Connect with us
Express news


Football

የላሊጋ ቅድመ -እይታ; ትናንሽ ክለቦች

La Liga Preview; The Smaller Clubs
https://counterfootball.wordpress.com/

ከነዚህ 4 አነስተኛ ቡድኖች ውስጥ በላሊጋ ውስጥ ለመቆየት ወይም አልፎ ተርፎም ስኬታማ ጉዞ ለማድረግ የሚያስችል ብቃት ያለው ቡድን ይኖራል? ማናቸውስ በዚህ በተወሰኑ ክለቦች የበላይነት ዝነኛ በሆነው ሊግ ውስጥ ያሉ ምርጥ ቡድኖችን ሊፈትኑ ይችላሉ?

ራዮ ቫሌካኖ

fcbarcelona.fr

ራዮ ቫሌካኖ በአስደናቂ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የመጨረሻውን የላሊጋ ቦታን ያገኘ አዲስ ያደገ ቡድን ነው። አንዴ ደስታው ካለፈ በኋላ ግን በዚህ ክለብ ውስጥ አሳሳቢችግሮች እንዳሉ አሁንም ግልፅ ነው። ከእነዚህ ጉዳዮች በጣም አጣዳፊው የዋና አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላን የወደፊት ሁኔታ ነው። ኢራኦላ በቅርብ ሳምንታት ከሌሎች ቡድኖች ጋር በጥብቅ ስሙ እየተነሳ ሲሆን ውሉ በወሩ መጨረሻ ላይ ኮንትራቱ ያበቃል። ራዮ ቫሌካኖ ከመውረድ ጋር መታገል ካልፈለጉ ይህንን ችግር በአስቸኳይ መፍታት አለባቸው። በአንድ ጨዋታ ብቻ ራሱ ትልልቅ ቡድኖችን መገዳደራቸው በጣም አጠራጣሪ ይመስላል። ይህ ክለብ ከሪያል ማድሪድ ፣ ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ከባርሴሎና ጋር በገንዘብም ሆነ በሜዳ ላይ ሊወዳደር አይችልም።

ዴፖርቲቮ አላቬስ

footballticket.net

ዴፖርቲቮ አላቬስ በእርግጠኝነት እንደ “ትንሽ ክለብ” ይቆጠራሉ ፣ ግን ቢያንስ በስፔን እግር ኳስ ከፍተኛ ሊግ ውስጥ ጥሩ የሚባል ታሪክ አላቸው። ከ 2016-17 የውድድር ዘመን ጀምሮ በላሊጋ ውስጥ ቆይተዋል። እንዲሁም አንዳንድ የአውሮፓ እና የኮፓ ዴል ሬይ ተሞክሮ አላቸው። እ.ኤ.አ. በ 2001 አላቬስ ለ ዩኤፋ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ደርሰው በሊቨርፑል ሲሸነፉ ፣ እ.ኤ.አ. በ 2017 በኮፓ ዴል ሬይ ፍፃሜ ላይ ከባርሴሎና ጋር ተገናኝተው 1-3 ተሸንፈዋል። አሰልጣኙ ሆዜ አንቶኒዮ ኩሬጄታ አልቱና በዚህ ወቅት ተመሳሳይ ታሪክ መድገም ከቻለ ለእሱ እና ለክለቡ ጥሩ ነገር ይሆናል። የማይቻል ነገር የለም የሚባል ቢሆንም ፣ ግን ዴፖርቲቮ አሌቭስ ለላሊጋ ዋንጫ ይወዳደራል ማለት ዘበት ነው። እነሱ ሊጠብቁ የሚችሉት በጣም ጥሩው ነገር በሌላ ዋንጫ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ እና ምናልባትም በተወሰኑ ጨዋታዎች ትልልቅ ቡድኖችን ባልተገመተ ሁኔታ መፈተን ሊሆን ይችላል።

ቫሌንሲያ እግር ኳስ ቡድን

france24.com

ባለፈው የውድድር ዘመን በላሊጋ በ 13 ኛ ደረጃ ላይ በመጨረስ ይህንን የትንሽ ክለቦች ዝርዝር የተቀላቀለው ቫሌንሲያ ነው። ወደ ላሊጋ አናት ቅርብ በሆነ ቦታ ላይ መጨረስ የለመዱት የቫሌንሺያ ደጋፊዎች 2020/21 መጥፎ ወቅት ይሆናል ብለው ፈርተው ነበር ፣ እንደፈሩትም ነው የሆነው። ከበጋው በፊት ቫሌንሲያ በርካታ ምርጥ ተጫዋቾቻቸውን ሸጠው እነሱን ለመተካት አልሞከሩም። ይህ ቡድኑ ሚዛናዊ ያልሆነ እና ከነበረው የበለጠ ደካማ እንዲሆን አድርጎታል። በቫሌንሲያ ብዙ መሥራት ይጠበቅበታል። ግን ሌላ ጥያቄ የሆነው ነገር ቦርዳቸው ይህንን ለመቅረፍ ይፈልጋል ወይ የሚለው ነው። በአሁን ሰአት በቫሌንሲያ ገንዘብ ለማውጣት ፈቃደኛ አለመሆን ያታያል እና በዛ ላይ አዲስ አሰልጣኝ ያስፈልጋቸዋል። ክለቡ ወደ ታች እያሽቆለቆለ እንደመሆኑም አሰልጣኝነቱን መረከብ ማራኪ የሚባል ሥራ አይደለም። ያለፈው አመት ለቫሌንሲያ መጥፎ ወቅት ነበር ፣ የሚቀጥለው ዓመትም ግን በጣም የተሻለ የሚሆን አይመስልም።

ሪያል ቤቲስ ባሎምፒ

theguardian.com

ሪያል ቤቲስ ባለፈው የውድድር ዘመን 6 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ጨርሷል። ሆኖም ፣ ጥቂት ክለቦች ያለማቋረጥ የበላይነትን በሚይዙበት ሊግ ውስጥ ፣ ሪያል ቤቲስ ትልቅ ክለብ ነው ብሎ መናገር ከባድ ነው። ሆኖም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በተወሰነ ደረጃ ጥሩ የአቋም ለውጥ አሳይተዋል። ሪያል ቤቲስ በ 2014/15 በሴጉንዳ ምድብ ውስጥ ሲጫወት የነበረ ቢሆንም እ.ኤ.አ. በ 2021 በላሊጋ ውስጥ ጥሩ በሚባል 6 ኛ ደረጃ ላይ አጠናቀዋል። በዚህ አነስተኛ ቡድን ዝርዝር ውስጥ ካሉ ቡድኖች ውስጥ አንዳቸው ትላልቅ ቡድኖችን የመፈተን እድል አላቸው ካልን ሪያል ቤቲስን ነው። አሰልጣኙ ማኑዌል ፔሌግሪኒ በአንጻራዊ ሁኔታ ያሏቸውን መሃከለኛ ብቃት ተጫዋቾች ጥሩ አቋም እንዲያሳዩ በማድረግ በዚህ ዓመት 6 ኛ ደረጃን ለማሻሻል መሞከር አለባቸው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football