Connect with us
Express news


Football

ማንቸስተር ሲቲ በ 10 ሰው የተጫወተው አርሰናልን 5-0 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል!

Manchester City FC humiliate 10-man Arsenal FC 5-0!
skysports.com

ሰማያዊዎቹ ማንችስተር ትክክለኛ 9 ቁጥር አጥቂ ባላሰለፉበት ጨዋታ በአርሰናል መረብ ላይ 5 ግቦችን አሳርፈዋል! ምን እንደተፈጠረ እንመልከት።

በ10 ሰው የተጫወቱት አርሰናሎች በማንቸስተር ሲቲ ሙሉ በሙሉ ተበልጠው በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግርጌ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።

መድፈኞቹ ከሊጉ የውድድር ዘመን የመጀመሪያዎቹን 3 ጨዋታዎች የተሸነፉት ከ 1954 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ሲሆን ይህ ጨዋታ ደግሞ ከእረፍት በፊት በ45 ደቂቃ ተጠናቋል።

የሲቲዎቹ ኢልካ ጉንዶጋን እና ፈራን ቶሬስ በመጀመሪያዎቹ 12 ደቂቃዎች ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል። አርሰናሎች የነበራቸውን ውጤት የመቀልበስ ተስፋ ግራንቲ ዣካ ጃኦ ካንሴሎ ላይ በሰራው የሁለት እግር ታክል በቀይ ከሜዳ በመሰናበቱ ተስፋቸውን አጨልሞታል ።

arseblog.news

በመቀጠልም የ 100 ሚሊዮን ፓውንዱ ጃክ ግሪሊሽ ከግማሽ ዕረፍት በፊት ለጋብሬል ጃሱስ በማሾፍ ያቀበለውን ኳስ በቀላሉ 3 ኛውን ግብ እንዲያስቆጥር አስችሎታል ፣ ከዚያ በኋላ ሮድሪ ከ 20 ያርድ ርቀት ላይ 4 ኛውን ግብ በእግሩ አስቆጥሯል ።

የሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ 2 ኛውን አጋማሽ በጀመረ በ 16 ደቂቃዎች ውስጥ 3 ቱን ተቀያሪዎቹን መጠቀሙ ጨዋታዉን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራችውን የሚያሳይ ነበር። ሲቲዎች ከዛ በኋላ ኳስን ተቆጣጥረው መጫወት ቀጠሉ፣ እናም ጨዋታው ሊጠናቀቅ 6 ደቂቃ ሲቀረው ቶሬስ ለራሱ 2 ኛ ግብ በማስቆጠር አስርሴናልን አዋርዷል ።

theathletic.com

ሚኬል አርቴታ ፣ የጋርዲዮላ ባልደረባ እና የቀድሞው ረዳት ፤ ራሄም ስተርሊንግ ፣ አይሜሪክ ላፖርቴ እና ሪያድ ማህሬዝ ያባከኗቸውን የግብ እድሎች በአሰልጣኙ እና በቴክኒካል ስታፎች ላይ ትልቅ መደናገጥ ሊፈጥር የሚችል ቁጥር ይመዘገብ ነበር።

በጨዋታው መገባደጃ ላይ አርሰናሎች ከግብ ውጭ የነበረችውን 1 ምት ብቻ አሳክተው ፣ በ19% የኳስ ቁጥጥር ጨዋታውን ጨርሰዋል።

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን በስራው ላይ ያለመተማመን ስሜት እየተሰማው መሆን አለበት። አርሴናል ለመጨረሻ ጊዜ የኢ.ፒ.ኤል. ጨዋታ ማሸነፍ የቻለው በየካቲት 2021 ሌስተር ሲቲን ከሜዳው ውጭ ሲያሸንፍ ነበር።

ድሉ ማንችስተር ሲቲን በኢ.ፒ.ኤል. የደረጃ ሰንጠረዥ በ4 ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አስችሎታል።

youtube.com

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football