Connect with us
Express news


Fighting

ነገ የዩ.ኤፍ.ሲ. ፍልሚያ ምሽት ነው! ካኖኒየር ከጋስትሉም! በጣም የሚጠበቅ ፍልሚያ

It’s UFC Fight Night Tomorrow! Cannonier vs. Gastelum! A Highly Anticipated Battle
bolavip.com

ቅዳሜ ምሽት “በአስርት ዓመታት ውስጥ በጣም የሚጠበቀው የ የዩ.ኤፍ.ሲ. ፍልሚያ” ተብሎ በተሰየመው ጃሬድ ካኖኒየር (13-5) ከ ከኬልቪን ጋስትሉም (17-7) ጋር ይፋለማሉ።

ካኖኒየር ጥቅምት 2014 ዩ.ኤፍ.ሲ.ን ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ በሶስት የተለያዩ የክብደት ክፍሎች እንደተወዳደረ መሆኑን ጋስትሉም ያውቃል። ወደ ቀላል ሚዛን ከመውረዱ በፊት በከባድ ሚዛን ሻምፒዮና ብዙ ድሎችን ማሳካት ችሏል ።

https://talksport.com/

ይህ ለጋስትሉም ይጠቅመዋል? ካኖኒየር በዊታከር ከመሸነፉ በፊት ፤ ዴቪድ ብራንች ፣ አንደርሰን ሲልቫ እና ጃክ ሄርማንሰንን በዝረራ (ቲ.ኬ.ኦ.) አሸንፏል። ዳላሳዊው የ 37 ዓመት ተፋላሚ ብራንች እና ሄርማንሰን በማሸነፍ ክብር አግኝቷል ፣ የቀድመው የዩ.ኤፍ.ሲ. መካከለኛ የክብደት ሚዛን ሻምፒዮና አንደርሰን ሲልቫን ፍልሚያዉን መቀጠል ቢፈልግም በመጀመርያ ዙር እንዳይነሳ አድግሮ አሸንፎታል ።

ጋስትሉም እንዲሁ በ ዩ.ኤፍ.ሲ. የውድድር ሂወቱ ብዙ ጊዜ የክብደት ክፍሉን ቀይሯል ፣ በ 2013 ወደ ዌልተርዌይት ሚዛን በፍጥነት ከመሸጋገሩ በፊት በመካከለኛ የክብደት ሚዛን ተወዳድሯል ፣ ከዚያም በ 2016 ወደ የመጀመሪያው የክብደት ሚዛኑ ተመልሷል። የ29 አመቱ ተፋላሚ ፣ ሚያዝያ 2013 ዩራህ ሃልን በውሳኔ-ክፍፍል (ስፕሊት – ዲዝዥን) ባሸነፈበት ፍልሚያ የመጀመርያ የአልትሜት ፋይተር ሲዝን 17 ተሳትፎዉን አድርጓል።

https://www.ufcespanol.com/

የሳን ጆሴ ተወላጅ ፣ ጋስተሉም በሰኔ 4 ከሜዳ የወጣውን ፓውሎ ኮስታን በመተካት ካኖኒየርን በሚፋለምበት ሰአት ነገሮችን መቀየር ይፈልጋል። ጋትስሉም ከመጨረቻዎቹ አምስት ፍልሚያዎች በአራቱም የተሸነፈ ሲሆን ይህም ሚያዝያ 2019 በእስራእል አዲሳያን በሙሉ ድምፅ (አንናሚዮስ ዲዝዥን) ሽንፈት ሲያስተናግድ ነበር የሽንፈት ጉዞውን የጀመረው። ክብሩን እንደገና መልሶ ማግኘት ይችላል? ጊዜ ብቻ የሚመልሰው ይሆናል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Fighting