Connect with us
Express news


Football

በጣሊያኑ ሴሪ ኤ ውስጥ ለሚገኙ ምርጥ ቡድኖች ሊፎካከሩ የሚችሉ ቡድኖች አሉ?

Can any of the Chasing Pack trouble the Big Clubs in Italy’s Serie A?
thelaziali.com

ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ አንዳቸው ወደ ምርጥ 4 ገብተው ለሻምፒዮንስ ሊግ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ? በዚህ የውድድር ዘመን ያልተጠበቀ ውጤት ሊያሳዩን ይችላሉ?

የ2020/1 የውድድር ዘመን በሁለቱም የሚላን ቡድኖች (ኤሲ እና ኢንተር) የበላይነት ነበር የተጠናቀቀው። በመጨረሻም ኢንተሮች በአስደናቂ የ12 ነጥብ ልዩነት ዋንጫውን አስተዋል። አታላንታ ከጁቬንቱስ ጋር በነጥብ እኩል ሆነው የውድድር ዘመኑ በ3ኛ ደረጃ አጠናቋል። አታላንታ በ 2017-18 የውድድር ዘመን 7 ኛ ደረጃ ይዘው ነበር የጨረሱት ፣ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በደረጃው ሰንጠረዥ አናት አካባቢ ሆነህ መጨረስ ልምድ አድርገው ቆይተዋል። ከእነዚህ ክለቦች ውስጥ አንዳቸውም ተመሳሳይ ሽግግር አድርገው ከትላልቅ ቡድኖቹ ተርታ ሊያስቀምጥ የሚችል አቅም አላቸው?

ዩሲ ሳምፕዶርያ

footballticket.net

ሳምፕዶሪያ የ 2019/20 አስቸጋሪ የውድድር ዘመን መቋቋም ነበረበት ነገር ግን 2020/21 የሊጉሪያን ቡድን የበለጠ የተረጋጋበት ወቅት ነበር። በ 9 ኛ ደረጃ ሆኖ ቢያጠናቀቁም አንዳንድ የሴሪአ ጠንካራ ቡድኖችን ማሸነፍ እንደሚችሉ አሳይተዋል። ሳምፕዶሪያ የውድድር ዘመኑን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችዎች ቢሸነፉም ፊዮረንቲና ፣ ላዚዮ እና አታላንታን በማሸነፍ ስድስተኛ ደረጃን መያዝ ችለው ነበር።

ሄላስ ቬሮና እና በክሮተን ላይ የተገኙት ድሎች መረጋጋት እስኪፈጥርላቸው ድረስ ጄኖዎቹ በቀጣዮቹ ስድስት ጨዋታዎች ያለ ምንም ድል በመጓዙ በደረጃ ሠንጠረዡ ወደ 15 ኛ ዝቅ ብለው ነበር። አዲሱ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲአቨርሳ የቀድሞ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ የጀመሩትን የከፍታ ጉዞ ለመቀጠል ተስፋ አድርጓል። ራኒዬሪም ቀደም ሲል በሌስተር እንዳደረገው ሁሉ ሳምፖዶሪያን በፊት ከነበረው የሚበልጥ ቡድን አድርጎታል። ዳአቨርሳ በዚህ ዓመት ሳምፕዶሪያን በደረጃ ሰንጠረዡ ከፍ ለማድረግ ከፈለጉ ተመሳሳይ ስራ ይጠበቅበታል!

ኤኤስ ሮማ

asroma.com

በተለምዶ ትልቅ ክለብ ሮማ ከ 2017/18 የውድድር ዘመን ጀምሮ ከከፍተኛዎቹ 4 ውስጥ ወጥቷል። በ 2020/21 የመጀመሪያ አጋማሽ የውድድር ዘመን ያሳዩት ጠንካራ አቋም ደጋፊዎቻቸው ወደ ቻምፒዮንስ ሊጉ እንመለሳለን የሚል ሃሳብ እንዲፈጠርባቸው አድርጓል ፣ አንዳንድ ጥሩ አመለካከት ያላቸው ‹ኩርቫ ሱዶች› ደግሞ ሮማ ከትላልቅ ቡድኖች ባሳየው አሪፍ አቋም ለዋንጫ እንዲያልሙ አድርጓል ።

በመጨረሻም በውድድር ዘመኑ ሁለተኛ አጋማሽ ያሳዩት መጥፎ አቋም ዋጋ አስከፍሏቸዋል ፣ ትኩረታቸውም ሙሉ ለሙሉ ከሰሪኤው ወጥቶ ወደ አውሮፓ ሊግ እንዲሆን አድርጓል። በአውሮፓ ግማሽ ፍጻሜዎች ሲጫወቱ ፣ በማንችስተር ዩናይትድ የደረሳቸው የ6-2 የመጀመሪያ ዙር ሽንፈት ለመቀልበስ በመልሱ ጨዋታ ያሳዩት አሪፍ አቋም እንኳን በቂ አልነበረም።

በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጆሴ ሞሪንሆ ወደ ሴሪ ኤ ተመልሰው ሮማን እንደገና የዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን አድርገው ለመቅረጽ በሚሰሩበት ጊዜ ሁሉም ዓይኖች በ ‹ስፔሻል ዋን› ላይ ያርፋሉ።

ዩዲኒዜ

ተስፋ አስቆራጭ የ 2019/20 የውድድር ዘመንን ተከትሎ ሉካ ጎቲ ቀደም ሲል ብዙም ፍላጎት ያልነበረውን ሚና ወስዶ በነሐሴ 2020 የአንድ ዓመት ማራዘሚያ ፊርማ ማኖሩን አጋርቷል እናም በቡድኑ ውስጥ የሚቆይ ከሆነ የሚታይ ይሆናል።

ሆኖም ፣ በቁልፍ ጨዋታዎች ፣ ጎቲ መመሪያዎቹን እና ታክቲኮችን በቦታው ላይ ስኬታማ ነበሩ ፣ እና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ‹ፍሩላኒዎች› በ 10 ጨዋታዎች ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ሽንፈት አይተው ነበር። ከነዚህ ጨዋታቶች አራቱ በድል ነብር የተጠናቀቁት። በዚያን ጊዜ ከኤሲ ሚላ፣ ኢንተር እና ከአታላንታ ጋርም አቻ ተለያይተው ነበር።ውጤቱም ብዙውን ጊዜ በምርጥ 4 ደረጃ ላይ ባሉ ቡድኖች እንደማይደናገጡ ያሳያል። ዩዲኒዜ ባለፈው ዓመት ማሳካት የቻሉት የ13 ኛ ደረጃን ለማሻሻል በዚህ የውድድር ዘመን ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት አለባቸው።

ጄንዋ ሲኤፍሲ

africa.espn.com

በወራጅ ቀጠናው ዝርዝር ውስጥ ፣ ጄንዋ በ2019/20 የውድድር ዘመን መጥፎ የመውረድ አገዳ ከተጋረጠባቸው በኋላ ነበር ወደ 2020/21 የውድድር ዘመን ያመሩት ። ዋና አሰልጣኝ ዴቪድ ባልላዲኒ በታህሳስ 2020 ወደ ክለቡ የተመለሰ ሲሆን ቡድኑ 11 ኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ አድርጓል።

ጄንዋ በመካከለኛው የደረጃ ሰንጠረዥ ለመቀመጥ 11 ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ ፣ 12ቱ ላይ  አቻ ወጥቶ 16 ጨዋታዎችን ተሸንፏል። ጄንዋ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እያመራ ያለ ቡድን ይመስላል። ማን ያውቃል? ምናልባት በ 2020/1 የውድድር ዘመን በሴሪ ኤ ውስጥ ልዩ ነገር ሊያያሳዩን ይችሉ ይሆናል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football