Connect with us
Express news


Football

ሊግ 1 ቅድመ -እይታ; ምርጥ ክለቦች

Ligue 1 Preview; The Top Clubs
cbssports.com

በዚህ የውድድር ዘመን ለሊግ 1 ዋንጫ የሚፎካከሩ ክለቦችን እንመልከት። ፓሪስ ሴንት ጀርሜን (ፒኤስጂ) ዋንጫውን ለማንሳት ግዙፍ ተጠባቂዎች ናቸው። ሌሎች ቡድኖች እነሱን ለማቆም ኃይል አላቸው ይሆን?

ሊል ኦኤስሲ

ሊል ባለፈው የውድድር ዘመን ዋንጫውን ለማንሳት እጅግ በጣም የተጠበቁትን ፓሪስ ሴንት ጀርሜንን(ፒኤስጂ) በልጠው ዋንጫውን ሲያሸንፉ እና ትልቅ አግራሞት ፈጥረው ነበር። ሊል ከአሰልጣኝ ክሪስቶፍ ጋልቴር ጋር፣ ፒኤስጂን ለ 3 ዓመት የፈረንሳይ እግር ኳስ ላይ የነበረውን የበላይነት ያበቃ አስደናቂ አመት አሳልፏል። ቡድኖቹ ለአብዛኛው የውድድር ዘመን አንገት ለአንገት የነበሩ ቢሆንም ሊሎች ከሜዳቸው ውጪ በፓርክ ዴ ፕሪንስ ላይ 1-0 ሲያሸንፉ ነው ዋንጫውን ማግኘታቸውን ያረጋገጡት። ሆኖም አሁን ጋልቴር ከሊል ለቆ ወደ ኒስ ተቀላቅሏል። አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ጆሴሊን ጎርቬኔክ ያለፈውን የውድድር ዘመን መድገም እንደሚፈልግ እርግጥ ነው። ጥያቄው እሱ ያንን ለመድገም የሚያስችል የማሰልጠን ችሎታ አለው ወይ ነው። በተጨማሪም የቱርኩ አጥቂ ቡራክ ይልማዝ ከዩሮዎች እፍረት አገግሞ በዚህ የውድድር ዘመን ለሊል ጥሩ እንቅስቃሴ ለማድረግ በአእምሮ ዝግጁ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ይደረጋል።

ፓሪስ ሴንት ጀርሜንን እግር ኳስ ቡድን(ፒኤስጂ)

psgtalk.com

ፒኤስጂዎች በዚህ ዓመት የሊግ 1 ን ዋንጫ ለማንሳት ከባድ ተጠባቂዎች ናቸው። በወረቀት ላይ አሁን ካለፈው ዓመት የበለጠ ከባድ ቡድን ይመስላሉ። ጣሊያናዊው የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማም ከመፈረሙ በተጨማሪ ፒኤስጂ ሰርጂዮ ራሞስን እና ጂዮርጊኒዮ ዋንያልደምን አግኝቷል። እነዚህ ሁሉ ዝውውሮች በነጻ ነበሩ! የፒኤስጂ ቡድን አቻራፍ ሃኪሚ ከኢንተር ሚላን የ 70 ሚሊዮን ዩሮ ማግኘቱ ደግሞ አሁን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ አስፈሪ እንዲመስል አድርጎታል። በዚህ ምክንያት እና እንደ ኔይማር እና ኪሊያን ምባፔ ባሉ ቁልፍ ተጫዋቾች ላይ ማንኛውንም ጉዳት ካልደረሰ ፒኤስጂ በ 2022 ወደ ዋንጫ የሚያደርገውን ጉዞ ለማስቆም ከሌላው ተፎካካሪ ቡድኖች ልዩ የሆነ ነገር እንደሚያስፈልግ ግልፅ ነው። ይህን አመት አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ በጉጉት እየጠበቀ መሆን አለበት።

ኦሎምፒክ ልዮኔስ

clcfootball.org

ሊዮን ከአሰልጣኝ ሩዲ ጋርሺያ ጋር ያለውን ኮንትራት ለማቆም የወሰነ ሲሆን በዚህ አመት የደቹን አሰልጣኝ ፒተር ቦዝን አስፈርመዋል። ቦዝ በእርግጠኝነት አንዳንድ ስልታዊ መልሶ ማደራጀት ማድረግ ያስፈልገዋል። በጋርሲያ ስር ቡድኑ የተቋቋመው በሆላንዳዊው ሜምፊስ ዴፓይ ዙሪያ ነበር ፣ ነገር ግን ዴፓይ ወደ ባርሴሎና ስለሄደ ቦዝ ያንን ማድረግ አይችልም። ሊዮን ለሻምፒዮንስ ሊግ ለማለፍ ባለፈው የውድድር ዘመን በጠባቡ ያመለጠው ሲሆን ዘንድሮ ግን በብዙዎች ዘንድ ግምት ተሰጥቶታል። ሆኖም ፣ በአሰልጣኝ ለውጥ ውስጥ ሆነው ከዚህ የተሻለ ሲሠሩ ማየት ከባድ ነው።

ኤኤስ ሞናኮ

ligue1.com

በዚህ ዙር ከተዘረዘሩት ክለቦች መካከል ሞናኮ ወደ ምርጥ 3 ለመግባት የበታችነት ደረጃ የተሰጣቸው ናቸው። ሆኖም ይህ ማለት ግን በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን የማግኘት ዝቅተኛ ዕድል አላቸው ማለት አይደለም። ሞናኮ በአሰልጣኝ ኒኮ ኮቫክ እየተመራ ባለፈው የውድድር ዘመን መጨረሻ ላይ የሚያስደንቅ ጥሩ አቋም አሳይቶ ብዙዎችን አስገርሟል። የክሮሺያዊው ዋና አሰልጣኝ ቡድን ከመጨረሻዎቹ 23 ጨዋታዎች 17 ቱን ሲያሸንፍ በሂደቱ ሁለት ጊዜ ብቻ ተሸንፏል። ሞናኮም ዋና ቡድኑን እና ባለፈው የውድድር ዘመን በሊጉ ፒኤስጂን ደርሶ መልስ ያሸነፈውን ቡድን በሙሉ እንደያዘ ነው። ያንን አቋም ይዘው ወደ አዲሱ አመት መቀጠል ከቻሉ ሞናኮ ከምርጥ 3 ውጭ ሊያጠናቅቅ የሚችል አይመስልም እና ማን ያውቃል ፣ ፒኤስጂን ራሱ እንደገና ማሸነፍ ይችሉ ይሆናል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football