Connect with us
Express news


Bundesliga

ቦርሲያ ዶርትመንዶች 5 ግብ በተቆጠረበት ጨዋታ ሆፈኒየምን 3-2 አሸንፈዋል

Borussia Dortmund Sink Hoffenheim 3-2 in 5 Goal Thriller
tt.loopnews.com

ኤርሊንግ ሃላንድ በዶርትመንድ ሲግናል ኢዱና ፓርክ ስታዲየም በአስደናቂ ጨዋታ ውስጥ ዘግይቶ ቢሆንም የማሸነፊያውን ግብ አስቆጥሯል።

አጥቂው ኤርሊንግ ሃላንድ ዓርብ በተደረገው ጨዋታ በተጨማሪ ሰአት ያስቆጠራትን ግብ ቦርሲያ ዶርትመንዶች ሆፈኒየምን 3-2 በሆነ ውጤት አሸንፈው ወደ ቡንደስሊጋው የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ እንዲቀመጡ አስችሏቸዋል!

የሆፈኒየም አጥቂ አንድሬጅ ክራማሪች በ 3 ኛው ደቂቃ የግቡ ጠርዝ የገጨ ሙከራ ሲያደርግ የቡድን አጋሩ ግብ ጠባቂ ኦሊቨር ባውማን ልክ ጨዋታው እንደተጀመረ የዶርትመንዱ ጆቫኒ ሬይናን ለግብ የቀረበ ኳስ ማዳን ችሏል።

በግራ በኩል የከፈቱትን የማጥቃት ጨዋታ ሬንያ ከግብ ጠባቂው ባውማን በስተቀኝ በኩል የመታትን ኳስ የመክፈቻ ግብ ከመሆንዋ በፊት ፣ በ 2 ኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ ዶርትሙንዶች ከብዙ የተሻሙ ኳሶችን መተረፋቸው ቀጥለው ለሚፈጠሩ ነገሮች ፍንጭ ሰጪ ነበር።  

bundesliga.com

ሆፈኒየሞች የማጥቃት ጫናውን ቀጠሉቡት እና በ 61 ኛው ደቂቃ ዴኒስ ጊገር ለ ክሪስቶፍ ባምጋርትነር ከተከላካዮች ጀርባ ድንቅ ኳስ በማቀበል የክንፍ አጥቂው ኳሱን ግብ ጠባቂው አልፎ ከመረብ ጋር ማገናኘት ችሏል።

ዶርትመንዶች ተስፋ አልቆረጡም ፣ ከ 8 ደቂቃዎች በኋላ እንደገና መምራት ችለዋል ፣ ጁድ ቤሊንግሃም በጭኑ ላይ በደካማ ሁኔታ ኳሱን በመቆጣጠር፣ በፔናሊቲ ሳጥን ውስጥ ፣ ኳሱን ወደ ግራ ጥግ በመምታቱ ውጤቱን 2-1 ለማድረግ ችሏል።

ሙናስ ዳቡር ውጤቱን 2-2 በማድረግ በተለመደው ሰዓት በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ሆፈኒየሞች አንድ ነጥብ እንደወሰዱ አስበው ነበር ፣ ነገር ግን ሃላንድ ከአንድ ደቂቃ በኋላ ሆፈኒየሞች ልቅ የሆነ ቅብብል አድርገው የፈጠሩትን ስህተት ተጠቅሞ ወደ ግብ ጠርዝ በመምታት ያስቆጠረውን ግብ እንዲያሸንፉ አስችሏቸዋል።

remonews.com

ዶርትሙንድ ዳኛው በ 98 ኛው ደቂቃ የመጨረሻውን ፊሽካ እስኪነፋ ድረስ ሲጠባበቁ ነበር። ዎልፍስበርግን በግብ በልጠው ፣ አሁን የቡድስ ሊጋውን የደረጃ ሰንጠረዥ በ 6 ነጥብ ይመሩታል ፣ ነገር ግን ከሚፎካከርዋቸው ቡድኖች በ1 ጨዋታ ይቀድማሉ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Bundesliga