Connect with us
Express news


Football

በ2020/21 ፕሪሚየር ሊግ ያልተሳካላቸው ተጫዋቾች!

Disasters of the Premier League 2020/21!
www.ilike.com

የትኞቹ ተጠባቂዎች ባለፈው የውድድር አመት ከቡድኖቻቸው ጋር ሳይሳካላቸው ቀሩ? በሚቀጥለው ዓመትስ ነገሮችን ለመቀየር ተስፋ አላቸው?

ዊሊያን (አርሰናል)

dailystar.co.uk

በቼልሲ ዓለምን የሚረታ መስሎ ከታየ በኋላ የአርሴናል ቴክኒካል ዳይሬክተር ኢዱ የ 32 ዓመቱን ዊልያንን በነፃ ዝውውር እና በከፍተኛ ሳምንታዊ ደመወዝ በሦስት ዓመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን እንዲ ብለው አስታወቁ።

“እሱ ወዲያውኑ በቡድኑ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ተጫዋች እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ።”

ከአራት ወራት በኋላ ግን እሱ የተለየ ሰው ይመስል ነበር – “ምን ትጠብቃለህ? ወዲያውኑ ለውጥ እንዲፈጥር? ቡም! ዊሊያን ምርጥ ሊሆን ይችላል” ግን ለዚያ ትንሽ ጊዜ ይፈልጋል።

ያ የድምጸት ለውጥ ብቻ ባለፈው ዓመት ዊልያን ምን ያህል አሳዛኝ እንደነበር ያሳያል እና ለአርሰናል መጥፎ የነበረው አመት የኤሚል ስሚዝ-ሮው የብራዚላዊውን ቦታ ተክቶ መያዝ ይበልጥ የከፋ ከመሆን ታድጎታል። በአዎንታዊ ጎኑ ዊልያን ዕድሜው 35 ዓመት እስኪሞላ ኮንትራቱ ስለሚቆይ በሰሜን ለንደን ውስጥ ለመኖር ብዙ ጊዜ ይኖረዋል።

ራያን ብሪውስተር (ሼፊልድ ዩናይትድ)

በዙሪያው እጅግ በጣም ብዙ አግራሞት ሲቸረው የነበረው የ 21 ዓመቱ ራያን ብሪውስተር ከሊቨርፑል ወደ ሼፊልድ ዩናይትድ በ 23m ፓውንድ ተዘዋውሯል። ባሳለፍነው አመት 12 ጨዋታዎችን በመጀመር 14 ጊዜ ተቀይሮ በመግባት ጨዋታዎችን ቢያደርግም አንድም ጎል አላስቆጠረም። ቡድኑም ከ 38 ጨዋታዎች በ 29 ተሸንፈው ወደ ቻምፒዮንሺፑ ወርደዋል። ይህ በረጅም እና ፍሬያማ በሆነ የጨዋታ ጊዜ ዉስጥ መጀመሪያ ላይ የተፈጠረ አጭር የተሳሳተ እርምጃ ሊሆን ይችላል ፣ ግን ደግሞ በተቻለ ፍጥነት መረሳት ያለበት ነው።

ኒል ማውፓይ (ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን)

bbc.co.uk

ባለፉት ሁለት አመታት እንዳየነው የግራሃም ፖተር ብራይተን ማራኪ የእግር ኳስ ችሎታ አላቸው እና ግን ከሚያስቆጥሩት የበለጠ ብዙ እድል ይፈጥራሉ። በግብ ፊት ያላቸው መጥፎ አጨራረስ በማውፓይ ላይ ብቻ የሚሳበብ አይደለም ፣ ነገር ግን ቀላል ኳሶችን እንደመሳቱ እናም ውድ ኮከብ አጥቂቸው እንደመሆኑ ፣ የችግሩ ዋና አካል መሆኑ አይካድም። ብራይተን በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ላይ ከመጠን በላይ የመውረድ ጫና ውስጥ አልነበሩም እና በበጀታቸው እና በታሪካቸው መሠረት መጥፎ በማይባል ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ፣ ግን ለሶስተኛ አመት ማውፓይ እና ሌሎች ሙሉ አቅማቸውን አለማሳካት ከቀጠሉ ለብራይተን የበለጠ ብስጭት የሚያስከትል ጊዜ ይሆናል።

ጆዜ ሞሪንሆ (ቶተንሃም ሆትስፐር)

football365.com

በዚህ ያልተሳካላቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አንድ ልዩ አሰልጣኝ ሊካተት ይገባዋል። ቶተንሃም ሆትስፐሮች ባለፈው የውድድር ዘመን የጠፋውን ልጃቸውን ጋሬዝ ቤልን በመመለስ እና በኦልድትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድን 6-1 በማሸነፍ ጀመሩ። በዚያን ጊዜ ጆሴ ሞሪንሆ ስለ “አስገራሚ ቡድኑ” ማውራታቸውን ጀመሩ። እነዚያ መልካም ጊዜያት ብዙም አልዘለቁም። ለወራት የደከመ የመከላከል እግር ኳስ ሲጫወቱ ከቆዩ እና በሃሪ ኬን እና በ ሶን ሂኡንግ-ሚን ላይ ከመጠን በላይ መመርኮዝን ካሳዩ በኋላ ሞሪንሆ ቡድናቸውን ወደ መሩት የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ ከመጫወታቸው በፊት በዳንኤል ሌቪ ተባረሩ።

በማንቸስተር ዩናይትድ ያሳለፈው አጥጋቢ ያልነበሩትን የውድድር ዘመናት እንኳን ሞሪንሆ በ 2017-18 ሁለተኛ ደረጃ ላይ መጨረሱን ወደ ኋላ ተመልሶ በሙያው ካሉት ታላላቅ ስኬቶች አንዱ አድርጎ ሲያቀርብ ነበር! በዚህ ጊዜ ግን የሚናገረው ነገር አልነበረም። ከመባረሩ ቀጥሎ የነበሩ ቀናትን ቀደም ሲል የነበሩትን ሁሉ ታላላቅ ስኬቶች በ ኢንስታግራም ላይ ፖስት በማድረግ ምርጥ አሰልጣኝ እንደነበረ ለማስታወስ ሲሞክር አሳልፏል።

ካይ ሃቨርትዝ (ቼልሲ)

በጣም ውድ የሆነው ዝውውር ቼልሲን ወደ አስፈሪ አጥቂ ቡድን ይለውጣል ተብሎ ነበር። ያ ሊሆን አልቻለም ፣ በፕሪሚየር ሊጉ ውስጥ አራት ግቦችን ብቻ ሲያስቆጥር በምርጥ 11 ውስጥም ቦታ ለማግኘት ተቸግሯል።

እነዚህ ለጀርመናዊው የመጀመሪያዎቹ ቀናት ናቸው እናም ይህ የሽግግር ዓመት ብቻ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ። ደግሞም በሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ አሸናፊውን ግብም አስቆጥሯል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football