Connect with us
Express news


Football

ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ቅድመ -እይታ; ቶተንሃም ሆትስፐር እግር ኳስ ቡድን

Premier League (EPL) Preview; Tottenham Hotspur FC
eurosport.com

ስፐርሶች ባለፈው የውድድር ዓመት መጥፎ ወቅት ነበር ያሳለፉት። አዲሱ አሰልጣኝ ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶ ለውጥ ለማምጣት እና ቡድኑን ለማነሳሳት ይፈልጋል።

በኖቬምበር 7 ቶተንሃም ሆትስፐር በፕሪሚየር ሊጉ (ኢፒኤል) የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ መቀመጥ ችለው ነበር። በውድድር ዘመኑ መጨረሻ አካባቢ ግን በግዚያዊ  አሰልጣኝ  ራያን ሜሶን እየተመሩ ወደ 7 ኛ ደረጃ ዝቅ ብለው ነበር።

shropshirestar.com

ራሱን ‘የተለየ’ ብሎ የሚጠራው አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ከሊግ ካፕ ፋይናል ትንሽ ቀናት በፊት ማሰናበት በኋል ለጊዜውም ቢሆን በሜዳ ውስጥ ወጥ የሆነ አቋም ለማሳየት እና መደበኛ ዋና አሰልጣኝ ለማኝየት በጣም ተቸግረው ነበር ። ብዙ አሰልጣኞች ስማቸው ከቡድኑ ጋር ተነስቶ ነበር ። በሚያሳዝን ሁኔታ አንቶኒዮ ኮንቴ ፣ ጌናሮ ጋቱሶ ፣ ፓውሎ ፎንሴካ እና ሞሪሲዮ ፖቼቲኖ ሁሉም ክለባቸውን ለቀው ስፐርሶችን መቀላቀል አልፈልጉም ነበር ።  ስፐርሶች በመጨረሻ የዎልቭስ ዋና አሰልጣኝ የነበረው ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶን መርጠዋል። አርጀንቲናዊው አዲስ አቀራረብ ይዞ ይመጣል እናም ለዋንጫ ይፎካከራል ተብሎ ይጠበቃል። የቻምፒዮንስ ሊግ ውልደት እና ከዛ ጋር ተያይዘው የሚመጡት ክብር እና ገንዘብ ፣ለአሰልጣኝ ኑኖ እስፓሪቶ ሳንቶ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ‹ቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም› ተብሎ በሚጠራው ስታዲየም ሥራውን እንዲቀጥል አስፈላጊ ናቸው ።

አዲሱ አሰልጣኝ

cetralto.com

ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶስ ወይም በአጭሩ ‹ኑኖ› ብቃት እና ልምድ ያለው የተመሰከረለት አሰልጣኝ ነው። በዎልቭስ የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ ዋንጫ አንስተው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲያድጉ አድርጓል። ከዛ በኋላ ከ1980 ወዲህ የመጀመርያውን ከፍተኛ ደረጃ ይዘው እንዲያጠናቅቁ አድርጓል። ቡድኑን ወደ የዩኤፋ አውሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜም አድርሷል። ይህንን ሁሉ በማሳካት የብዙ የዎልቨርሃምፕተን ደጋፊዎች ፍቅር እና ክብርን አግኝቷል። ባለፈው የውድድር ዘመን በ ኢፒኤል በ 13 ኛ ደረጃ ላይ በመጨረስ አስደናቂ ስኬት ባያሳካም የስፐርስ ደጋፊዎች ይህ እስከዛሬ ድረስ በጣም አስደናቂ በሆነ የማሰልጠን ዘመኑ ላይ ያጋጠመ ትንሽ ብልጭታ እንደነበር ተስፋ ያደርጋሉ።

ኑኖ ለቶትንሃም ሲፈርም ይህንን ብሏል;

ጥራት እና ተሰጥኦ ያለው ቡድን ሲኖርህ ደጋፊዎችህን እንዲኮሩ እና እንዲደሰቱ ማድረግ ትፈልጋለህ። [እዚህ መሆን] ትልቅ ደስታ እና ክብር ነው ፣  በጣም ደስተኛ ነኝ እናም ሥራ ለመጀመር በጉጉት እየጠበቅኩ ነው። ምንም የምናጠፋው ቀን አይኖርም ስለዚህም የቅድመ – ውድድር ዘመን የአቋም መለክያ ጨዋታዎች በቅርብ ቀናት መጀመር አለብን ።

ኑኖ በዎልቭስ ውስጥ ከነበሩት የበለጠ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች በስፐርስ ውስጥ ይኖሩታል ይህም ደስተኛ ያደረገው ይመስላል ፣ ስፓርሶችም ቢያንስ ክለቡ በአሰልጣኝነት ዘመኑ ስኬታማ እስከሆነ ድረስ ከሱ ጋር መስራት የፈለጉ ይመስላሉ።

የሃሪ ኬን አወዛጋቢ ጉዳይ

የስፐርሱ አጥቂ  ለቅድመ-ውድድር ልምምድ ሪፖርት ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆኑ የቅርብ ጊዜ ዜና ሆኗል ። በግልጽ ለመናገር ፣ ስፐርሶች ዋጋ ያለው ነገር በጭራሽ አያሸንፈው አያውቁም እናም ይህ በጣም ጎበዝ አጥቂ ሳጥኑ ውስጥ ዋንጫ ማስቀመጥ ይፈልጋል። ለስፐርስ ትልቁ ችግር ኬን ወደ ሌላ ክለብ መዘዋወር እንደሚፈልግ በአደባባይ መናገሩ ነው። እሱን ለማስፈረም ፍላጎት ካሳዩት ቡድኖች የ ኢፒኤል ሻምፒዮኑ ማንቸስተር ሲቲ አንዱ ነው ፣ ነገር ግን የስፐርስ ሊቀመንበር ዳንኤል ሌቪ በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም የተለያዩ ሀሳቦች አሏቸው። ኬን እስከ 2024 የሚያቆየውን ኮንትራቱን ማየት እንዳለበትም አጥብው ይናገራሉ።

ይህ በተጫዋች እና አሰልጣኝ መካከል እውነተኛ የሥልጣን ሽኩቻ ይመስላል ፣ ኬን የማንቸስተር ሲቲ ዝውውር ተስፋ በማድረግ ለሥልጠና መቅረብ ፈቃደኛ አለመሆን በብዙዎች ዘንድ የዘገየ እና ጠብ ሊያስነሳ የሚችል ዘዴ ነው ይላሉ ። ስፐርሶች እሱን ማቆየት ከቻሉ በዚህ የውድድር ዘመን እንደገና በአጥቂ ክፍሉ ውስጥ ወሳጥ ተጫዋች ይሆናል።

በዚህ የውድድር ዘመን ሌሎች መታየት ያለባቸው ተጫዋቾች

thetimes.co.uk

ቀጥተኛ ፣ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፣ በልበ ሙልነት እና በተነሳሽነት የተሞላ ፣ እና ጥሩ ጎል የማየት አይን ያለው የደቡብ ኮሪያው ተጫዋች ሶን ሄንግ-ሚን በዚህ የውድድር ዘመን እንደገና መመልከት ካሉብን ተጫዋቾች አንዱ ነው። ኬን በጉዳት ከሜዳ በራቀበት ጊዜ የአጥቂ መስመሩን በተሳካ ሁኔታ መርቷል ።

ግብ ጠባቂው ሁጎ ሎሪስ ሌላው የስፐርስ ምርጥ ተጫዋቾች ነው። በእርግጥም በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች አንዱ ነው። ፈረንሳዊው ባለፈው የውድድር ዘመን ከ38 ጫወታዎችን አድርጎ በ12 ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት ወቷል ። ከኋላ ሲጫወቱ የነበሩትን ተከላካዮች ከግምት ካስገባን ይህ ቁጥር መጥፎ አይደለም!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football