Connect with us
Express news


Football

ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ቅድመ እይታ; ኖርዊች ሲቲ ፣ ክሪስታል ፓላስ እና በርንለይ እግር ኳስ ቡድን

Premier League Preview; Norwich City FC, Crystal Palace FC, and Burnley FC
sillyseason.com

ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ኖርዊች በቀጥታ ወደ ሻምፒዮንሺፕ ይመለሳል? ክሪስታል ፓላሶች ከአምናው የ14ኛ ደረጃቸው ያሻሽላሉ እና ደግሞ በርንለዮች እንደገና ወደ ሻምፒዮንሺፕ እንዳይመለሱ ተአምር መስራት ያስፈልጋቸዋል ?

ኖርዊች ሲቲ እግርኳስ ቡድን

canaries.co.uk

ኖርዊቾች በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ሻምፒዮንሺፕ ከወረዱ በኋላ ፣  ሊጉን በ97 ነጥብ ማሸነፍ ችለዋል ፣ ይህ ደግሞ በሻምፒዮንሺፕ ታሪክ ከፍተኛ ነጥብ ሆኖ ተመዝግቧል ። ይህ እንዳለ ሆኖ ቡድኑ የሊግ ስኬታማነት እና ቢኢፒኤል የሚመጣ ገንዘብ እና ክብር ላይ ትኩረት በማድረጋቸው የዋንጫ አቋማቸው ወርዷል ። ምናልባት ዘንድሮ ካናሪዎቹ ለክብር ትልቅ ተስፋ አድርገዋል ፣ ግን ዋንጫ የማንሳት ጉዞም ሊሆን ይችላል። አሰልጣኝ ዳንኤል ፋርክ በዋናነት በ ኢፒኤል ውስጥ ለመቆየት በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ምናልባትም በአንዱ የዋንጫ ውድድር ውስጥ አንድ ነገር ለማሳካት በጥበብ መስራት ይኖርብርታል  ።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

ቲሞ ፑኪ

ፊንላንዳዊው አጥቂ ቲሞ ፑኪ ባለፈው የውድድር ዘመን በሻምፒዮሺፕ ምርጥ አቋም አሳይቷል። ለምሳሌ ፣ በኤፕሪል 6 ቀን 2021 ሃደርስፊልድን 7-0 በበሆነ ሰፊ ልዩነት ሲያሸንፉ የመጀመሪያውን ሀትሪክ ሰርቷል። ይህን በማድረግ የውድድር ዘመኑን 25 ኛ ግቡን አስመዝግቧል። ብዙ ምርጥ አጥቂዎች ከፕሪሚየር ሊጉ ታላላቅ ተጫዋቾች ጋር ለመመሳሰል ሞክረዋል። ፑኪ አሁንም በ ኢፒኤል ጎሎችን ያስቆጥራል ወይስ ልክ ከሱ በፊት እንደነበሩት ተጫዋቾች ይቸገራል ?

ቶድ ካንትዌል:

የ 23 ዓመቱ ታዳጊ ኮከብ እና የአከባቢው የኖርፎልክ ልጅ ፣ ካንትዌል በሻምፒዮንሺፑ ውስጥ በእውነቱ ከፍተኛ ብቃት አሳይቷል ። ከመሃል ሜዳ በመሮጥ ፣ በተረጋጋ ሁኔታ ጎሎችን በመጨረስ እና በማታለል የአካዳሚው ፍሬ ለሊጉ ተስማሚ ሊሆን ይችላል። የካንትዌል እና ፑኪ ጥምረት በጣም ቁልፍ ነው እና ባለፈው የውድድር ዘመን ጥሩ ልምዶች ነበሩት ። አሁንም ጥያቄው ለፕሪሚየር ሊጉ ፈተናዎች አስፈላጊውን መሻሻል ማድረግ ይችላል?

ክሪስታል ፓላስ እግር ኳስ ቡድን

footballticket.net

ክሪስታል ፓላስ ባለፈው የኢፒኤል ውድድር ዘመን ተሳፋ አስቆራጭ ጉዞ ነበር ያደረጉት ። አሰልጣኝ ሮይ ሆድሰን ንስሮችን በ ኢፒኤል 14 ኛ ደረጃ ብቻ ነበር ማሳካት የቻሉት ። ከዚያ በኋላ ፓላስ እና ሆድሰን ተለያዩ እና ትልቁ ዜና አዲስ የተመረጠው አሰልጣኝ የአርሰናሉ አንጋፋ ተጫዋች የነበረው ፓርቲክ ቬራ መሆኑ ነው ። በአንፃራዊ ሁኔታ ልምድ የሌለው አሰልጣኝ ነው። የእሱ ብቸኛ የትልቁ ሚና በፈረንሣይ ኒስ በ2018-2020 ነበር። ቪራ ከዚህ የተጫዋቾች ቡድን ጋር በአርሴናል ሜዳ ላይ እንደነበረ ዓይነት መሪ ሊሆን ይችላል ወይስ የአሰልጣኝ ሚና ስለ ፈረንሳዊው ብዙ ነገሮችን ያረጋግጥልናል ? ብዙ ተጫዋቾች ባለፈው የውድድር ዘመን ክለቡን ለቀው የወጡ ሲሆን ቬራ በዝውውር መስኮት ውስጥ ስራ የበዛበት ሰው ነበር። ያ በእርግጥ የማሰልጠን ችሎታውን ማሳያ ይሆናል።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

ዊልፍሬድ ዛሃ

ዛሃ ከፓላሶች ጋር ለብዙ የውድድር ዘመናት የቆየ ችሎታ ያለው ፣ ፈጣን እና ተንኮለኛ አጥቂ ነው። ባለፈው የውድድር ዘመን 11 ጊዜ ኳስን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 2 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቷል። አይቮሪኮስታዊው ያንን ቁጥር ለማሻሻል እና ንስሮቹ ባለፈው አመት ከሊጉ ከ14 ኛው ደረጃ የተሻለ ነገር እንዲያሳኩ ለመርዳት እንደሚጥር ጥርጥር የለውም።

ኤብረቺ ኢዜ

ኢዜ በፓላስ አጥቂ መስመር ለዛሃ አስተማማኝ እና እድል ፈጣሪ አጋር ለመሆን እንደሚፈልግ ጥርጥር የሌለው አጥቂ አማካይ ነው።  እንደ አለመታደል ሆኖ በግንቦት 2021 የጉልበት ጉዳት እንደደረሰበት እና ለበርካታ ወሮች ከጨዋታ ውጭ እንደሚሆን ሪፖርት ተደርጎ ነበር።  ሆኖም ፣ ያ የህክምና ትንበያው ትክክለኛ ከሆነ ፣ አስደሳቹ አማካይ በዚህ ዓመት ኢ.ፒ.ኤል. ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ብዙ ጊዜ አለው።

በርንለይ እግር ኳስ ቡድን

insidermedia.com

በርንሌይ ብራይተን በተርፍ ሞር በማስተናገድ የ ኢፒኤል ጨዋታቸውን ይጀምራሉ። ቀጣዩ ጨዋታ ከሜዳቸው ውጪ ከየርገን ክሎፑ ሊቨርፑል ሲሆን በጣም አስፈሪ ጨዋታ ነው። ሆኖም ትንሹ በርንሌይ ቀልብን ይስባል ምክንያቱም እነዚህ ሁለቱ ቡድኖች ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት ጨዋታ በርንሌይ የሊቨርፑልን በሜዳቸው ለተከታታይ 68 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ እንዲቋጭ አድርጓል ። አሰልጣኝ ሾን ዳይስ እንደዚህ ያሉ ተጨማሪ ውጤቶችን እና ከሁሉም በላይ ደግሞ በሊጉ ውስጥ ካሉ የቅርብ ተቀናቃኞች ከፍተኛውን የነጥብ መጠን ለመውሰድ ይፈልጋል።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

ክሪስ ዉድ

ይህን አጥቂ ተጫዋች ይመልከቱ ።  በ 2020-21 ወቅት ፣ 9 ቁጥር የለበሰው የኒውዚላንድ ዜጋ 33 ጨዋታዎችን አድርጎ 12 ግቦችን አስቆጥሯል።  ሆኖም በርንሌይ በዚህ አመት የተሻለ የውድድር ዘመንን የሚያሳልፍ ከሆነ ይህ ተጫዋች በዚህ ዓመት ይበልጥ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚችል ግልጽ ነው ።

ድዋይት ማክኔይል

ድዋይት ማክኔል በ 21 ዓመቱ ተሰጥዎ ያለው ተስፋ ሰጪ ወጣት ነው። በመሀል ሜዳ እና ብዙውን ጊዜ በክንፍ ላይ ይጫወታል።  ተጫዋቹ ለበርንሌ በ96 ጨዋታዎችን የተሰለፈ ሲሆን ይህም ሾን ዳይስ በእሱ ላይ ብዙ እምነት እንዳለው ይጠቁማል።  ያ እንዳለ ሆኖ ግን በእነዚያ 96 ጨዋታዎች 7 ጊዜ ብቻ ኳስን ከመረብ አገናኝቶ 16 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football