Connect with us
Express news


Football

የአውሮፓ እግር ኳስ ማጠቃለያ!

European Football Round-Up!
cbssports.com

ትናንት ምሽት 1 ኛ ዙር የቻምፒየንስ ሊግ (ዩ.ሲ.ኤል.) እና የአውሮፓ ሊግ (ዩ.ኢ.ኤል.) የማጣሪያ ጨዋታዎች ተካሂደዋል። ውጤቱን እና ምን እንደተፈጠረ እንመልከት!

የዩ.ሲ.ኤል. ጥሎ – ማለፎች

ቤነፊካ 2 – ፒኤስቪ ኢንድሆቨን 1

ራፋ ሲልቫ ለባለሜዳዎቹ የመጀመርያው ግብ አስቆጠረ። ከዚያ ጁሊያን ዌግል ሁለተኛውን ግብ ከመረብ አሳርፎ መሪነቱ እጥፍ አድርጎታል። በሁለተኛው አጋማሽ ኮዲ ጋክፖ ባስቆጠራት አንድ ግብ ቤኔፊካዎች 1 የግብ ልዩነት ይዘው ወደ ኢንድሆቨን እንዲጓዙ አድርጓል።

ማልሞ ኤፍ.ኤፍ. 2 – ሉዶጎሬትስ 0

ከቬልክጆ ቢርማንሴቪች እና ከጆ ኢንጅ በርጌት የተገኙ ሁለት ግቦች ማልሞ የቡልጋሪያውን ሉዶጎሬትን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት እንዲያሸንፍ አስችሎታል። ማልሞዎች ወደ ቡልጋሪያ ተጉዘው በ2 ኛው ዙር ሥራቸውን መጨረስ አለባቸው።

ያንግ ቦይስ 3 – ፌረንክቫሮሲ ቲሲ 2

idnes.cz

የምሽቱ በጣም አስደሳች ጨዋታ የስዊዘርላንዱ ያንግ ቦይስ የሃንጋሪውን ፌረንቫሮሲን ያስተናገደበት ጨዋታ ሲሆን ፣ እጅግ በጣም ጠባብ በሆነ ውጤት አሸንፏል። ሆኖም ስልቫን ሄፍቲም በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል። ስለዚህም የመልስ ጨዋታው አስደሳች ሊሆን ይችላል!

የዩ.ኢ.ኤል. ጥሎ – ማለፎች

ሴልቲክ 2 – ኤዝ አልካማር 0

ሴልቲክ ትናንት ምሽት ብቸኛውን የ ዩ.ኢ.ኤል. ጥሎ ማለፍ ጨዋታ 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ፣ ለመልሱ ጨዋታ ወደ ሆላንድ የሚያቀኑት በሙሉ መተማመን ነው!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football