Connect with us
Express news


Football

የማንችስተር ሰማያዊ ግማሽ የፕሪሚየር ሊጉን (ኢ.ፒ.ኤል.) ዋንጫ ድጋሜ ማንሳት ይችላሉ?

Can the Blue Half of Manchester Retain The Premier League (EPL) Title?
nytimes.com

ማንቸስተር ሲቲ እግር ኳስ ቡዱን ባለፈው የውድድር ዘመን በኢ.ፒ.ኤል. ያሳኩትን የዋንጫ ጉዞ ያስጠብቃሉ ወይስ ሌሎች ተፎካካሪዎች ይኖራሉ?

ባለፈው የውድድር ዘመን

የማንችስተር ሲቲ የ2019/20 ውድድር ዘመን እጅግ አሳዛኝ ነበር። ዋንጫውን ያነሳሉ ተብለው ተጠብቀው የነበሩ ቢሆንም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ለሊቨርፑል አሳልፈው ሰጥተዋል። ሆኖም እንደገና በ2020/21 የውድድር ዘመን ድጋሜ ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት ተሰጧቸው ሊጉን ጀመረዋል። ይህ ግምት የተሰጣቸው ባላቸው ጥልቅ የተጨዋቾች ስብስብ እና ለሊቨርፑል ዋንጫውን ማስጠበቅ ይከብደዋል በሚል እሳቤ ነው ።

ይህን ካልን በኋላ ማንችስተር ሲቲ የ2020/21 የውድድር ዘመን በጣም ደካማ የሆነ አጀማመር ነበረው። ዎልቨርሃምፕተን ዋንደርስ በሜዳቸው አሸንፈው ቢጀምሩም ከአንድ ሳምት በኋላ በሌስተር ሲቲ (2-5) በሆነ ሰፊ ልዩነት ተሸንፈዋል። ይህ ደግሞ ያለፈው የውድድር ዘመን ጉድለቶችን ያጎላ ሽንፈት ነበር እና ለአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አስጨናቂ ጊዜ ነበር።

ወዲያውኑ ከዚያ ውጤት ያገገሙ ቢሆንም ፣አሁንም ግን አጨዋወታቸው እና ውጤቶቻቸው አስደናቂ አልነበሩም። በተለይ አጨዋወታቸው ደካማ ነበር። በዚህ ወቅት ሼፊልድ ዩናይትድ እና ፉልሃምን አሸንፈዋል ፣ነገር ግን በዚያን ጊዜ የዋንጫ ተፎካካሪ በነበረው ቶተንሃም ሆትስፐር አስደንጋጭ ሽንፈትን አስተናግደዋል!

bitterandblue.sbnation.com/

ስለዚህ ፣ ጥያቄው ማንቸስተር ሲቲ እና ጋርዲዮላ ከሊቨርፑል ዋንጫዉን ሊመልሱ የሚችሉበትን አቋም ማግኘት ይችላሉ? መልሱ አጽንዖት ያለው ‘አዎ’ ነበር። የጋርዲዮላ ቡድን የውድድር ዘመኑ ሲጀመር በአጥቂ ክፍል ችግሮች ነበሩት። አጥቂዎቹ ሰርጂዮ አጉዌሮ እና ገብርኤል ጀሱስ ወጥ የሆነ አቋም አልነበራቸውም። ሆኖም ፣ በታህሳስ ወር ጋርዲዮላ የሐሰት-ዘጠኝ አጨዋወት ጀመረ፣ ይህ ስልትም በጣም አዋጪ ነበር።

የጆኦ ካንሴሎ ከፊል ተመላላሽ ክንፍ እና ከፊል-ሐሰተኛ አማካይነት እንደገና ማንሰራራቱ እንዲሁ የአሰልጣኙ ጉልህ ብልህነት የሚያሳይ ነበር። በታህሳስ አጋማሽ እና በመጋቢት መጀመሪያ መካከል ማንችስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች በተከታታይ 21 ጨዋታዎችን ያሸነፈ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 15 ቱ በሊጉ ውስጥ ነበሩ። ዋንጫውን እንዲያነሱ የረዳቸው ይህ አስደናቂ ጉዞ ነበር።

ማንችስተር ሲቲ በመጨረሻ መዋጥ የነበረበት ብቸኛው መራራ ውጤት በቻምፒየንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ በቸልሲ መሸነፉ ነው።

በዚህ የውድድር ዘመን

በዚህ የውድድር ዘመን ሌላ ቡድን ዋንጫውን ሊያነሳ ይችላል? ሁሉም ቡድኖች የተሻሻሉ ይመስላሉ ፣ ነገር ግን ሲቲ ባለፈው ዓመት ያሳደረባቸው ተፀዕኖ በጣም ከፍ ያለ በመሆኑ ከዚህ ቡድን ጋር የሚፎካከር ቡድን ማየት ከባድ ይመስላል። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን በ 2018 ያሳኩትን መቶ ነጥብ ላይ ላይደረስ ይችላል ፣ ነገር ግን ከተብታባ ጅማሮ ውጪ በቀሪው አመት በጣም ከባድ እና ምህረት የለች ቡድን ነበር ።

ይህ ጽሑፍ በሚጽፍበት ጊዜ ማንቸስተር ሲቲን በ2022 የውድድር ዘመን ዋንጫውን ድጋሜ እንዳያነሳ የሚያግደው ብቸኛው ነገር በአንድ ቁልፍ ተጫዋች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ይመስላል። ለምሳሌ ፣ ሩበን ዲያስን ወደ ተከላካይ ክፍሉ መጨመሩ የተከላካይ መስመሩ ወደ ግምብ አጥር ቀይሮታል። አምና ሊቨርፑሎች ቨርጂል ቫን ዳይክን በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ ስለነበር ዋንጫዉን ለማንሳት ከድዷቸው ነበር ፣ የዚህ ተጫዋች ጉዳትም ተመሳሳይ ተፀዕኖ ሊያሳድር ይችላል ።

መመልከት ያለብን ተጫዋቾች

ሩብን ዲያዝ

news.in-24.com

በማንችስተር ሲቲ ተከላካይ መስመር ላይ ሩበን ዲያስ ያሳደረውን ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። በመስከረም ወር በሌስተር ሲቲ 5-2 ከተሸነፈ በኋላ ዲያስ ለሻምፒኖቹ የፈረመ ሲሆን የተከላካይ ክፍሉም ቀይሮታል። በዚያ 21 ጨዋታ የማሸነፍ ጉዞ ሲቲ የተቆጠረባቸው ግቦችን 9 ብቻ ሲሆኑ አንደኛው በቅጣት ምት የተቆጠረ ነበር። ዲያስ የሲቲ የተከላካይ መስመር ብቻ አልነበረም የቀየረው ፣ ሲቲን ይለቃል ሲባል የነበረው ጆን ስቶነስንም ወደ ምርጥ አቋሙ እንዲመጣ ረድቶታል።

ኢልካይ ጉንደጋን

anglickaliga.com/

ዲያዝ የጀርባው ዓለት ከሆነ ፣ ኢልካይ ጉንደጋን በሜዳው ሌላኛው መስመር አስማተኛ ነበር። ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪያቸው በ13 ግቦች መጨረስ ያን ያህል የሚያስደንቅ አይመስልም። ነገር ግን ጉንዶጋን ያንን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንዲሆን ያደረገው የሲቲ የተጨዋች ሮቴሽን የጨዋታ ታክቲክ ነው። የጀርመናዊው ሚና ባለፈው የውድድር ዘመን ትንሽ ተቀይሯል ፣ እናም ከበፊቱ የበለጠ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football