Connect with us
Express news


Football

ስፐርሶች በፓኮስ ዴ ፌሬራ ተሸነፉ!

Spurs Stunned by Pacos de Ferreira!
thetimes.co.uk

የሰሜን ለንደኑ ቡድን በኮንፈረንስ ካፕ በፖርቹጋሉ ትንሽ ቡድን 1 ለ 0 ሽንፈት ደርሶበታል ይህም ስፐርሶች በአዲሱ አሰልጣኛቸው ስር የመጀመሪያ ሽንፈታቸው ሆኗል!

ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶ ጨዋታው እንዳለቀ ከሜዳው በሚወጣበት ጊዜ ጭንቅላቱን እና ጢሙን እያሻሸ ሲሆን የሃዘን ስሜትም ይታበት ነበር። ሆኖም በቶተንሃም የመጀመሪያውን የውድድር ሽንፈቱ ሊወስዳባቸው የሚችላቸው ሁለት አዎንታዊ ጎኖች ነበሩ።

አንደኛው አወንታዊ ጎን በለንደኑ ሜዳቸው የሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ ፣ አሰልጣኙ እና ተጫዋቾቹ በመጀመርያው ዙር የሰሩትን ስህተቶች ለማስተካከል ሁለተኛ እድል ይሰጣቸዋል ። ሁለተኛው አወንታዊ ጎን ደግሞ በጽንሰ -ሀሳብ ደረጃ ቢሆንም እንኳን ፣ ካሁን በኋላ ቶተንሃሞች ከዚህ የባሰ አቋም አያሳዩም።

የስፐርስ ደጋፊዎች ማንችስተር ሲቲን ካሸነፉ በኋላ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ነበሩ ፣ ነገር ግን በአውሮፓ የሶስተኛ ደረጃ ቡድኖች ውድድር ፣ የመጀመሪያ-ጨዋታ መሸነፍ በእርግጠኝነት የቡድኑን አቅም መውረድ ያስከትላል!

ኑኖ ‘መሸነፍ የሚወድ ሰው የለም። በጥሩ ሁኔታ አለመጫወት የሚወድ ሰው የለም’። ብሏል።

ጥሩ ስሜት ያለው ነገር ጠፍቷል። ይህ እግር ኳስ ነው ፣ ከፍ ዝቅ ማለት የተለመደ ነገር ነው። ወደ አቋማችን መመለስ አለብን እናም ይህ ነው ማድረግ ያለባቸው።

eurosport.com

ስፓርሶች በአውሮፓ የደረሳቸው አደጋ አስታዋሽ ይፈልጋሉ? ባለፈው አመት ቶተንሃም በቡልጋሪያው ሎኮሞቲቭ ፕሎቭዲቭ ከኤውሮፓ ሊግ የማጣሪያ ውድድር ውጪ ሊሆን 10 ደቂቃ ብቻ ቀርቶት ነበር። በዚያን ምሽት ሃሪ ኬን እና ታንጉይ ንዶምቤሌ ነበሩ ከውድድሩ ውጪ እንዳይሆኑ ያደረጓቸው ፣ እነዚህ ተጫዋቾች ደግሞ በጨዋታው አልተሰለፉም ነበር ፣ ለዚህም ይመስላል ማንም ሊያድናቸው ያልቻለው! እውነቱ ይህ ቢሆንም አሰልጣኝ ኑኖ ታዳጊ ተጫዋቾ ይዞ ነበር ወደ ጨዋታው ያቀናው ፣ ታዳጊዎቹም ሙሉ ቱክረታቸው ጨዋታው ላይ አላደረጉም ነበር ።

የቶተንሃም ቀጣዩ ትውልድ በግድየለሽነት የተሞላ እና በግራ መጋባት የታመሱ ይመስሉ ነበር። ከዚያም ትልቅ መደናገጥ ተፈጠረባቸው እና ሉካስ ሲልቫ ከእረፍት በፊት መላውን የቶተንሃም ቡድን ያፈዘዘ ምርጥ ግብ አስቆጥሯል!

the-sun.com

የቶተንሃም ደጋፊዎች በሳምንት ውስጥ ሁለት ጊዜ ያለ ኬን ሕይወት ምን እንደሚመስል ተመልክተዋል። ሙሉ በሙሉ የማይመሳሰሉ ሁለት ጨዋታዎች። አሁን ኑኖ ሃያ ሁለት ተጫዋቾች ማየት ችሏል። ሁለት በጣም የተለያዩ ውጤቶች!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football