቭሶች መመልከት ካሉብን ተጨዋች አንዱ ራውል ሂሜኔዝ ነው ፡፡ ሂሜኔዝ ለተከታታይ ሁለት ሲዝኖች በጎል ሰንጠረዥ ላይ ከፍተኛ ደረጃ ይዞ ነበር ፡፡ ባለፈው ዓመት ግን የ 9 ቁጥሩ ተጫዋች ብቃት በተወሰነ ደረጃ ቀንሷል ፡፡ በ2019 – 20 ሲዝን በ38 ጨዋታዎች 19 ግቦችን ወዳስቆጠረበትን አቋሙ እንዲመለስ ተስፋ አድርጓል ።

በስታቲስቲክስ መሠረት የዎልቭስ ምርጥ ተጫዋች ፔድሮ ኔቶ ነው ፡፡ በአሁኑ ወቅትም በዎልቭስ ምርጥ የመሃል ሜዳ ተጫዋች ነው ፡፡ በድምሩ 6 ጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል አሁን በአውሮፓ ደረጃ ላይ 234 ኛው ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተቀምጧል ፡፡ ኳስ ለማቀበል ጥሩ አይን ያለው ተጫዋች ሲሆን የመሃል ሜዳው እንቅስቃሴውም አሪፍ ለማድረግ ተስፋ ሰንቀዋል ።

ዋትፎርድ

theguardian.com

ዋትፎርዶች ከአንድ አመት የሻምፒዮንሺፕ ቆይታ በኋላ ወደ ኢፒኤል ተመልሰዋል ።  በፈረንጆቹ ነሐሴ 14 አስቶን ቪላን በሜዳቸው በማስተናገድ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ህይወታቸውን እንደገና ይጀምራሉ ፡፡ አምና በታችኛው ሊግ ሁለተኛ ሁኖ ላጠናቀቀው ኖርዊች ምስጋና ይድረሰው እና ቀንደኞቹ (ዎልቭሶች) አልፈዋል ። በታችኛው ሊግ ውስጥ አውሎ ነፋሳዊ ዘመቻ እያጣጣሙ 91 ነጥቦችን መሰብሰብ ችለዋል ። አሰልጣኝ ሲስኮ ሙኖዝ በዚህ ክረምት ተጫዋቾች በማስፈረም ተጠምደዋል ። እስካሁን ዳኒ ሮዝ ፣ ጆሽ ኪንግ እና አሽሊ ፍሌቸር ወደ ቪካርጄ ሮድ አምጥተዋል ። እስካሁን ደግሞ አስፈርሞ አልጨረሰም የሚል ሃሜት አለ ። ሆኖም በ ኢፒኤል የመቆየት ችሎታ ያለው ቡድን መገንባት ይችላል?

መመልከት ያሉብን ተጫዋቾች

ባለፈው የውድድር አመት ኢስማኢላ ሳር የዋትፎርድ ምርጥ አጥቂ ተጫዋች ነበር ፡፡ በመጨረሻ የኢፒኤል ተሳትፋቸው 5 ጎሎችን ሲያስቆጥር ሰባት ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አቀብለዋል ፡፡ በ 6 ሚሊዮን ፓውንድ የዋትፎርድ በጣም ውዱ ተጫዋች ነው ፡፡ የሳር የሜዳ ላይ ብቃት በደማቅ ጥበብ የሚለዩ እና ሰአታቸውን የጠበቁ ናቸው ፡፡ ሁለቱም ሳር እና ሙኖዝ ከባለፈው ሲዝን የተሻለ ነገር ይጠብቃሉ ።

ዋትፎርድ በተመጣጣኝ ሁኔታ ቢያንስ ጠንካራ እሚባል ተከላካይ ያለው ሲሆን ከኋላ የምንመለከተው ተጫዋች የስፔኑ ኪኮ ፌሜኒያ ነው ፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን 37 ጨዋታዎችን ያደረገው ፌሜኒያ በቀኝ መስመር ተከላካይ ስፍራ ላይ ለዋትፎርድ ቦታውን ያጠናከረ ይመስላል ፡፡ ወደፊትም በመሄድም ውጤታማ ነበር ፡፡ በዋትፎርድ ቡድን ውስጥ 4 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ሁለተኛ ደረጃ መያዝ ችሎ ነበር ።

ሳውዝሃፕተን እግርኳስ ቡዱን

https://www.southamptonfc.com/

በዚህ ክፍል ከተጠቀሱት ሶስቱ ክለቦች ውስጥ ሳውዝአምፕተኖች ምናልባትም እጅግ በጣም የሚጠበቁ ናቸው ፡፡ ቢያንስ በተለምዶ ሳውዝሃምፕተኖች በኢ.ፒ.ኤል. ቆይተዋል ። ሆኖም በቅርቡ የሜዳ ላይ ብቃታቸው ብዙ ነገር እንደሚያስፈልጋቸው አሳይተዋል ፣ ባለፈው የውድድር ዘመን በኢፒኤል 15ኛ ደረጃ ብቻ ነው መያዝ የሻሉት። ሳውዝሃምፕተኖች በ 43 ነጥብ ቢያጠናቅቁም ብሊጉ ውስጥ ካሉ 10 ምርጥ ግብ አስቆጣሪ ብዱኖች አንዱ ለመሆን ችለዋል ፡፡ ሆኖም የእነሱ የመከላከል ድክመት ወደ አንዳንድ አሳፋሪ ውጤቶች አስከትላቸዋል ፡፡ በኢ.ፒ.ኤል. ጨዋታ 9 ግቦችን ያስተናገደ ብቸኛው ቡድን ሳውዛምፕተን ነው ፡፡ አሰልጣኝ ራልፍ ሀሰንሁንትል በእርግጠኝነት እንደዚህ የመሰለ ነገር እንደገና እንደማይከሰት ተስፋ ያደርጋሉ ፡፡

መመልከት ያሉብን ተጫዋቾች

ምንም እንኳን የመከላከል ጉዳዮች ቢኖሩም ፣ የመሀል ተከላካዩ ያኒክ ቬስትጋርድ በብዙዎች ዘንድ የሳውዝሃምፕተን ምርጥ ተጫዋች ነው ተብሎ ይታሰባል ፡፡ በቅርቡ በአውሮፓ ዋንጫ ጥሩ ብቃት ላሳዩት የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ይጫወታል ፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን አጠገቡ ያሉትን ተጫዋቾች በማወሃሀድ የመከላክል አቅማቸው ከፍ እንደሚያደርግ ተስፋ ተደርጓል ። በማጥቃት ቦታ ዳኒ ኢንግስ ልንመለከተው የሚገባው ተጫዋች ነው ፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን 12 ጎሎችን በማስቆጠር የሳውዝሃምፕተን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነበር ፡፡ በኢ.ኢ.ፒ. ውስጥ 65 ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በ 2021/22 የውድድር አመት ውስጥ የጎል ቁጥሩን እንደሚጨምር ተስፋ አድርጓል ፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football