Connect with us
Express news


Fighting

የ 2018 ምርጥ 6 የ ዩኤፍሲ አሳምኖ ማሸነፎች!

Top 6 UFC Submissions of 2018!
cbsistatic.com

አሳምኖ ማሸነፍ በዩኤፍሲ ፍልሚያ ለማሸነፍ በጣም የሚኮራበት መንገድ ነው – አንድ ተዋጊ ጉዳት ደርሶበት ወይም ራሱን በመሳቱ ዳኛው ወይም ሐኪሙ ትግሉን ሲያቆሙ ማለት ነው።

6. ራያን ​​ሆል ቢጄ ፔንን አሸነፈው

ራያን ሆል በብራዚል ጁ-ጂትሱ የዓለም ሻምፒዮን ቢጄ ፔንን በገራሚ ሁኔታ ዘርሮ የዓለም አድናቆትን አግኝቷል። ሆል ፔንን በእግሩ ቆልፎ የተቀራረበ የነበረውን ትግል አሸንፏል ፣ የእግር አቆላለፉም ለምን ከምርጦቹ መካከል አንዱ እንደሆነ ከዚያም አልፎ በኤምኤምኤ ውስጥ ምርጡ የሚባል እንደሆነ አሳይቷል። ፈጣን ፣ አጥፊ እና ቆራጥ ፣ ሆል የተቀራረበ ፍልሚያን ከፍቶ በሰከንዶች ውስጥ በሂል ሁክ ማሸነፍ ችሏል ያውም ከዩኤፍኤፍ ሆል ኦፍ ፌመር ጋር።

5. ፖል ክሬግ ማጎሜድ አንካሌቭን አሸነፈው

thesun.co.uk

የስኮትላንዱ ፖል ክሬግ ከውድድር አለም ሊርቅ ትንሽ ነበር የቀረው ግን ማጎሜድ አንካላሌቭ ወደ ዝና መልሶታል ያውም የመጀመሪያውን የዩኤፍሲ ድሉን በክሬግ ላይ ያስመዘግባል ተብሎ ሲጠበቅ። ነገር ግን ተዓምር በሆነ ሁኔታ ክሬግ በሦስት ማዕዘን ማነቆ ይዞ የአንካሌቭን የአየር መተላለፊያዎች በመቁረጥ መሬት ደብድቦ መሸነፉን እንዲያምን አስገደደው። ድሉን በሦስተኛው ዙር ዘግይቶ ነበር ያሳካው ፣ ይህም ለክሬግ የምሽቱ ምርጥ እንቅስቃሴ ማዕረግ ፣ እና አዲስ የዩኤፍሲ ኮንትራት አስገኝቶታል።

4. አሌክሴ ኦሌኒ በጁኒየር አልቢኒ ላይ

mmamania.com

አሌክሴ ኦሌኒክ “ዘ ቦአ ኮንስትሪክቶር” የሚባለውን የራሱን ልዩ እንቅስቃሴ ተጠቅሞ ጁኒየር አልቢኒን በ ዮኤፍሲ 224 ግንቦት 13th 2018 አሸንፏል። ዩክሬናዊው ይህንን እንቅስቃሴ ከ 11 በላይ ተጋጣሚዎችን ለመጨረስ ተጠቅሟል – ሰዎች በ ዩኤፍሲ ታሪክ ውስጥ በጣም አስፈሪ ከሆኑት ተፋላሚዎች አንዱ ቢሉት አያስገርምም።

3. ቻርለስ ኦሊቬራ ክሪስቶስን ጊያጎስን አሸነፈ

mmafighting.com

ሮይስ ግሬሲ በኤምኤምኤ ውስጥ የመጀመሪያው አሳምኖ የማሸነፍ ጥበበኛ ነበር ፣ እና የእሱ የ ዩኤፍሲ የማሸነፍ ሬከርድ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀ መሆኑ ብዙ ይናገራል። ሆኖም ፣ ሁሉም ሬከርዶች መሰበር አለባቸው! በመስከረም ወር 2018 ፣ ቻርለስ ኦሊቬራ ክሪስቶስን ጊዮጎስን በልዩ እንቅስቃሴው የኋላ ኔክድ ቾክ በማሸነፍ በኦክታጎን ውስጥ 11 የማሳመን ድሎችን በማስመዝገብ እና “ዱ ብሮንክስ” ን እንደ የዩኤፍሲ የሁል ጊዜ የአሳምኖ ማሸነፍ ንጉስ አድርጎ አስመዘገበ።

2. ዳረን ኤልኪንስ ማይክል ጆንሰንን አሸነፈ

ይህ የተለመደው የዳርረን ኤልኪንስ ፍልሚያ ነበር። የኢንዲያና ‘ግሪትማስተር’ ገና ከመጀመሩ የማይክል ጆንሰን የጥቃት ተቀባይ ሆነ። ሆኖም ፣ በሁለተኛው ዙር ፣ ዳረን ኤልኪንስ በኃይል በተሞላ ሁኔታ መልሶ እያጠቃ ነበር። የኋላ ማነቆን ተጠቅሞ ማይክል ጆንሰንን በማሸነፍ ሕዝቡን አስደንግጧል።

1. አልጃሜይን ስተርሊንግ እና ዛቢት ማጎሜድሻሪፖቭ

https://www.bloodyelbow.com/

ኤምኤምኤ ከታዩ አሳምኖ ማሸነፎች በጣም የተለዩ ከሚባሉት አንዱን የተመለከትነው በመስከረም 2018 ነው። ሁለት ጊዜ! ሁለቱም አልጃሜይን ስተርሊንግ እና ዛቢት ማጎሜድሻሪፖቭ ሰዎች ስም ሊሰጧቸው ባልቻሉ እንግዳ እንቅስቃሴዎች በመጠቀም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል – ‘ባናና ስፕሊት’ ይባል ፣ ‘ኒባር’ ፣ ‘ሱሎዬቭ ስትሬች’ ይባል አይታወቅም? ምን እንደሚባል ለማወቅ ከባድ ነበር ፣ ግን ይህ ልዩ እንቅስቃሴ እስከዚያ ድረስ በ ዩኤፍሲ ታሪክ ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነበር የተደረገው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Fighting