Connect with us
Express news


Football

ፕሪሚየር ሊግ ቅድመ -እይታ; ማንቸስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ቡድን

Premier League (EPL) Preview; Manchester United FC
unitedinfocus.com

ማንችስተር ዩናይትድ ባለፈው ዓመት ኢ.ፒ.ኤል. 2 ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል ፣ ነገር ግን ከከተማው ተቀናቃኛቸው ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በ12 ነጥቦችን ርቀው ነበር ያጠናቀቁት። የማንችስተር ቀይ ግማሽ ጨዋታቸውን በማሻሻል በዚህ የውድድር ዘመን ከሰማያዊ ግማሽ ጋር ለዋንጫ ሊወዳደር ይችላል?

ባለፈው ዓመት

ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፈው ዓመት የውድድር ዘመን አስቸጋሪ አጀማመር ከጀመረ በኋላ በመጨረሻ በሊጉ ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል። ዋና አሰልጣኝ እና የቀድሞ የዩናይትድ ተጫዋች ኦሌ ጉናር ሶልሻየርም ከ 8 ጨዋታዎች በኋላ ሊባረሩ ተቃርበው ነበር ነገር ግን ከታህሳስ ዓለም አቀፍ ዕረፍት በኋላ ነገሮችን ቀይረዋል። ብዙ ጠበብቶች ቡድኑን በደረጃ ሰንጠረዡ መሃል ላይ እንደሚያጠናቅቁ እየጠቆሙ ነበር ፣ ነገር ግን ጥር ሲደርስ 1 ኛ ደረጃ ላይ ነበሩ።

goal.com

ጥሩ ጊዜ

በማንችስተር ዩናይትድ ባለፈው የውድድር ዘመን ብዙ ጥሩ ጊዜያት ነበሩ ፣ ዋናው ግን በኦልትራፎርድ የራልፍ ሁሴንህትል ሳውዝሃምፕተን ቡድን ላይ ያደረሱት የ9-0 የማፈራረስ ሥራ መሆን አለበት። ቀያይ ሰይጣኖቹ በጨዋታው ግማሽ 4-0 ሲመሩ ቀሪዎቹ 5 ግቦች በሁለተኛው አጋማሽ ነበር የተቆጠሩት። ማንችስተር ዩናይትድ መመለሱን እና እንደገና እንደ ሀያል ሊቆጠር የሚችል ቡድን መሆኑን የሚያሳይ ጨዋታ ነበር።

manutd.com

መጥፎ ጊዜ

ለማንቸስተር ዩናይትድ ባለፈው የውድድር ዘመን ዝቅተኛው ጊዜ ከቶተንሃም ጋር ነበር። የሶልሻየር ቡድን በኦልድትራፎርድ 1-6 ሲሸነፍ ማለት ነው። ለሶልሻየር አሳፋሪ የነበረው ነገር (ከአሳማሚ ውጤት እና በሜዳው ከመሆኑ ባሻገር) ፣ በሰአቱ የቶተንሀም አሰልጣኝ የነበረው የቀድሞው የቀይ ሰይጣኖች አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ መሆኑ ነው። ያ ሽንፈት ሶልሻየር በአስቸኳይ ከሥራ እንዲባረር የነበረውን ጥሪ ጮክ እንዲል አድርጎት ነበር ።

standard.co.uk

ምርጥ ተጫዋቾች

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ ኤዲሰን ካቫኒ እና ሉክ ሾው እዚህ መጠቀስ አለባቸው። ፈርናንዴስ ለቀይ ሰይጣኖች የማይታመን ነበር። የፍራንክ ላምፓርድን በአንድ የውድድር ዘመን የ 28 ግቦችን ሪከርድ ሰብሯል። ኤዲሰን ካቫኒ የክሪስቲያኖ ሮናልዶ 7 ቁጥር እርግማን 10 ግብ በማስቆጠር ሰብሮታል። ከፖርቹጋላዊው በኋላ ያንን ማሊያ ለብሶ በተጫወተ ማንኛውም ተጫዋች ከተቆጠረው በላይ ማለት ነው። ካቫኒ ከቪላሪያል ጋር በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ያገባውን አንድ ጨምሮ በዩሮፓ ሊግ ውስጥ 6 ጊዜ ኳስ ከመረብ አገናኝቷል።

ሉክ ሻው ባለፈው የውድድር ዘመን ለማንችስተር ዩናይትድ ፍፁም ለዋጭ ነበር። ክለቡ አሌክስ ቴሌስን በግራ ጎኑ ያለውን ጥራት ለማሻሻል አስፈርሟል ፣ ነገር ግን ሻው ይህንን አይቶ በሚያስደንቅ ሁኔታ እየተከላከለ እንዲሁም የማጥቃቱን ፍጥነት ከፍ ሲያደርግ ነበር ። ቀያዮቹ ሰይጣኖች በሁሉም ውድድሮች በተመለከቱት ጥሩ አቋም ምክንያት ውሉን ለማራዘም ይፈልጋሉ።

በዚህ አመት

የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ጅማሮ አሁን ከ 2 ሳምንት ያነሰ ጊዘ ነው የቀረው! በቅርቡ ኮንትራቱ ከተራዘመ በኋላ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር በ 3 ኛ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ አመቱ ቀዮቹን ሰይጣኖች ለመምራት በጉጉት ይጠብቃል። በአሁኑ ጊዜ በክለቡ ዙሪያ ትልቅ የአዎንታዊነት ስሜት ያለ ይመስላል እናም በቅርብ ጊዜ በጄደን ሳንቾ እና ራፋኤል ቫራን እንዲሁም አንጋፋው ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን ፊርማዎች ተበረታተዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን እውነተኛ ስኬት የሚያመጣ ከሆነ ፣ ከመጀመሪያ ጀምሮ ጥሩ ጥሩ ውጤቶችን ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል ። በወረቀት ላይ ሲታይ፣ የአመቱ መጀመሪያ ላይ በአንፃራዊ ሁኔታ የማያስቸግሩ ጨዋታዎች ያሏቸው ይመስላል ። እስከ 8 ኛው ሳምንት ድረስ የባለፈው አመት የምርጥ 6 ቡድን አይገጥሙም። ያለፈው ዓመት የመክፈቻ ጨዋታዎች አይነት ውጤት መደገም ለኦልድትራፎርድ ደጋፊዎች በቂ አይሆንም። ማግኘት ከሚችሉት 18 ነጥቦችን 7 ነጥቦችን ብቻ ሰብስበው እስከ 5 ኛ ጨዋታቸው ድረስ በሜዳቸው ድል አላስመዘገቡም ነበር።

ሌሎች መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

sport.aktualne.cz

ሃሪ ማጉየር ለማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ግንብ ነው። ባለፈው ዓመት አስጨናቂውን መርሃ ግብር ተቋቁሞ እያንዳንዱን ጨዋታ ተጫውቷል። በሶልሻየር ተከላካይ ክፍል ውስጥ ዋና አደራጅ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ለቡድን አጋሮች ትእዛዝ ሲሰጥ ይሰማል። የማጉዋየር አስፈላጊነት ምናልባት ከሊቨርፑል ጋር ሳይጫወት ሲቀር ቡድኑ ላይ ያለው ለውጥ ታይቷል ፣ የዩናይትድ ተከላካዮችም ያለ እሱ ሲቸገሩ ጎልተው ይታዩ ነበር። በዚህ አመትም ከማጉዋየር ሌላ ጠንካራ እንቅስቃሴ ይጠብቁ።

አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ አብዛኛውን የውድድር ዘመኑን በትከሻውና በቁርጭምጭሚቱ ካጋጠመው ጉዳት ጋር ተጫውቷል። ሰውነቱን ለመጠበቅ ብዙ ጊዜ እራሱን እየጠበቀ ሲጫወት ቢታይም በሁሉም ውድድሮች ላይ 21 ጊዜ ጎል አስቆጥሮ እና 12 ለ ግብ ሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል። ራሽፎርድ ከማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጫዋቾች አንዱ እንደነበረ ምንም ጥርጥር የለውም እናም ለማጥቃት ጨዋታው የግብ ስጋት ፣ ተለዋዋጭነት እና ግላዊ ብቃት ይጨምራል። እንዲሁም ተጫዋቹ ከአውሮፓ ሻምፒዮና ሀዘን እና ጣሊያኖች ላይ ያንን ቅጣት ከሳተ በኋሏ እንዴት እንደሚመለስ ማየት አጓጊ ይሆናል። ምልክቶቹ አብዛኛዎቹ የእንግሊዝ እግር ኳስ ደጋፊዎች ከጀርባው መሆናቸው ነው እና ይህ በተለይ ለማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች እውነት ነው። ስለዚህ ፣ ወደ ሙሉ የአካል ጤንነት የተመለሰ ማርከስ ራሽፎርድ በዚህ አመት በጥሩ ሁኔታ የመሥራት ችሎታ እና ጥሩ ብቃት ማሳየት ይችላል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football