Connect with us
Express news


Football

ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ቅድመ እይታ ; ዌስትሃም ዩናይትድ እግር ኳስ ቡድን እና ሌስተር ሲቲ እግር ኳስ ቡድን

Premier League (EPL) Preview; West Ham United FC and Leicester City FC
whufc.com

ሁለቱም ክለቦች ባለፈው የውድድር ዘመን በጣም ስኬታማ ጊዜ አሳልፈዋል። ቢያንስ አንዳቸው በዚህ የውድድር ዘመን የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ማሳካት ይችላሉ?

ዌስትሃም ዩናይትድ እግር ኳስ ቡድን

ዌስትሃም የ 2020/21 ን የውድድር ዘመን በ 6 ኛ ደረጃ አጠናቋል። አመቱ ሲጠናቀቅ ከቻምፒዮንስ ሊግ ቦታ ላይ በ2 ነጥብ ብቻ ነበር የራቁት ። ከሌስተር 1 ነጥብ ብቻ እና በ 4 ኛ ደረጃ ላይ ከጨረሰው ቼልሲ በ 2 ነጥብ ርቀው ነው የጨረሱት።  ዌስትሃም በ 35 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የኘሪምየር ሊግ ነጥቦችን በመያዝ የ 2020/21 ን የውድድር ዘመን አጠናቋል።  ያንን በዚህ አመት መድገምም ከባድ ተግባር መሆኑን ይገነዘቡ ይሆናል።  ሆኖም መዶሻዎቹ በእርግጥ ለአውሮፓ ሊግ  አልፈዋል ።

https://www.football.london/

ነሐሴ 27 በእያንዳንዱ የዌስትሃም ደጋፊ የማይረሳ ቀን ነው። በሚቀጥለው ወር ዓርብ እለት ከሰዓት በኋላ የአውሮፓ ሊግ የምድብ-ደረጃ ዕጣ ድልድል ይደረጋል ፣ ደጋፊዎችም ከማን ጋር ሊደርሳቸው እንደሚችል በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ ።

ዌስትሃም በአውሮፓ ውስጥ  ለመጨረሻ ጊዜ የተጫወቱት በ1999 ሲሆን አሁን የተቋረጠው ኢንተርቶቶ በሃሪ ሬድካንብ እየተመሩ ዋንጫውን ችለው ነበር ። መዶሻዎቹ በስላቫን ብሊክ እየተመሩ 2015/16 እና 2016/17 እንዲሁም ካርሎስ ቴቨዝ እና ማሽራኖ ይጫወቱ በነበርበት የ2006/07 የማጣርያ ዙሮች ማሳካት ችለው ነበር ።

ሆኖም ባለፈው ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ዌስትሃምን ባነሳሳው ዴቪድ ሞዬስ ስር በምስራቅ ለንደን ጥሩ እንቅስቃሴ እና ተስፋ ታይተዋል ፣ አሁን ደግሞ ቡድኑ እንደ ናፖሊ ፣ ላዚዮ ፣ ሊዮን ካሉ እና ማርሴይ የመሳሰሉት ብዱኖችን ጋር በ2021/22 ዩኤኢ ለመጫወት ራሱን እያዘጋጀ ይገኛል ።

ከብዙ የፕሪሚየር ሊግ  የመካከለኛው እስከ ታችኛው ደረጃ ቆይታ በኋላ እና በአውሮፓ ውድድሮች የመሳተፍ ጉጉት ውጪ  ፣ በዚህ የውድድር ዘመን ከሞይስ ቡድን ምን እንጠብቃለን? ሞይስ አንዳንድ የተጫዋቾች ጉዳት እና ሌሎች መጥፎ አጋጣሚዎች በጥበብ ነበር ያለፋቸው ፣ ስለዚህ በዚህ የውድድር ዘመን ጥሩ ብቃት እንደሚያሳዩ ይጠበቃል ።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

givemesport.com

ዌስትሃም ዲክላን ራይስን መያዝ ከቻለ በውድድር አመቱ ለክለቡ ግዙፍ ጥቅም ይኖረዋል።  አንዴ እንደ የጎን ኳስ ማቀበል ጥበበኛ ተደርጎ ይቆጠር ነበር ፤  የድሃው ልጅ ሰርጂዮ ቡስኬትስ ፣ አሁን አሁን ግን እሱ እንደዛ ዓይነት እንዳልሆነ ግልፅ ነው።  እንግሊዝ በዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒዮና ወደ ፍፃሜ ውድድር ያደረገው ግስጋሴ ይህንን አረጋግጧል። አሁን ሞዬስ ተፅዕኖ ፈጣሪውን የተከላካይ አማካይ ለማቆየት የተቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት።  ከ 2021 ጀምሮ ራይስ የመዶሻዎቹ ምክትል አምበል ነው።  ይህ በክለቡ ከቆየ ከሚያገኘው የጨዋታ ጊዜ ጋር ተደምሮ እንደሚመቸው ጥርጥር የለውም።

standard.co.uk

ልንጠብቀው የሚገባ ሌላ ተጫዋች ሁለገብ የሆነው የ 31 ዓመቱ ሚካኤል አንቶኒዮን ነው።  በእግር ኳስ ዘመኑ እንደ አጥቂ ፣ የክንፍ ተጫዋች እና በመከላከል ውስጥም ተጫውቷል።  ተጫዋቹ ራሱ የሚመርጠው ቦታ በክንፍ ላይ መሆኑን ይናገራል ፣ ግን አንቶኒዮ ባለፈው የውድድር ዘመን 10 ጊዜ ግብ ማስቆጠር ችሏል ፣ ይህም የግል ሪከርድ ነው እና በመጪው የውድድር ዘመን ለዌስትሃም የፊት መስመር አስፈላጊ እንደሚሆን ግልጽ ነው።

ሌስተር ሲቲ እግር ኳስ ቡድን

https://www.footballticketnet.com/

ባለፈው የውድድር ዘመን ቀበረዎቹ  በተለያዩ ጨዋታዎች ብዙ ነጥቦችን መሰብሰብ ቢችሉም አሁንም የአውሮፓ ቻምፒዮንስሊግ ተሳትትፎ ማሳካት አልቻሉም ።

ቢሆንም ይሄ ሙሉውን ታሪክ አይናገርም። ሌስተሮች በእውነቱ ከባለፈው ዓመት 4 ተጨማሪ ነጥቦችን በመሰብሰብ በሊጉ በጣም ጥሩ የስኬት ጊዜ አሳልፈዋል ። በኢትሃድ እስቴድየም ማንቸስተር ሲቲን 5 – 2 ፣ አርሰናል ፣ ቸልሲ ፣ ሊቨርፑል ፣ ቶትንሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸነፉበትን ጨዋታ ለብዙ ግዜ ይታወሳል ። ይህ ደግሞ ቀበረዎቹ ስድስቱን የ‹ሱፐር ሊግ› ቡድኖችን አሸንፈዋል ማለት ነው ።  ኤፍኤ ዋንጫን በታሪካቸው ለመጀመርያ ግዜ አንስተዋል ።

ከእነዚህ ውጤቶች ውስጥ የተወሰኑትን ያስመዘገቡት በተጫዋቾች ጉዳት ተጨናንቀው በነበሩ ሰአት ነው ።  ከዩሪ ቲለማንስ እና ከማርክ አልብሪተን በስተቀር እያንዳንዱ ዋና የውጪ ሜዳ ተጫዋች ባለፈው የውድድር ዘመን ጉዳት ደርሶበታል።  ከእነዚህ ጉዳቶች መካከል አንዳንዶቹ በመጥፎ ጊዜ ላይ ነበር የተከሰቱት።

 ጄምስ ጀስቲን እና ሃርቬይ ባርኔስ ለእንግሊዝ የዩሮ 2020 ቡድን ዕጩ ሆነው እየቀረቡ በነበሩበት ወቅት ነው የሙሉ አመት ጉዳት ያጋጠማቸው ።  ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋና ተከላካያቸው ጆኒ ኢቫንስ አብዛኛው የፕሪሚየር ሊጉን ውድድር አምልጦታል ።

ይህን ስናስብ ሌስተር በቀላሉ ምርጥ ስድስቱን መቀላቀሉ የበለጠ አስደናቂ ነው።  ቢሆንም ግን በፉልሃም እና በኒውካስትል ያጋጠማቸውን አመቱን የሚያበላሹ ሽንፈቶችን ለመቀበል ቀላል አይሆንም ።  በዚህ የውድድር አመት አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ምናልባትም ቀበሮዎቹን ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመውሰድ ተስፋ አድርጓል።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

lcfc.com

በሌስተር በኩል እንደ ወትሮው  በዚህ የውድድር ዘመን ጄሚ ቫርዲን ይመልከቱ ። አንጋፋው አጥቂ ከቀበሮዎቹ ጋር 245 ጨዋታዎችን የተሰለፈ ሲሆን 118 ጊዜ ኳስ ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 38 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል።

footballtransfers.com

ሌላው መታየት ያለበት ተጫዋች  ቤልጄማዊው የአጥቂ አማካይ ዮሪ ቲሌማንስ ነው። በፍጥነት ፣ በትኩስ ኃይል እና በእድገቱ የሚታወቀው ተጫዋች ለቫርዲ ጥሩ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን እንደሚያቀብል እና ለራሱ ብዙ ጎሎችን እንደሚያስቆጥር ምንም አያከራክርም ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football