Connect with us
Express news


Football

የጣሊያን ሴሪ አ ከፍተኛ ክለቦች ዘንድሮም የበላይነቱን ይቀጥሉ ይሆን?

Will the Top Clubs of Italy’s Serie A Continue to Dominate this Year?
https://www.news18.com/

ሁለቱ የሚላን ክለቦች ፣ ጁቬንቱስ እና አታላንታ ባለፈው የውድድር ዘመን በሴሪ ኤ የምርጥ 4 ቦታዎችን ይዘዋል። በዚህ ወቅት ተመሳሳይ ይሆናል ወይስ ሌሎች ክለቦች ወደ ጥሩ ብር የሚገኝበት ሻምፒዮንስ ሊግ ሊገቡ ይችላሉ?

ያለፈው አመት ምርጥ 4

ኢንተር ሚላን

ቡድኑ በጣም ብዙ አሠልጣኞችን እንዲቀያይር ካደረገው የ11 ዓመታት ዋንጫ ጥማት በኋላ በመጨረሻ ኢንተር የሴሪአ ዋንጫን አሸነፈ። ብዙዎች የውድድር ዘመኑ ከመጀመሩ በፊት የአንቶኒዮ ኮንቴን ቡድን እንደ ስኩዴቶ ተፎካካሪዎች ቢጠብቁም ፣ አራት ጨዋታዎች እየቀሩ ያሸንፋሉ ማለት ግን የማይጠበቅ ነገር ነበር።

አጀማመራቸውም ምርጥ የሚባል አልነበረም ከመጀመሪያዎቹ ሰባት የሴሪ አ ውድድሮች ሶስቱን ብቻ ነበር ያሸነፉት ከዛ ተነስተው ዋንጫ ማሳካታቸውም የበለጠ አስደናቂ ነው። ያ አቋም ለዩኤስኤኤል እድገታቸውም እንቅፋት ሆኗል ፣ ከሻክታር ዶኔትስክ ጋር 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ከወጡ በኋላ የምድቡ መጨረሻ ሆነው አጠናቀዋል ።

ሆኖም ያ ጉዞ መቋረጥ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በሴሪ አ ላይ እንዲያተኩር አረገው ፣ ጣሊያናዊው ኢንተር ለምን በግንቦት 2019 በጣሊያን ውስጥ ከፍተኛ ደመወዝ ያለው አሰልጣኝ እንዳደረገው አሳይቷል።

ኢንተር ሮሜሉ ሉካኩን ለቸልሲ በ 135 ሚሊዮን ዶላር ሸጦታል። ባለፈው የውድድር ዘመን ተሰጥኦ ያለው ቤልጄማዊ አጥቂ 24 የሴሪ አ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። እነዚያ በሴሪ ኤ ውስጥ ትልቅ ቁጥሮች ናቸው እና ያለሱ ወደዚህ አመት እንደመግባታቸው እንደበፊቱ የማጥቃት ስጋት ሆነው ይቀጥሉ ይሆን የሚለውን ማየት አስደሳች ይሆናል።

ኤሲ ሚላን

pelisterfc.com

የኤሲ ሚላን ደጋፊዎች በ 2020/2021 የውድድር አመታቸው አጨራረስ በእርግጠኝነት ሊደሰቱ ይችላሉ ፣ ግን አሁንም ቢሆን አትጋቢ እንዳልነበር የሚሰማቸው ሊኖሩ ይችላሉ።

የበጋ ሻምፒዮን ሲሆኑ እና እስከ ጥር መጀመሪያ ድረስ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፉ ሲሄዱ ፣ በአመቱ በመጨረሻው ቀን ምርጥ-አራተኛ ቦታን ማረጋገጥ ብቻ ይሆናል መጨረሻው ብለው አይጠብቁም።

ኤሲ ሚላን እና ደጋፊዎቻቸው በውድድር አመቱ መጀመሪያ አንድ ሰው ሁለተኛ ደረጃ ይሰጣቹ ቢላቸው ለነሱ በጣም ምርጥ ነገር ሆኖ ነበር ሚታያቸው። ሚላን ከ 2013/14 የውድድር ዘመን ጀምሮ በዩኤሲኤል ውስጥ አልታየም። ውድድሩን ሰባት ጊዜ ላሸነፈ ቡድን ፣ ያ በጣም ረጅም ጊዜ ነው።

በኤሲ ሚላን እንደገና መገንባት አሁንም እየተካሄደ ነው ፣ ነገር ግን በአውሮፓ ሻምፒዮና የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች ግብ ጠባቂው ጂያንሉጂ ዶናሩማ እና በፈጠራ ኃይሉ ምናቀው ሃካን ካልሀኖግሉ ለቆ መውጣት በዚያ ሂደት ውስጥ ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸዋል። የዝውውር መስኮት እንቅስቃሴያቸውም ለመጪው አመት ቡድኑን የማጠናከር አዝማምያ የለውም።

አታላንታ ቢሲ

ከእንግዲህ ምኞት ብቻ አይደለም። አታላንታ ለሦስተኛው ተከታታይ የውድድር ዘመን በሴሪ አ ሦስተኛ ሆኖ አጠናቋል ፣ እናም አሁን ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ በጣሊያን ምርጥ አራት ውስጥ አጠናቋል ፣ በአሰልጣኝ ጂያን ፒሮ ጋስፔሪ ሥር በአውሮፓ እግር ኳስ በአምስት የውድድር አመቶች ለአምስተኛ ጊዜ ተሳታፊ ሆነዋል ።

ካፒቴኑ ፓዉ ጎሜዝ በጃንዋሪ ከቤርጋሞ ሲወጣ እሱ ምናልባት ሊተካ ይችላል ብሎ መገመት ከባድ ነበር ፣ ግን እንዲህ አይነት ነገሮች በአታላንታ የተለመዱ ናቸው። ቀደም ሲል በጋስፔሪኒ ስር ኮከብ ተጫዋቾችን አጥተዋል – ፍራንክ ኬሴ ፣ ሊዮናርዶ እስፒናዞላ ፣ ሮቤርቶ ጋግሊዲኒ ፣ አንድሪያ ኮንቲ ፣ ብራያን ክሪስታን ፣ ማቲያ ካልዳ ፣ ጂያንሉካ ማንቺኒ ፣ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ፣ ግን እነሱ ሁል ጊዜ ወድቀው አይወድቁም። ያ እንዳለ ሆኖ ግን ፣ ከዚህ በፊት እንደ ጎሜዝ አስፈላጊ የሆነን ሰው አላጡም ነበር።

አንዳንድ ጊዜ የእሱ አለመኖር ሲያስታውቅ ነበር ፣ ግን ብዙ ጊዜ አይደለም። አታላንታ ያለ በፊቱ 10 ቁጥራቸው የተሻሉ ቡድን ነበሩ ማለት ይከብዳል ፣ ነገር ግን ያለ እሱ ከአንድ የውድድር ዘመን ሲያሳልፉም በጣም የከፋ አልሆኑም እናም ይህ በጌዊስ ስታዲየም ውስጥ ጋስፔሪኒ እየሰሩት ላለው ጥሩ ሥራ ማረጋገጫ ነው።

የአታላንታ ዋና ቡድን ለዚህ አመት እንዳለ ይቆያል እና ለዚህ የውድድር ዘመንም ጠንካራ ይመስላሉ። ሌላ የምርት 4 አጨራረስ ሙሉ በሙሉ የሚቻል ይመስላል።

ጁቬንቱስ

cnn.com

በ 2020/21 የውድድር ዘመን መጀመሪያ ላይ ፣ የጁቬንቱስ ደጋፊዎች ታሪካዊ አሥረኛ ተከታታይ የሴሪ አ ዋንጫን ከፍ ለማድረግ ህልም ነበራቸው ፣ ግን በመጨረሻ ቀን እስኪተርፉ ድረስ ለሻምፒዮንስ ሊግ እንኳን ብቁ አለመሆን እድል ነበራቸው እናም ያ በውድድር አመቱ ብዙ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን እንዲያሳልፉ አርጓል።

ከአውሮፓ ምርጥ ፉክክር ውድድር አሳፋሪ የመጨረሻ -16 ሽንፈትን በፖርቶ እጅ ሲከናነቡ እና ወደ ሱፐር ሊግ ለመገንጠል በሚሞክሩበት ጊዜም ሳይሳካላቸው የመቅረቱ ውርደት ሲጨመር ፣ 2020/21ን ከቱሪን ግዙፉ ቡድን ጋር የተገናኘ እያንዳንዱ ሰው መርሳት የሚፈልገው ውቅት አርጎታል።

ሆኖም በኮፓ ኢታሊያ ፍፃሜ ላይ በአታላንታ ላይ ያሳኩት ድል ቢያንስ ለጁቬንቱስ እና ለጀማሪ አሰልጣኙ አንድሪያ ፒርሎ ወደ መጨረሻው የውድድር ዘመን አካባቢ የሚያስደስት ነገር ሰቷቸዋል። ምንም እንኳን ጁቬንቱስ ትንሽ ቆይቶ ፒርሎን ካሰናበተው በኋላ ያ ደስታ በአጭሩ ቢቀጭም።

ጁቬንቱስ ከ 10 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስኩዴቶውን ከማስጠበቅ ይልቅ ወደ ሴሪ አው የውድድር ዘመን እንደአዲስ ለማሸነፍ አልሞ ይገባል። ይህን ለማድረግ ተስፋ ሲያደርጉ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ ወደ አሰልጣኝነት ቦታቸው ተመልሰዋል ፣ ክለቡ አንድሪያን ፒርሎ ከአንድ የውድድር ዘመን በኋላ ብቻ ካሰናበተ በኋላ ማለት ነው። ጁቬንቱስ አልቫሮ ሞራታን ከአትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት እና ካዮ ጆርጌን ከብራዚሉ ክለብ ሳንቶስ በ 3 ሚሊዮን ዩሮ አምጥቷል። እነዚህ ሁለቱም ተጫዋቾች አጥቂዎች ናቸው እናም እኚህ ተጫዋቾች ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር ከቻሉ ጁቬንቱስ በዚህ ወቅት ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ይችላል።

ተቀናቃኞች

footballticket.net

ካለፈው የውድድር ዘመን ምርጥ 4 ውጭ ሲንመለከት ፣ የትኞቹ ክለቦች በዚህ አመት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ? ናፖሊ ፣ ሮማ እና ምናልባትም ላዚዮ እንኳን ዕድል ሊኖራቸው ይችላል። እዚህ የሚያስደንቀው ነገር እነዚህ ቡድኖች በተጫዋቾች ረገድ ትልቅ ማሻሻያ አልነበራቸውም ፣ ግን እንደ ሮማ ፣ ላዚዮ እና ናፖሊ የመሳሰሉት የአሰልጣኝ ለውጦች አድርገዋል ያም ደግሞ ኬሚስትሪውን ፣ ዘይቤውን እና የቡድኖቹን የመጨረሻ ደረጃ ይለውጣል። ስለዚህ በ 2021/22 ወቅት በሴሪ አ ውስጥ ለስኩዴቶ እና ለ ዩሲኤል ቦታዎች በጠረጴዛው አናት ላይ አስደሳች ፉክክር ምናይ ይመስላል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football