Connect with us
Express news


Football

የ 10 ተጫዋቹ ቼልሲ እድሎቹን መጠቀም ያልቻለውን ሊቨርፑል ገቶ ይዟል

10-man Chelsea Stun Impotent Liverpool
https://www.bbc.com/

ዳኛ አንቶኒ ቴይለር አወዛጋቢ በሆነ ውሳኔ ሪስ ጄምስን በቀይ ቢያሰናብትም ቼልሲ ሊቨርፑልን አቻ አስወጥቶታል።

ሪስ ጄምስ ከጨዋታው አጋማሽ በፊት ቢሰናበትም ቼልሲ ሊቨርፑልን በአንድ ነጥብ ብቻ በቃ ብሎታል።

ሰማያዊዎቹ በጥሩ አጨዋወት ጀምረው ነበር ፣ ካይ ሃቨርትዝ ከሪስ ጄምስ ከተሻማ ማእዘን ምት አስደናቂ ግብ በ 21 ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል ። ቼልሲ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ተደራጅቶ ፣ አስፈሪ ሆኖ እና አተኩሮ ነበር ሲጫወት የነበረው ። ተጨማሪ ግቦችን ሚያስቆጥሩ ይመስሉ ነበር ፣ ግን ያ ጨዋታውን በከፍተኛ ሁኔታ ከቀየረው ከዳኛ አንቶኒ ቴይለር ውሳኔ በፊት ነበር።

theathletic.com

በ 46 ኛው ደቂቃ ላይ ሊቨርፑል የግብ ዕድል ነበረው ፣ አንድሪው ሮበርትሰን ያሻማው ኳስ በማኔ ወደ ኋላ ማዕዘን ሲሞከር ፣ የጄምስ ጭን እና ከዚያ እጁን ነካው። ውሳኔው ወደ ቪኤአር ሄደ ፣ እናም አንቶኒዮ ቴይለር ክስተቱን ራሱ በመመርመር እንደ ሆን ብሎ የእጅ ኳስ አድርጎ ጄምስን አሰናብቶ ለሊቨርፑል ፍፁም ቅጣት ምት ሰጥቷል። በቀጣዩ ትርምስ ውስጥ የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኤዱዋርድ ሜንዲ እና አማካዩ ማቲዮ ኮቫቺ ለተቃውሞም ቢጫ ካርድ አይተዋል።

መሐመድ ሳላህ በቀላሉ ፍፁም ቅጣት ምቱን ካገባ በኋላ 1-1 ሆነ ፣ እና ቼልሲ ወደ 10 ሰዎች ዝቅ ሲል ጨዋታው ለመርሴሳይዱ ቡድን የተረጋገጠ ይመስል ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ ቀዮቹ ቼልሲን ወደ ገደባቸው በመግፋት ሙሉ በሙሉ ሲያጠቁ ነበር። ሆኖም ሁለተኛ ግብ ሊቨርፑል ሊያገኝ አልቻለም ፣ የቶማስ ቱቸል ቡድን የመከላከል መረጋጋትን ፣ አደረጃጀትን እና በራስ መተማመንን አሳይቷል። 90 ኛው ደቂቃ እየቀረበ ሲመጣ በአንፊልድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጥረት እያደገ መጣ ደጋፊዎችም በሜዳቸው በ 10 ተጫዋች ቼልሲ ሁለት ነጥቦችን ሊያጡ እንደሚችሉ ተረዱ።

 በመጨረሻ ቼልሲዎች ተቋቁመው ወጡ ፣ ሜንዲ በጎል ላይ ስድስት ሙከራዎችን መልሷል ፣ ለሰማያዊዎቹ ከፈረመ በኋላ በማንኛውም መልኩ በአንድ ጨዋታ ያደረገው ከፍተኛ ነው። ቼልሲ ከዚህ በፊት ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ እንደ ከባድ ተፎካካሪ ተደርጎ ካልተቆጠረ በእርግጥ አሁን በደንብ ይጠበቃል – ከዓለም አቀፉ ዕረፍት በፊት በልበ ሙሉነት ከዚህ ጨዋታ መውጣት ችለዋል ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football