Connect with us
Express news


Football

የዩሮ ደካማ ተጫዋቾች; በአህጉሩ እግር ኳስ ውስጥ ያልተሳካላቸው ተጫዋቾች!

Eurotrash; Flops in Continental Football!
daznservices.com

ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ውስጥ ያልተሳካላቸው 3 ታላላቅ ተጫዋቾች እንመለከታለን። በ 2020/21 ለምን ከበዳቸው እና በዚህ የውድድር ዘመን ማሻሻል ይችላሉ?

አርተር (ጁቬንቱስ)

ሰኔ 2020 አርተር ለጁቬንቱስ ሲፈርም ማውሪዚዮ ሳሪ አሁንም ዋና አሰልጣኝ ነበር እና ብዙዎች የብራዚላዊው አማካኝ በአሰልጣኙ ታክቲክ ስር እንዴት ሊጫወት እንደሚችል አስገርሟቸዋል። የአሰልጣኙ ለውጥ አርተር እንዲረጋጋ ሊረዳው አይችልም ፣ ነገር ግን ይህ ማለት አንድሪያ ፒርሎ በቱሪን የመጀመሪያ የውድድር ዘመን ለአርተር ውድቀት ተጠያቂ ነው ማለት አይደለም። ቴክኒካዊ ችሎታው ያለ ጥርጥር አሪፍ ነው; ምናልባትም ከጁቬንቱስ የአማካይ ክፍል ውስጥ ከሁሉም የተሻለ አማካይ ሊሆን ይችላል። ችግሩ ፣ ወጥነት ባለው ሁኔታ ብቃቱን ማሳየት አለመቻሉ ነው።

ከሜዳ ውጭ ያለው ባህሪም ተቀባይነት አልነበረውም። በሚያዚያ መጀመሪያ ላይ የዌስተን ማክኬኒ ፓርቲ ተሳታፊዎች ከነበሩት አንዱ ነበር። ለዚህም ጁቬንቱሶች በገንዘብ ሲቀጡት ለ 1 ጨዋታም አግዶታል። ከቤኔቬንቶ ጋር በሚጫወቱበት ሰአት ፣ ኳስ ሊያቀብል በሰራው ስህተት የፍሊፖ ኢንዛጊ ብቸኛውን የሊጉ ሁለተኛ አጋማሽ ድል እንዲያስመዘግቡ ረድቷቸዋል ። አርተር ፒጃኒክን ባካተተ የልውውጥ ስምምነት ጁቬንቱስን ተቀላቀለ ፣ ነገር ግን ጁቬንቱስ በተጫዋቹ ላይ ያስቀመጠው የዋጋ መጠን 80 ሚሊዮን ዩሮ ነበር ፣ ይህም በበጋ ወቅት እሱን ለመሸጥ ችግር እንደፈጠረ ጥርጥር የለውም። አርተር በዚህ የውድድር ዘመን ውስጥ የጁቬንቱስ ተጫዋች ሆኖ ይቆያል።

ቨዳት ሙሪቂ (ላዚዮ)

dailyadvent.com

የኮሶቮ ዓለም አቀፍ ተቻዋች በመስከረም 2020 ለላዚዮ ፊርማውን ሲያሳርፍ ፣ ሲሞን ኢዛጊ መደበኛ አጥቂያቸው ሲሮ ኢሞቢሌ እንዲያርፍ ያግዘዋል የሚል ተስፋ ነበረው። ላዚዮዎች በቻምፒየንስ ሊጉ ውስጥ የተሳተፉ ሲሆን በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ የበለጠ ጥልቀት ያለው ተጫዋች ይፈልጉ ነበር። ሙሪቂ ለላዚዮ የክረምቱ ትልቁ ፈራሚ ነበር። የሮማው ቡድን ስፖርት ዳይሬክተር ኢግሊ ታሬ በጣም ጥቂት የዝውውር ስህተቶች ይሰራል በርግጥም ሙሪቂ አንዱ ስህተት ይመስላል። የ 27 ዓመቱ ተጫዋች በሁሉም ውድድሮች በ 34 ጨዋታዎች 2 ግቦችን ብቻ በማስቆጠር የወጣለትን ዋጋ እንደማይመጥን አሳይቷል ። በሴሪ ኤ ውስጥ 1 ግብ ብቻ ያስቆጠረ ሲሆን ከቱርክ ከመጣ በኋላ ከጣሊያን እግር ኳስ ጋር ለመላመድ በግልፅ ሲቸገር ታይቷል።

ለሴሪአ ጨዋታዎች 8 ጊዜ ብቻ በመጀመርያ 11 የተካተተ በመሆኑ ብዙ ጨዋታዎችን ከመቀመጫ ወንበር በመነሳት ነበር የሚጫወተው። ይህ እንዳለ ሆኖ ፣ ማንኛውንም ዓይነት ተጽዕኖ ማሳደር አልቻለም እና ክለቡ በዋና ከተማው ውስጥ ስላለው የወደፊት ዕጣ ፈንታ አንድ ነገር ማድረግ አለበት! ተጫዋቹ በላዚዮ የሚቆይ ሲሆን በዚህ የውድድር ዘመን የበለጠ ነገር መሥራት ይችል እንደሆነ ማየት አስደሳች ይሆናል።

ሚራለም ፒያኒች (ባርሴሎና)

goal.com

ባርሴሎና ሚራለም ፒያኒችን ከጁቬንቱስ በ 60 ሚሊዮን ዩሮ የመጀመሪያ ክፍያ መግዛቱን ሰኔ 2020 ላይ አስታወቀ። ቦስኒያዊው በሚቀጥለው ዓመት 30 ዓመት እንደሚሆን ግምት ውስጥ በማስገባት ገንዘቡ ከመጠን በላይ ሆኖ ታየ። በመጀመሪያ ፣ ይህ በቀጥታ ወደ ከክለብ ወደ ክለብ ዝውውር ተደርጎ ታይቶ ነበር ፣ ግን ባርሴሎና እና ጁቬንቱሶች ፒያኒችን እና አርተርን የሚያካትት የልውውጥ ስምምነት ነበር ፣ ብራዚላዊውን በተቃራኒው ወደ ቱሪን የሚወስድ (ከላይ ይመልከቱ!)። የዝውውር ክፍያዎች ምናልባት ለሂሳብ አያያዝ ሲባል ተደርገዋል።

በሜዳው ላይ ፒያኒች ወደ ባርሴሎና ምርጥ 11 ለመግባት ተቸግሯል። ባለፈው የውድድር ዘመን ሮናልድ ኮማን በመጀመሪያ በ 2 የመሀል ሜዳ ተጫዋቾች ነበር የሚጫወተው ፣ ሰርጂዮ ቡስኬትስ እና ፍራንኪ ዴ ዮንግ እነዛ ቦታዎች ላይ ሲጫወቱ የነበረ ቢሆንም በቅርብ ፔድሪ ባሳየው ምርጥ አቋም ምክንያት ወደ 4-3-3 ተቀይሯል። በዚህ ለውጥ እንኳን ፒያኒች አሁንም የመጫወት ዕድል ማግኘት አልቻለም እና ካምፕ ኑ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ 6 የላሊጋ ጨዋታዎችን ብቻ ነው የጀመረው። አሁን ለባርሴሎና 0 ግቦችን እና 0 አሲስቶች አለው። በሐምሌ 2021 ፒያኒች ወደ ጁቬንቱስ ይመለሳል የሚል ወሬ ነበር ፣ ግን እስካሁን ይህ አልሆነም እና በባርሴሎና ይቆያል ….. ለአሁን!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football