Connect with us
Express news


Tennis

የዩ.ኤስ ኦፕን; በሴቶች በኩል ማን ያሸንፋል እና ማንን አትኩረን እንመልከት?

The US Open; Who will prevail and who to look out for in the Women’s (WTP) section?
bleacherreport.net

የዘንድሮው የዩ.ኤስ. ኦፕን 15 ከዚህ ቀደም አሸናፊ የነበሩ ተጫዋቾችን አካቷል። አንዳቸው እንደገና ማዕረጉን ያነሳሉ ወይስ በ 2021 አዲስ አሸናፊ ይኖራል?

በዚህ ዓመት በሙሉ አቅሙ ታዳሚ በሚይዘው በኒው ዮርክ ፍለሺንግ ሜዶውስ በከዋክብት የተሞላ የሴቶች ውድድርን ያስተናገዳል።  ሰባት ዋና አሸናፊዎች በአሁኑ ስአት በደብሊው.ቲ.ፒ 10 ከፍተኛ ደረጃዎች ውስጥ ተቀምጠዋል ።  በአጠቃላይ የ 34 የተለያዩ ሀገራት ተጫዋቾች በዚህ ዓመት በዩ.ኤስ ኦፕን በ ሴቶች ምድብ ይወዳደራሉ።  በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ካሉ 100 ምርጥ ውስጥ ያሉ 16 አሜሪካውያንን ያጠቃልላል።

ለአሸናፊነት ተጠባቂዎች

አሽሌይ ባርቲ

skysports.com

በቅርቡ ሁለተኛውን ዊምብሌዶኗን   ካሸነፈች በኋላ አውስትራሊያዊዋ የዓለም ቁጥር 1 አሽሌይ ባርቲ ሰንጠረዡን ትመራለች።  በዚያ የቅርብ ጊዜ ድል መሰረትም በራስ መተማመን ተሞልታ ወደዚህ ውድድር መግባት አለባት።  በዛም ምክንያት ፣ ምንም እንኳን በብዙ ጎበዝ ተጫዋቾች የታጨቀ ውድድር ቢሆንም ለማሸነፍ ከተጠበቁት መካከል አንዷ ናት።

ናኦሚ ኦሳካ

theghanareport.com

የአራት ጊዜ የግራንድ ስላም አሸናፊ ፣ ናኦሚ ኦሳካ ቀኗ በሆነ ጊዜ በቀላሉ ሻምፒዮናውን ማንሳት የሚትችል ሌላ ተጫዋች ናት።  የባለፈው አመት የዩኤስ ኦፕን ሻምፒዮን ስለሆነችም ፣ ቦታው ከእሷ ጋር ሊስማማ ይችላል ።  ይሁን እንጂ ኦሳካ ባለፉት የተወሰኑ ወራት ውስጥ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ አሳልፋለች።  ከፈረንሣይ ኦፕን ወጣች እና በቅርቡ በቼክ ተጫዋች ማርኬታ ቮንዶሮቫ ከኦሎምፒክ ተሰናበተች።

ቢያንካ አንድሬሴኩ


www.wtatennis.com

ካናዳዊዋ ቢያንካ አንድሬሴኩ በአሁኑ ጊዜ የዓለም ቁጥር 5 ናት። በ 2019 ደረጃዋን በአንዴ ከፍ አድርጋለች ግን ከዚያ በኋላ በኮቪድ እና በጉዳት ምክንያት ስትቸገር ነበር።  እሷ ከዚህ ቀደም ወደነበራት አስደናቂ ስኬት ለመመለስ የዩኤስ ኦፕንን ለመጠቀም ተስፋ ታደርጋለች።

ኢጋ ስዊአቴክ

tennishead.net

የዓለም ቁጥር 8 ፣ የፖላንድ ተጫዋች ኢጋ ስዊአቴክ ሌላዋ ተጠባቂ ተጫዋች ናት ።  እ.ኤ.አ. በ 2020 በፈረንሣይ ኦፕን በሸክላ ሜዳ አሸንፋለች እና በኒው ዮርክ የከባድ ሜዳ ወለል ላይ እኩል ምቾት እንዳላት ለማሳየት መፈለጓ አይቀርም ።

ሌላ ሰው ዋንጫውን ሊያነሳ ይችል ይሆን?

ከዚህ በላይ ያልተዘረዘረ ሌላ ተጫዋች ዋንጫውን ሊያነሳ ቢችልም ፣ ተጠባቂዎቹ ያለ ምክንያት አይደለም ተጠባቂ የሆኑት።  ማንኛውም ተጫዋች ሊያደርገው ይችላል ፣ ዋናው ጥያቄ ግን ያደርጉታል ወይ ነው?  በዚህ ዓመት በዩኤስ ኦፕን ላይ ያልተጠበቁ ድሎችን ሊያሳኩ የሚችሉ አንዳንድ ተጫዋቾችን እንመልከት ።

ስለ ሴሬና ዊልያምስ ሳይጠቅስ በዘመናዊ የሴቶች ቴኒስ ላይ የሚደረግ ውይይት የተሟላ አይሆንም ።  ለ 39 ዓመቷ ታዋቂ አሜሪካዊ የጉብዝና ጊዜዋ ያለፈ ሊመስል ይችላል ።  እሷ ከዊምብሌዶን ዝነኛ የሣር ሜዳዎች እያነከሰች ለመውጣት ስትገደድ ብዙዎች ውድድሩ ላይ እንደገና  እናያታለን የሚለውን ጥያቄ ጠይቀው ነበር።  ወሬው ዊሊያምስ እንደ እናት ውድድሩን ማሸነፍ ትፈልጋለች እና በእርግጥ የማርጋሬት ኮርትን የ 24 ዋና ዋና የነጠላዎች ውድድር የሁሉም ጊዜ ሪከርድ ለመጋራት በጣም ትፈልጋለች ።

ከላይ ከተጠቀሱት ተወዳጆች በተጨማሪ በእጩው ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ የተሰጣቸውን እና በዚህ ውድድር ውስጥ ተወዳጅነትን ያተረፉትን ለማስቸገር አቅም ያላቸው ሌሎች የነጠላ ውድድር አሸናፊዎች አሉ።  በመጀመሪያ ፣ የአሁኑ የዓለም ቁጥር 10 እና የቀድሞው የዓለም ቁጥር 1 ፣ ሲሞና ሀሌፕ አለች።  ሮማኒያዊቷ በ 2019 የዊምብሌዶንን አንስታ ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ግን በፈረንሣይ ኦፕን እና በዊምብሌዶን እንዳትወዳደር ያጋጠሟት ጉዳቶች አግደዋታል ።  ተመልሳ ተፅእኖ መፍጠር እንደምትችል ጊዜ የሚነግረን ይሆናል ።

ምናልባት ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስመዘግቡ የሚችሉ ሌሎች በርካታ ተጫዋቾች አሉ።  የፈረንሣይ ኦፕን ሻምፒዮን እና የዓለም ቁጥር 11 ን ፣ ባርባራ ክሬጅኮኮቫ ፣ የሁለት ጊዜ የዊምብሌዶን አሸናፊ እና የዓለም ቁጥር 13 ፣ ፔትራ ኪቪቶቫ ፣ የሁለት ጊዜ የአውስትራሊያ ኦፕን ሻምፒዮን እና የዓለም ቁጥር 14 ቪክቶሪያ አዛሬንካ ፣ እና የሶስት ጊዜ የግራንድ ስላም ሻምፒዮን አንጀሊከ ኬርበር።

 የዘንድሮው የዩኤስ ኦፕን በዚህ ዓመት ከፍተኛ ፉክክር የሚኖረው ይመስላል በመጨረሻ ዋንጫውን የሚያነሳውም ተጠባቂ ተጫዋች ላይሆን ይችላል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Tennis