Connect with us
Express news


Football

6 ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ ሌቫንቴ ዩድ ከሪያል ማድሪድ ጋር በሜዳው አቻ ወቷል!

6 Goal Thriller as Levante UD Hold Real Madrid CF at Home!
skysports.com

የጋሬዝ ቤል ከ 2019 በኋላ የመጀመሪያ የላሊጋ ግብ እና ተከላካይ ተጫዋች ግብ ጠባቂ ሆኖ መጫወቱ በዚህ አስደሳች ጨዋታ ከተፈጠሩ ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው።

ሪያል ማድሪድ ከመመራት ተነስቶ በቪኒሺየስ ጁኒየር 2 ግቦች ከሊቫንቴ ጋር እሁድ ምሽት 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ማድሪድ በመልሶ ማጥቃት ከሄዱ በኋላ ካሪም ቤንዜማ በፍጹም ቅጣት ምት አካባቢው ጠርዝ ላይ ኳሱን መልሶ ለጋሬዝ ቤል ካቀበለው በኋላ ውድያው መቶ ከመረብ በማሳረፍ ለማድሪድ መሪነቱን ሰጥቷል።

ከሌቫንቴ ትንሽ ብልህ የሆነ ቅብብል ጨዋታው ከቤል ጎል በኋላ በተጀመረ በሰከንዶች ውስጥ አቻ ማድረግ ችለዋል ፣ ሮጀር ማርቲ ነው ከማድሪዱ ግብ ጠባቂ ቲባው ኩርቱዋስን 10 ያርድ ላይ ተገናኝቶ ያስቆጠረው ።

remonews.com

ሌቫንቴ ብዙም ሳይቆይ ጆሴ ካምፓና በቀኝ በኩል በተሻማለት ኳስ እንደገና ጎል አስቆጥሮ 2 ለ 1 መምራት ችሏል።

የሪያል አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ከመጀመሪያው 45 ደቂቃዎች በኋላ በቡድናቸው ንቃት መቀነስ እጅግ ሲናደዱ ነበር።

“ሁሉም ነገር በቁጥጥራችን ስር ነበረ ነገር ግን በሁለተኛው አጋማሽ በጣም ለሰለስን ፣ ከሪያል ማድሪድ የምትጠብቀው ይህ አይደለም። ዛሬ 2 ነጥቦችን ጥለናል።” ብሏል ጣልያናዊው አሰልጣኝ

ተቀያሪው ቪኒሲየስ ጁኒየር ከካሴሚሮ የተሻገረለትን ኳስ ተረጋግቶ በማስቆጠር ከ 70 ደቂቃዎች በኋላ ሪያልን አቻ ማድረግ ችሏል።

managingmadrid.com

ሆኖም ሊቫንቴ ብዙም ሳይቆይ ሮበር ከቅጣት ምት ሶስተኛ ግባቸውን አስቆጥሮ መሪነቱን እንደገና ተቀበለ አራተኛ ሊሆን የሚችል ጎልም ማእዘኑን ገጭቶ ወቶባቸዋል።

ቪኒሲየስ ግብ ሲያስቆጥር ጨዋታው መልሶ 3 ለ 3 ሆኗል ፣ ወድያውም አይተር ፈርናንዴዝ በቪኒሲየስ ላይ በሰራው ጥፋት ቀጥታ ቀይ አይቷል።

የፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ የመጨረሻውን ቅያሪ ካደረጉ ከአንድ ደቂቃ በኋላ መሆኑ ለሌቫንቴ አጉል ነገር ነበር ፣ ግን እንደ እድል ሆኖ ፣ ሪያል በተጨማሪ 6 ደቂቃዎች ውስጥ የሮቤን ቬዞን በረኛነት መጠቀም አልቻለም።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football