Connect with us
Express news


Football

ትንሹ ብሬንትፎርድ አርሰናልን ቀጥቷል!

Little Brentford Humble Arsenal!
arseblog.news

አዲስ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ብሬንትፎርድ በአርሰናል ላይ ትልቅ ድል በማስመዝገብ የውድድር ዘመናቸውን ጀምረዋል። አርሴናል ትናንት ቀርፋፋ ሆኖ ነበር ያንን ክፍተትም ብሬንትፎርድ ሙሉ በሙሉ ተጠቅሟል!

 ከ 1947 ወዲህ የብሬንትፎርድ የመጀመሪያ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው ፣ በሰርጊ ካኖስ እና ክርስቲያን ኖርጋርድ ግቦች አዲስ ያደገው ቡድን አርሴናልን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

 የቶማስ ፍራንክ ቡድን ከፍተኛ ጥንካሬ እና ጉልበት ያለው ተጭኖ መጫወት እንዲሁም መግባባት ከከፍተኛ ድባብ ጋር ተዳምሮ አርሴናል ገና ከጅምሩ ሲታገል እንዲቆይ አድርጎታል። በርንድ ሌኖ እና በተለይም ፓብሎ ማሪ የተደናገጡ ይመስሉ ነበር።

ድንጋጤው ወደ ካሉም ቻምበርስም የተጋባ በሚመስል ሁኔታ ፣ ብሬንትፎርድ የመአዘን ምት እንዳያገኝ በመፍራት ኳሱን ከመስመር ላይ ወደ አየር ጠለዘው። ኳሱ ሲወርድ የመጣው ወደ ካኖስ ነው ፣ እሱም ቀጥታ የአርሴናሉ ተከላካይ ላይ መታው። በፍጥነት የተመታው ምት በተከላካዩ እግሮች ውስጥ ሲያልፍ ሌኖ ምቱን ለማገድ ምንም ማድረግ አልቻለም።

ብሬንትፎርድ ተጋጣሚዎቻቸውን ወደኋላ አፍነው ይዘዋቸው ነበር እናም በ 30ኛው ደቂቃ መሪነታቸውን በእጥፍ ማሳደግ ይችሉ ነበር። ብራያን ምቤሞ የፕሪሚየር ሊጉን የመጀመሪያ ጨዋታ እያደረገ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ብቃቱ ፣ ጉልበቱ እና ለግብ ያለው አይን የአምስት ዓመት ልምድ ያለው እንዲመስል አድርጎታል! ቤን ኋይትን ጀማሪ እንዲመስል አደርጎ ካንገላታው በኋላ ግን ቸኩሎ ኳሱን መቶት ከማእዘን ውጪ ሆኖበታል።

worldfootballindex.com

 የብሬንትፎርድ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የማደጉ ምክንያት ጀግና ኢቫን ቶኒ በአለሁ ባይ ፣ የድሮ አጥቂዎች አጨዋወት ትናንት ማታ ግብ ባያገባም የለመደ የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋች ነበር የሚመስለው። በአየር ላይ ኳሱ በተከታታይ ወደ እሱ ሲሳብ ነበር። ወደ እግሩ የመጣውንም ኳስ በሚያስፈራ ስኬት እና ፍጥነት ሲዞር እና ሲያቀብል ነበር።

አርሰናልም አዲስ ተጫዋች ነበራቸው ፣ የታመሙትን የፒየር-ኤምሪክ ኦባሜያንግ እና የአሌክሳንደር ላካዜቴ እና እስከሚቀጥለው ወር ድረስ የተጎዳውን ኤዲ ንኬቲያን ቦታ ወስዶ ፎላሪን ባሎን ገብቶ ነበር። በኒው ዮርክ ከተማ ለተወለደው ወጣት የረጅም ጊዜ ተስፋ ከፍተኛ ነው ፣ ነገር ግን በከፍተኛው ሊግ መጀመሪያው ላይ የተሟላ ተጫዋች ሆኖ አልታየም ፣ በሳጥን ውስጥ አንዴ የተሰራበት ጥፋት ከሌላ ዳኛ ቢሆን ፍጹም ቅጣት ምት ያሰጥለት ነበር ትላንት ግን አልሆነለትም።

 በአጠቃላይ ፣ አርሴናል በኤሚል ስሚዝ-ሮው ላይ በጣም ጥገኛ ነበር ፣ ምንም እንኳን የአዲሱ ቁጥር 10 ችሎታ እና ብቃት ሁሉም የምስረታ ኳሶች በ 21 ዓመቱ በኩል ለምን እንደሚያልፉ ለመረዳት ቢያስችልም ማለት ነው። በጨዋታው ክፍተቶችን እየገኘ ነበር እና በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ በአስደናቂ ሁኔታ ኳስ ገፍቶ ሄዶ ፣ ነገር ግን ብሬንትፎርዶች ወደ ግብ የሚወስደውን መንገድ ሲያጨናንቁበት በቀጥታ በበረኛው ዳቪድ ራያ ላይ ኳሱን መቶታል።

nevermanagealone.com

 የቡካዮ ሳካ መግባት ለስሚዝ ሮው እና ለኪራን ቲርኒ የሚያጫውታቸው ሰው ሰቷቸዋል። እነሱ እና አዲሱ ፈራሚ ሳምቢ ሎኮንጋ ፈጣን ፣ በሩጫቸው ቀጥታ እና እድል ፈጣሪ ነበሩ ፣ የቡድን ጓደኞቻቸው ያልነበሩትን ማለት ነው። ኋይት ጫናውን ተቋቁሞ ኳሱን ወደ ሳካ በመግፋት የተጀመረው የፍሰት እንቅስቃሴ በመጨረሻ ግብ መሆን ቢኖርበትም የቲየርኒ ምት ወደ ውጭ ወጥቷል።

ሁለተኛው አጋማሽ የአርሰናል ነበር። ያው እስኪያጡት ድረስ። የተለመደውን የአርሰናልን ራስ ማስበላት እስኪደግሙት ማለት ነው። ከፊት የነበሩት ሁለት ተከላካዮች የማድስ ሶሬንስን ረጅም ውርወራ ሳቱት። ሌኖ ከፖንቱስ ጃንሰን ጋር ከተፈጠረው ልፊያ እራሱን ማስወጣት አልቻለም። ከዚያ ሁለት የብሬንትፎርድ ተጫዋቾች መስመር ላይ ሆነው ግብ ለማስቆጠር ሲጠብቁ ማንም አላስተዋለም። ክርስትያን ኖርጋርድ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ቡድኑን የመጀመሪያዎቹን የከፍተኛ ሊግ ነጥቦቻቸው እንዲያገኙ ያደረገው።

france.tenzica.com/

ይህ ለብሬንትፎርድ በጣም አዲስ ቢሆንም ፣ ለአርሴናል ግን በጣም የተለመደ ነበር። ማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲን ከዓለም አቀፉ ዕረፍት በፊት ስለሚጫወቱ ደግሞ የሆነ ነገር ለ ሚኬል አርቴታ መለወጥ አለበት!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football