Connect with us
Express news


Football

ኬን ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ስፓርሶች ወደ ዩኤፋ ኮንፈረንስ ሊግ (ዩ.ሲ.ኤል.) የምድብ ደረጃ እንዲያልፉ አድርጓል!

Kane Scores a Brace to Send Spurs into UEFA Conference League (UCL) Group Stage
eurosport.com

በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በመጀመርያው ዙር በፓኮስ ዴ ፌሬራ የደረሳቸው የ0-1 ሽንፈት በቀለበሱበት ጨዋታ ታታሪው የቶተንሃም ሆትስፐር እና የኢንግሊዙ አጥቂ ወደ ግብ ማግባት አቋሙ ተመልሷል።

የቶተንሃሙ ዋና አሰልጣኝ ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶ ሃሪ ኬን ለክለቡ ቁርጠኛ መሆኑን እና ሁሉም ‘ወደ ፊት የሚሄድበት ጊዜ ነው’ ብለዋል።

ስለ የወደፊቱ ዕጣ ፈንታ ብዙ ግምቶችን ተከትሎ ፣ ኬን ከጨዋታው በፊት ‹በዚህ ክረምት በብድኑ እንደሚቆይ› አስታውቋል።

ወደ ኢ.ሲ.ኤል. የቡድን ደረጃ ለመድረስ በፓኮስ ዴ ፌሬራራ ላይ የመጀመሪያውን ዙር ሽንፈት እንዲቀለብሱ ትልቅ ሞራል ሲሰጣቸው ነበር።

በፖርቱጋል ውስጥ በ1 ኛው ዙር 0-1 በሆነ ውጤት ከተመሩ በኋላ ፣ ኬን በክንፍ በኩል ከብሪያን ጊል የተሻገረለት ኳስ ወደ ግብ በመቀየር ግብ የማስቆጠር ዘመቻዉን አስጀምሯል።

stedmood.ru

የእንግሊዝ ካፒቴን ወደ ግራ የቦታው ክፍል በመምታት አስደናቂ ግብ አስቆጥሮ ለመጀመርያ ጊዜ በድምር ውጤት እንዲመሩ አስችላቸዋል።

በ 70ኛው ደቂቃ ጊዮቫኒ ሌ ሴልሶ የስፐርስን ጥሩ አቋም ያሳረገች ከተጋጨ ፍፁም ቅጣት ምት የተገኘ 3 ኛ ግብ አስቆጥሮ ባለሜዳዎቹ እንዲያሸንፉ አድርጓል ።

football.london

ኬን ለሰሜን ለንደኑ ቡድን 223 ኛ ጎሉን ከመረብ ካሳረፈ በኋላ በ 72 ደቂቃ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል።

ኬን ተቀይሮ በሚወጣበት ሰአት የስፐርስ ደጋፊዎች ስሙን ሲያሰሙ ልክ እንደ የድሮው ጥሩ ዘመን ፊቱ ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር።

ቶተንሃሞች አርብ ከሰዓት 13:30 በሚደረገው እጣ ድልድል ተጋጣሚያቸውን ያውቃሉ።

ስፐርሶች በዚህ የውድድር ዘመን እስካሁን ከ 4 ቱ የመክፈቻ ጨዋታቸው 3 ቱን አሸንፈው ፣ 5 ግብ በማስቆጠር እና በ3 ጨዋታዎች ምንም ሳይቆጠርባቸው በመውጣት የላቀ ብቃት አሳይተዋል።

የስፐርስ አለቃ የመጀመሪያውን የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ለቡድኑ ጥቅም ማዋል ይፈልጋል።

ኑኖ አክለውም “ይህ ውድድር እንድናድግ ያደርገናል” “እኛ የምንፈልገውም ይህ ነው” ብለዋል።

youtube.com

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football