Connect with us
Express news


Football

ኤልዶር ሾሞሮዶቭ በቱርክ ትራብዞንስፖር ላይ ሮማ የ 2 ለ 1 ድልን እንዲያገኝ ያስቻለውን ግብ አስቆጠረ!

Eldor Shomurodov Scores Winning Goal to Give Roma a 2-1 Victory in Turkey against Trabzonspor!
star.com.tr

በጆዜ ሞሪኒሆ የመጀመሪያ የውድድር ጨዋታ ላይ ‘ዘ ስፔሻል ዋን’ በሮም ወደሚደረገው ሁለተኛው ዙር ጨዋታ የ 1 የግብ ብልጫን ይዞ ይገባል። ታዲያ ምን ተፈጠረ?

የመጀመሪያው አጋማሽ የተጀመረው በሮማ የክንፍ ተከላካዮች ከመሃል ተከላካዮች ጋር መስማማት ላይ ያተኮረ በመሆኑ በትራብዞንስፖር ላይ ምንም ጫና ሳይኖር ቱርኮች የጨዋታዎቹን የመጀመሪያ 15 ደቂቃዎች በበላይነት መቆጣጠር ችለዋል። ትራብዞንስፖር እንደልብ መርጦ ለማቀበል ብዙ ጊዜ እና ቦታ ነበረው ነገር ግን ትክክለኛውን ማግኘት አልቻሉም ፣ ስለሆነም ሮማ ትንሽ ወደ ጨዋታው መግባት ጀመሩ።

የአጋማሹ የመጨረሻ እንቅስቃሴ ትራብዞንስፖር በሬክ ካርርስዶር ዙሪያ 1-2 ተቀባብሎ ለማለፍ ሲሞክር ነበር ፣ ነገር ግን ዳኛው ግማሹን ለማጠናቀቅ ፊሽካውን ከመነፋቱ በፊት እንቅስቃሴው ከጨዋታ ውጪ ተብሏል። በአጠቃላይ ፣ የቱርኩ ቡድን ግማሹን ተቆጣጥሮ ነበር ማለት ይቻላል ፣ ግን ሁለቱም ወገኖች በዚህ ባለ ሁለት ዙር ውድድር እስካሁን ሙሉ ብቃታቸውን አላሳዩም።

በሁለተኛው አጋማሽ ፣ አናስታሲዮስን “ታሶስ” ባካሴታስን በግማሽ መስመር አቅራቢያ ከነጠቁ በኋላ ፣ በግራ መስመር በኩል ኳሷን ወደ ሄንሪክ ሚኪታሪያን በማሻገር ድንቅ መልሶ ማጥቃት ፈጠሩ ፣ ትራብዞንስፖር በቀላሉ በሰዓቱ ማገገም አልቻለም እና ሚኪታሪያን በረጅሙ ወደ ክፍቱ የትራብዞንስፖር ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ያሻገረውን ኳስ በ 55 ኛው ደቂቃ ላይ ሎሬዞ ፔሌግሪኒ አስቆጠረው።

ፔሌግሪኒ ከቅርብ ርቀት አስቆጥሮ ሮማ 1-0 ሲመራ ወደ ግማሽ ሰዓት አካባቢ በጨዋታው ቀርቶ ነበር። በነዚያ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት ተጨማሪ ግቦች ተቆጥረዋል። መጀመሪያ ለትራብዞንስፖር በ 64 ኛው ደቂቃ አንድሪያስ ኮርኔሊየስ በግንባሩ ገጭቶ አንድ ጎል ቢያስቆጥርም ማሸነፊያው ግብ በ 81 ኛው ደቂቃ በኤልዶር ሾሞሮዶቭ ተቆጥሮ ሞሮኒሆ በአንፃራዊ ሁኔታ ደስተኛ ሰው እንዲሆን አስችሎታል ፣ የ ሁለተኛ ዙሩን ጨዋታም በሜዳው የ 1 ግብ ብልጫ ይዞ ሚጫወት ይሆናል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football