Connect with us
Express news


Football

በዚህ አመትም የተለመደውን የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድን ፉክክር ይሆን ምንመለከተው?

Will it be the traditional battle between Barcelona FC and Real Madrid CF this season?
bleacherreport.net

በዚህ ጽሁፍ በዚህ የውድድር ዘመን ለላሊጋ ዋንጫ ተፎካካሪ የሆኑትን ዋና ዋና ክለቦች እንመለከታለን። ዋንጫውን ማን ያነሳዋል እና ሊዮ ሜሲስ የዚህ ውድድር አካል ይሆናልን?

አትሌቲኮ ማድሪድ

marca.com

በዚህ የውድድር አመት የአትሌቲኮ ማድሪድ ዋንጫ ማስጠበቅ ከሪያል ማድሪድ እና ከባርሴሎና ከባድ ፈተና እንደሚጠብቀው ግልጽ ነው። ሆኖም ባለፈው ዓመት ትንሹ የሚባለው የማድሪድ ክበብ ለገጠሙት ፈተናዎች ሁሉ መልስ አግኝቶ በመጨረሻ ሊጉን በ 2 ነጥብ ልዩነት አሸንፏል። ይህን ለማድረግ በአጠቃላይ 26 ድሎችን ፣ 8 አቻዎችን እና 4 ሽንፈቶችን አስመዝግበው 86 ነጥቦችን አግኝተዋል።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

የክንፍ ተከላካዩ ያኒክ ፌሬራ ካራስኮ ባለፈው ዓመት ግሩም የውድድር ዘመን ነበር ያሳለፈው ፣ ስለሆነም በዚህ አመትም በትኩረት መከታተል አለብን። ረጅሙ ቤልጂየማዊ በመከላከልም ላይ በማጥቃትም ላይ ጥሩ ነው።

የኡራጓይው ጠንካራ አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝ በዚህ የውድድር ዘመን ከአትሌቲኮ የሚጠበቅ ሌላ ተጫዋች ነው። አንዳንድ ሰዎች የእሱ ከባርሴሎና ለቆ መውጣት አዲሱ ክለቡ ዋንጫ ካነሳበት ዋና ምክንያቶች አንዱ ነው ይላሉ! በሊጉ 21 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን ፣ ብዙዎቹ ወሳኝ ነበሩ እናም እሱ በመጪው የውድድር ዘመንም መመልከት ያለብን የአትሌቲኮ ተጫዋች ነው።

sport.tn.nova.cz

አትሌቲኮ በዚህ የውድድር ዘመንም የሚናቅ ቡድን አይደለም። አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሚዮኔ አሁንም ጠንካራ ቡድን አለው እናም አትሌቲኮ በዚህ ዓመት እንደገና ሻምፒዮን ሊሆን ይችላል!

ሪያል ማድሪድ እግር ኳስ ቡድን

therealchamps.com

ሪያል ማድሪድ በዑደት ማብቂያ ላይ ያለ ክለብ ነው ፣ ይህም እንዳላቸው ትልቅ ተጠባቂነት አለመረጋጋት ፈጥሯል። በክለቡ ውስጥ ለውጥ ያስፈልጋል ፣ እና የመጀመሪያው ለውጥ ከዚነዲን ዚዳን መልቀቅ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ይሆናል።

የሪል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በአውሮፓ ሱፐር ሊግ ቃለ መጠይቅ ወቅት ስለ ሪያል ማድሪድ ሲጠየቅ “ማሻሻያ እንጂ አብዮት አይደለም” ብለዋል። እንደ ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ገለፃ በእርግጥ በዚህ ክረምት ለውጥ እየመጣ ነበር።

ይህንንም ካርሎ አንቼሎቲን በአሰልጣኝነት በመሾሙ አረጋግጧል። አንቼሎቲ በሰኔ ወር ከለቀቀው ከዚነዲን ዚዳን ከባዱን ሃላፊነት ተረክቧል።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

ካሪም ቤንዜማ ባለፈው ዓመት ለፈረንሣይ ብሔራዊ ቡድን ለዩሮዎች ያልተጠበቀ ጥሪ ተደርጎለት ነበር። አጥቂው ባሳለፍነው የውድድር ዘመን 30 ጎል አስቆትሯል ከዛም ባሻገር ግን ለቡድኑ ብዙ አስተዋጽኦ አድርጓል። ቤንዜማ ያላደረገው ነገር አልነበረም ፣ ነጮቹን በዚህ አመት ብዙ ጊዜ በካፒቴንነት መርቷል። ከጥልቅ እየተነሳ እና የማቀባበል ጨዋታን ተጫውቷል። ጥሩ የሆኑ ቅብብሎችን እያደረገ በተቻለ መጠን በሜዳው ላይ ሁሉንም ተጫዋች ወደ ጨዋታው ሲያስገባ ነበር።

የቤልጂየሙ ግብ ጠባቂ ቲቦው ኮርቶዋም ባለፈው ዓመት አስደናቂ የውድድር ዘመን አሳልፏል። በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 51 ጫወታዎችን በማስመዝገብ ለሪያል ማድሪድ እያንዳንዱን ጨዋታ ተጫውቷል። በነዚያ ጨዋታዎችም ሁለት ‘የጨዋታው ኮከብ’ ሽልማቶችን አግኝቷል ፣ ይህ ደሞ ለግብ ጠባቂ ቀላል አይደለም!

ባርሴሎና እግር ኳስ ቡድን

በባርሴሎና ዙሪያ የቅርብ ጊዜ አነጋጋሪው ዜና ሜጋስታር ሊዮኔል ሜሲ በክለቡ ከ 17 አስደናቂ የውድድር ዘመናት በኋላ ባርሴሎናን ለቆ እንደሚወጣ መነገሩ ነው። ይህ እውነት ይሁን ፣ ወይም በባርሴሎና/ሜሲ እና በላሊጋ መካከል በ ‘ሱፐር ሊግ’ ገንዘብ ዙርያ የሚደረግ ጨዋታ ብቻ ነው ፣ ወይም በእውነቱ የዘመናችን ምርጡ ተጫዋች ክለቡን ለቆ ይሄዳል ማለት ነው።

ከሜሲ ጋር ምንም ይሁን ምን ፣ ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን የአሸናፊነት ቀመርን እንደገና መፈለግ አለባቸው። ያለፈው ዓመት የኮፓ ዴል ሬይ ስኬት ፣ ክለባቸው ላሊጋውን ከዓመት ዓመት እንደሚያሸንፍ ለሚጠብቁ የባርሴሎና ደጋፊዎች በቂ አልነበረም።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

sportslumo.com

ሆላንዳዊው ሜምፊስ ዴፓይ ባለፈው የውድድር ዘመን 20 ግቦችን አስቆጥሮ 12 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቷል። በዚህ ምክንያት ለባርሴሎና የሚጠብቅ ተጫዋች ነው። ከሜሲ ቀጥሎ ዴፓይ ለባርሴሎና ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠው ተጫዋች ነው። ከሳጥኑ ውጪ ለሚያደርጋቸው የግብ ማመቻቸቶችም ቁጥር አንድ ሆኖ ተመድቧል።

የ 1.94 ሜትሩ ግዙፍ አንጋፋው ጄራርድ ፒኬ ከትውልዱ ምርጥ ተከላካዮች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል። ፒኬ ዘመናዊ የጨዋታ ዘይቤ አለው። እሱ ጥንካሬን እና የማጥቃት ችሎታን ከጥሩ ቴክኒክ እና ማቀበል ችሎታ ጋር ያጣምራል። በአየር ላይ ኳሶችም ጥሩ ነው።

ሲቪያ

indianexpress.com

በሲቪያ በዚህ የላሊጋ ምርጥ ቡድኖች ስብስብ ሲቪያ ያለ ምንም ጥያቄ ታናሽ የምንለው ነው። ሆኖም ባለፈው የውድድር ዘመን አራተኛ ሆነው ማጠናቀቃቸው እዚህ ዝርዝር ውስጥ ለመካተታቸው ምክንያት ነው።

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሴቪላ በጣም ስኬታማ አመት ነበር ፣ ሙሉው መንገድ ግን ቀላል አልነበረም። ጁለን ሎፔቴጊ የሴቪያ ደጋፊዎችን ልብ ለማሸነፍ ሁል ጊዜ ጠንክሮ መሥራት ነበረበት እና በራሞን ሳንቼዝ-ፒዝጁአን ደጋፊዎች ዘንድ ተወዳጅ ባልሆነ የእግር ኳስ ዘይቤው መጀመሪያ ላይ ያንን ለማድረግ ተቸግሮ ነበር።

የሚገርመው ብዙውን ጊዜ በስሜታዊ ደጋፊዎቻቸው ላይ የተመረኮዘ አቋም የነበራቸው ሲቪያ ፣ በኮቪድ ምክንያት ከተዘጉ በሮች በስተጀርባ ሲጫወቱ የተሻለ ብቃት ሲያሳዩ ነበር። አንዳሉሲያውያኑ ጨዋታዎች እንደገና ከተጀመሩ በኋላ በ 11 የሊጉ ጨዋታዎች በአንዳቸውም አልተሸነፉም እናም በቀላሉ የምርጥ 4 ደረጃን መያዝ ችለዋል።

በዛም ምክንያት ፣ በየካቲት ወር መጀመሪያ በቪጎ 2-1 ከተሸነፉ በኋላ ካለፉት 10 ጨዋታዎች 9 ቱን አሸንፈው በአጠቃላይ በ 21 ጨዋታዎች ሳይሸነፉ ወደ አዲሱ አመት ይገባሉ። ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ጥሩ መነሻ ነው።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

የላሊጋው ቡድኖች ካለፈው በጋ በፊት ካደረጓቸው ፊርማዎች ሁሉ የሲቪያ ሉካስ ኦካምፖስ ምናልባት የተሻለው ምርጫ ሊሆን ይችላል። እሱ ለጁለን ሎፔቴጊ ቡድን በጥግ በኩል በሰፊው ጎልቶ ወጥቷል እና ለጎሎች በአጥቂዎቹ ላይ ለሚተማመን ቡድን ኦካምፖስ በላሊጋው 14 ግቦች በማስቆጠር በጣም የሚፈለግ የጎል ምንጭ ነበር።

ከኦካምፖስ በተመሳሳይ ፣ ኦስካር ተፈጥሯዊ አጥቂ ባይሆንም ባለፈው አመት የቡድኑ የግብ ምንጭ ነበር ማለት ይቻላል። ሌጋኔስ በአስደናቂ ሁኔታ ሲያመልጥ 9 ግቦችን አስቆጥሯል። ከነዚህ ግቦች ቅጥት ምቶች ነበሩበት እናም በዛው በላሊጋው ውስጥ የቆመ ኳስ ሁኔታ ላይ ከምርጦቹ አንዱ መሆኑን አሳይቷል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football