Connect with us
Express news


Football

ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ቅድመ – እይታ; አርሰናል እግር ኳስ ቡድን

Premier League (EPL) Preview; Arsenal FC
arsenal.com

መድፈኞቹ ባለፈው የውድድር ዘመን ከሰሜን ለንደኑ ተቀናቃኛቸው ቶተንሃም ሆትስፐር በአንድ ደረጃ አንሰው 8ኛ ደረጃን ላይ ሆነው ማጠናቀቃቸው በጣም እሚያበሳጭ ነበር ።  በዚህ የውድድር ዘመን ወደቀድመው ብቃታቸው ይመለሳሉ ወይንስ ሌላ መጥፎ አቋም ያሳያሉ ።

ያለፈው የውድድር ዘመን

silly season.com

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በኤሚሬትስ የመጀመሪያው የውድድር ዘመኑ አሰልቺ ነበር። በ8ኛ ደረጃ መጨረስ ማለት መድፈኞቹ ቢያንስ ወደ ዩኤፍ ኮንፈረንስ ሊግ (ዩሲኤል) እንኳን መግባት አልቻሉም ማለት ነው። በዚህ ምክንያት አንዳንድ የአርሴናል ደጋፊዎች አርቴታን ቡድኑን እንዲለቅ ሲጠይቁ ሌሎች ደግሞ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጠው እንደሚገባ ሀሳብ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

የሊግ አቋም

በፕሪሚየር ሊጉ 13 ሽንፈቶች እንደ አርሴናል ላሉት ትላልቅ ቡድኖች በጣም አስደንጋጭ ስታቲስቲክስ ነው። የአርሰናሎች የባለፈው ዓመት ትልቁ ችግር ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት አለመቻላቸው ነበር። ብዙ ተንታኞች የቡድኑን ዋና አሰልጣኙ ከቡድኑ ጋር የሚያሳየው ክፍተት ፣ ከመጠን በላይ የመከላከል ስልት እና በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ትክክለኛውን የማጥቃት ስልት አለመጠቀሙ ነው ይላሉ።

ምርጥ ተጫዋች

arsenal.com

ባለፈው ዓመት የአርሰናል ምርጥ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ነበር ማለት ይቻላል። ከሌሎቹ የቡድኑ አባላት በተለየ መልኩ በሜዳው ወጥ የሆነ አቋም አሳይቷል። የእንግሊዝ ደጋፊዎችም በቅርቡ በተደረገው የአውሮፓ ሻምፒዮንሺፕ ውስጥ ምን ማድረግ እንደሚችል ለማየት ችለዋል ።

በዚህ የውድድር ዘመን

አርሰናል እና አርቴታ በዚህ የውድድር ዘመን ቢያንስ የተወሰነ መሻሻል ይጠበቅባቸዋል። ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ ጎልቶ የታየው የክለቡን ውድቀት መቀልበስ አለባቸው። ዝቅተኛው መስፈርት ከ8 ኛ ደረጃ በላይ ሆኖ መጨረሽ ሲሆን ምናልባትም ለሻምፒዮንስ ሊግ ቦታ መፎካከርም ይሆናል።

አርቴታ በዚህ ጉዳይ ላይ ብሩህ ተስፋ የሚያይበትን ምክንያት ይናገራል። ከአውሮፓ እግር ኳስ ለአንድ ዓመት ርቀው የተመለሱት ሊቨርፑል እና ቼልሲዎች በአርቴታ እና አርሰናል በብዛት እንደምሳሌ እየተነሱ ነው ።

በማንኛውም የአውሮፓ ውድድር አለመሳተፍ እና ወረርሽኙ በአርሴናል ፋይናንስ ውስጥ ትልቅ ክፍተት ፈጥሯል። ይህ እንዳለ ሆኖ ፣ በዝውውር መስኮቱ የነበራቸው ተሳትፎ ፈጣን ነበር። 75 ሚልዮን ፓውንድ ገደማ ለአማካይ አልበርት ሳምቢ ሎኮንጋ እና ለተከላካዮቹ ኑኖ ታቫሬስ እና ቤን ኋይት ወጪ አድርገዋል። የቀድሞው የብራይተን ተጫዋች ኋይት መድፈኞቹን 50 ሚልዮን ፓውንድ አስከፍሏቸዋል ። እነዚህ ሁሉ ተጫዋቾች የ 23 ዓመት ወይም ከዚያ በታች ናቸው ፣ ይህ ደግሞ አርሴናሎች ሃብታቸውን ወጣት ተጫዋቾች ላይ ማፍሰስ እንደሚፈልጉ ያመለክታል።

በዚህ የውድድር ዘመን መታየት ያለባቸው ተጫዋቾች

ቶማስ ፓርቴይ በጉዳት ምክንያት የአርሴናል የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት ቆይታ በጣም ከባድ ነበር ። በተቻለው አቅም ፈጣን ኳሶችን በማቀበል ፣ በጉልበት በመጫወት እና አሪፍ ቦታዎችን በመያዝ የኢፒኤል አማካይ መስመርን መቆጣጠር እንደሚችል አሳይቷል። ከአትሌቲኮ ማድሪድ የፈረመው ተጫዋች ወት አቋም ማሳየት ከቻለ በደረጃ ሰንጠረዡ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል የቅድመ-ውድድር ብቃቱ ያሳያል ።

africatopsports.com

በ 72 ሚልዮን ፓውንድ የክለቡ ሪከርድ በሆነው ገንዘብ የፈረመው አይቮሪኮስታዊው የክንፍ ተጫዋች ኒኮላስ ፔፔ በመጪው የውድድር ዘመን ሌላ የምንመለከተው ተጫዋች ይሆናል። ተጫዋቹ በሁለቱም ጎኖች ላይ መጫወት የሚመቸው ቢሆንም ቆርጦ ገብቶ በግራ እግሩ ለመጫወት እንዲመቸው በቀኝ በኩል መሰለፍ ይወዳል ። በወቅቱ የሊል አሰልጣኝ ማርሴሎ ቢኤልሳ ወደ አጥቂ ተጫዋች ተቀይሮ ነበር። አርሰን ቬንገር ለቴሪ ሄንሪ ያደርገው እንደነበር አርቴታ ፔፔን በዚህ መንገድ ሊጠቀምበት ይችላል?

paininthearsenal.com

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football