Connect with us
Express news


Football

ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ቅድመ – እይታ ; ኒውካስትል እግርኳስ ቡድን ፣ ኤቨርተን እግርኳስ ቡድን እና አስቶን ቪላ እግርኳስ ቡድን

Premier League (EPL) Preview; Newcastle FC, Everton FC and Aston Villa FC
sportskeeda.com

ኤቨርተን ፣ አስቶንቪላ እና ኒውካስል ዩናይትድ ባለፈው የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ 10 ኛ ፣ 11 ኛ እና 12 ኛ ሆነው አጠናቀዋል። እነዚህ ክለቦች በዚህ ዓመት ከፍ ያለ ምኞቶች አሏቸው ፣ ወይስ ብቸኛ ዓላማቸው በደረጃ ሰንጠረዡ መካከል ላይ መሆን እና በኢ.ፒ.ኤል. መቀጠል ነው ?

ኒውካስትል ዩናይትድ እግርኳስ ቡድን

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን አስማተኞቹ በእርግጥ መከላከል ላይ ተቸግረው ነበር ። ኒውካስትሎች ከተሞከሩባቸው ሙከራዎች እስከ ተቆጠሩባቸው ግቦች ድረስ በታችኛው አራት ውስጥ ነበሩ ፣ የወረዱት ሸፊልድ ዩናይትድ እና ዌስትብሮምዊች አልቢዮን ነበሩ ያነሰ ጊዜ ግብ ሳይቆጠርባቸው የወጡት ። በአሰልጣኝ ስቲቭ ብሩስ ስር ከነበሩት መካከለኛ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ ፣ በቡድኑ ተከላካይ መስመር ላይ ለታየው ደካማነት በርካታ ጉልህ ምክንያቶች ነበሩ። ከነዚህ ምክንያቶች አንዱ የተጫዋቾች አለመገኘት ነበር። ሌላው ምክንያት የቀድሞው አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ ተጽእኖ ይመስላል። ቤኒቴዝ በስሩ ጥሩ የማጥቃት ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች እንደሌሉት አምኖ የበለጠ ተግባራዊ የማጥቃት ስልትን ይመርጥ ነበር። ብሩስም ይህንን ችግር ያውቃል ፣ ግን እሱ አሁንም ቡድኑን ወደ አጥቅቶ መጫወት መቅረፅ ይፈልጋል። ለኒውካስትሎች አስደሳች የውድድር ዘመን ሊሆን ይችላል!

lcfc.com

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

ጆንጆ ሼልቪ  ምን እንደሚያሳየን በጭራሽ አይታወቅም። አማካዩ ያለ ጥርጥር አሁን ባለው ቡድናቸው ውስጥ ምርጥ ኳስ አከፋፋይ ነው እና አስገራሚ እንቅስቃሴዎች ሊያሳይ ይችላል። ይህ እንዳለ ሆኖ ፣ በሜዳ ውስጥ በሚያሳያቸው ሞኝነት እና የአመጽ ባህሪ ትላልቅ ቡድኖች ሊያስፈርሙት ፍቃደኛ አልሆኑም ።

በሐምሌ 7 ቀን 2021 ጃኮብ መርፊ ከኒውካስል ጋር የኮንትራት ማራዘሚያ ውል ፈርሟል።  ኳስ መግፋት ፣ ከክንፍ ኳሶችን ይዞ ወደ መሃል መግባት እና ኳስ ማሻማት እሚወደው የ26 ዓመቱ ወጣት ሌላኛው ከሼልቪ ጎን ሆኖ የሚጫወት የመሃል ሜዳ ተጫዋች ነው። በዚህ ወቅት ለ ሼልቪ አስፈላጊ ሽፋን ሊሰጠው ይችላል።

ኤቨርተን እግርኳስ ቡድን

evertonfc.com

የቀድሞው የኒውካስል አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ አሁን የኤቨርተን አሰልጣኝ ሆነዋል። የቀድመው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሊቲ በአውሮፓ ውድድሮች እንሳተፋለን ቢሉም ቡድናቸው ኤቨርተን ባለፈው የውድድር ዘመን ማሳካት የቻለው ምርጥ አስር ብቻ ነው ። በ 2020/21 የውድድር ዘመን መጀመርያ አካባቢ በግብ የተሞላ ግዜን ብያሳልፉም አመቱ በሄደ ቁጥር የማጥቃት ጨዋታቸው ቀንሷል ፣ የተከላካይ ብቃታቸው ግን አልቀነሰም ነበር ።  ስለዚህ ቤኔቴዝ ከአንቸሎቲ የተቀበለው ጥሩ የመከላከል አቅም በመጠበቅ ምናልባትም በማሻሻል አጥቂ ተጫዋቾቹን ትላልቅ ነገሮችን እንዲያልሙ ለማነሳሳት ተስፋ አድርጓል።    

መመልከት ያለብን ተጫዋች

ኮሎምቢያዊው አማካይ ጄምስ ሮድሪጌዝ በየሆነ ጊዜ ከዓለም ታላላቅ የእግር ኳስ ተጫዋቾች አንዱ እንደሚሆን ተገምቷል። በሪያልድ ማድሪድ ከብዙ የተቀያሪ ወንበር ግዜያት በኋላ በኤቨርተን ጨዋታዎችን መጀመር ችለዋል ። ሆኖም እሱ ኤቨርተንን ለመልቀቅ እያሰበ መሆኑ በስፖርቱ ፕሬስ እየተዘገቡ ነው ። ሆኖም በቡድኑ የሚቆይ ከሆነ ወደ አውሮፓ እግርኳስ ውድደር የሚያደርጉትን ጉዞ ወሳኝ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

ሌላው መመልከት ያለበት ተጫዋች አጥቂው ዶሚኒክ ካልቨርት-ሌዊን ነው። የ 24 ዓመቱ ተጫዋች ባለፈው የውድድር ዘመን ከ 33 ጨዋታዎች 16 ጎሎችን አስቆጥሯል ፣ ስለዚህ ባለፈው የውድድር ዘመን ለኤቨርተን ሲጫወት ከ 50% በላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል። ካልቨርት-ሌዊን 186 ሴ.ሜ ቁመት ያለው ረዥም ሰው ነው ፣ ስለሆነም በጭንቅላት ብዙ ግቦችን አስቆጥሯል ።

standard.co.uk

አስቶን ቪላ እግር ኳስ ቡድን

ሐምሌ 26 ቀን 2021 ፣ ታዋቂው የቼልሲ ተጫዋች-አሰልጣኝ ጆን ቴሪ በክለቡ ከ 3 ዓመታት ቆይታ በኋላ አስቶንቪላን ለቀቀ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማለፍ ሲችሉ በሊጉ ቆይታቸውንም ማጠናከር ችለዋል ። ሆኖም ከ2018 ጀምሮ ለአሁኑ ዋና አሰልጣኝ ዲን ስሚዝ ረዳት አሰልጣኝ ብቻ ነበር። ስሚዝ ቡድኑን ማሻሻል እንደሚፈልግ አቋሙን ግልፅ አድርጓል። ያለፈው የውድድር ዘመን ለአስቶንቪላ በእርግጠኝነት የእድገት ጊዜ ነበር። ከአስደናቂው 10 ወራት የኢፒኤል ቆይታቸው በኋላ አሁን በሁሉም የሜዳው እንቅስቃሴዎች ተሻሽለዋል ። በ11 ኛ ደረጃ አስቶን ቪላ በጄራርድ ሃውልሊ መሪነት ከ 2010/11 በኋላ በኢፒኤል የውድድር ዘመን እጅግ የላቀውን ደረጃ አስመዝግቧል።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

ጃክ ግሪሊሽ ያለ ጥርጥር በአስቶንቪላ ዋናው ተጫዋች ነው። ስለዚህ የመጨረሻ ጨዋታቸው በሁለት ክፍሎች ሊከፈል ይችላል። ከግሪሊሽ ጋር እና ያለ ግሪሊሽ! የ 25 ዓመቱ ተጫዋች በየካቲት ወር የእግር ጉዳት ከደረሰበት በኋላ 12 ጨዋታዎችን አምልጦታል ፣ እና ዲን ስሚዝ ከዛ በኋላ እድል ሊቀናችቸው አልቻለም ፣ እሱ እስኪመለስ ድረስ ከባድ ወራት አሳልፈዋል ። እሱ በሌለበት ወቅት ቪላዎች ከ36 ነጥቦች ማግኘት የቻለው 12 ብቻ ሲሆን 13 ጎሎችም አስቆጥረዋል ።  በስታቲስቲክስ ሲገለጽ ፣ ግሬሊሽ ባለፈው የውድድር ዘመን በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች አስቶንቪላ በትክክል 50%ን ያክል አሸንፈዋል። እሱ ባልተሰለፈበት ጊዜ በትክክል 25%ን አሸንፈዋል። ጥያቄው አስቶን ቪላ እሱን ማቆየት ይችል ይሆን ወይስ ማንችስተር ሲቲ እምቢ ማለት የማይችሉትን ገንዘብ ያቀርብላቸዋል ?

ዲን ስሚዝ ኤሚሊያኖ ቡንዲያን በ 33 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈረም በግሬሊሽ ላይ የነበረውን ከፍተኛ ጥገኝነት ለመፍታት መርጧል ። የተከፈለው ክፍያ የክለቡ ሪከርድ ስለሆነ ተጫዋቹ ዋጋውን ለማሳየት ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረዋል። አርጀንቲናዊው ጨዋታ ፈጣሪ ጎል የማስቆጠር እምቅ ችሎታ አለው ፣ ሆኖም ግን የጎል እድል መፍጠር ችሎታው ይበልጥ አጓጊ ነው ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football