Connect with us
Express news


Football

የቅዳሜ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል.) ማጠቃሊያ!

English Premier League (EPL) Saturday Round-up!
thesun.co.uk

ሁሉም ጨዋታዎች ፣ ሁሉም ግቦች እና ሁሉም የመነጋገርያ ነጥቦች! ታዲያ ትናንት በኢ.ፒ.ኤል ምን ተፈጠረ ?

ማንቸስተር ሲቲ እግር ኳስ ቡድን 5 – አርሰናል እግር ኳስ ቡድን 0

በ 1 ኛው አጋማሽ አርሰናሎች 10 ተጫዋቾች ለመጫወት በተገደዱበት ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ መድፈኞቹን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፈዋል። ለዚህ መፈጠር ምክንያት የስዊስ ኢንተርናሽናል ተጫዋች በሁለት እግሩ ታክል ወርዶ ጃኦ ካንሲሎ ላይ ጥፋት በመስራቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱ ነበር ። ኢካይ ጉንዶጋን ፣ ፈራን  ቶሬስ (2) ፣ ጋብሬል ጃሱስ  እና ሮድሪ ለሲቲ ሲቲ ጎል ማስቆጠር ችለዋል። አርሰናል ተስፋ የቆረጠ ይመስላል (በጨዋታው 19% ብቻ የኳስ ቁጥጥር ነበራቸው) እና በሰሜን ለንደን ውስጥ አንዳንድ ለውጦች መደረግ እንዳለባቸው ግልፅ ነው። ሲቲ በ ኢ.ፒ.ኤል. 5 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ፣ አርሰናል በዜሮ ነጥብ እና በ -9 የግብ እዳ መጨረሻ ላይ ተቀምጧል!

አስቶን ቪላ እግር ኳስ ቡድን 1 – ብሬንትፈርድ እግር ኳስ ቡድን 1

በቪላ ፓርክ ውስጥ ፈጣን እና አስደሳች ጨዋታ ኢቫን ቱኒ ባስቆጠራት ግብ ብሬንትፎርድ ገና በመጀመርያው 7 ደቂቃ ውስጥ መምራት እንዲችል አድርጓል ፣ ሆኖም ኤሚልያኖ ቡንዲያ ከ 5 ደቂቃ በኋላ በጥሩ ሁኔታ ወደ ግቡ ጠርዝ የመታው ኳስ አቻ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። በመጨረሻ ፣ እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ ማኝየታቸው ፍትሃዊ ውጤት ነበር ፣ ብሬንትፎርድ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደገ በኋላ እስካሁን አልተሸነፈም። ውጤቱም አስቶን ቪላ በ 11 ኛ እና ብሬንትፎርድ በ ኢ.ፒ.ኤል የደረጃ ሰንጠረዥ በ 9 ኛ ደረጃ እንዲቀመጡ አድርጓል።

ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን እግር ኳስ ቡድን 0 – ኤቨርተን እግር ኳስ ቡድን 2

ኤቨርተን ከሜዳው ውጪ በቪላ ፓርክ 2 ለ 0 በማሸነፍ በኢ.ፒ.ኤል. ያለመሸነፍ ጉዞዉን ማስጠበቅ ችሏል ። የመጀመርያው አጋማሽ ሊያልቅ 4 ደቂቃ ሲቀረው ዲማራይ ግረይ በራሱ ጥረት የግብ ማግባት ዘመቻዉን አስጀምሯል ። ከዚያ ዶሚኒክ ካልቨር-ሌዊን እስካሁን በውድድር ዘመኑ 3 ኛውን ፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል። ሆኖም ዕድሉን ያገኘው ቅጣቱን ለመውሰድ የፈለገው ሪቻርሊሰን በመጨረሻ ለኳልቨር-ሌዊንን ኳሱን ከሰጠ በኋላ ነው። ውጤቱ ኤቨርተንን በደረጃ ሠንጠረዡ ወደ 2 ኛ ሲያመጣው ብራይተንን በ7 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ኒውካስትል ዩናይትድ እግር ኳስ ቡድን 2 – ሳውዝሃምፕተን እግር ኳስ ቡድን 2

liechtenstein.bpositivenow.com

ጀምስ ዋርድ-ፕሮውስ በ96ኛ ደቂቃ ባስቆጠራት አስደናቂ ፍጹም ቅጣት ምት ሳውዝሃምፕተኖች በኒውካስል ሜዳ ውስጥ በአቻ ውጤት እንዲለያዩ አድርጓል። ይህ የሆነው አላን ሴንት-ማክሲሚን ለኒውካስትል በባከነ ሰአት ያስቆጠራት የአሸናፊ ግብ ከያዘ በኋላ ነበር። ሆኖም ሁለቱም ቡድኖች በመጨረሻ በዚህ በሴንት ጀምስ ፓርክ ከተደረገው አስደሳች ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ ወስደዋል። ከዚህ ውጤት በኋላ ኒውካስትል አሁን በ 13 ኛ እና ሳውዝሃምፕተን በኢ.ፒ.ኤል የደረጃ ሰንጠረዥ 15 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ኖርዊች ሲቲ እግር ኳስ ቡድን 1 – ሌስተር ሲቲ እግር ኳስ ቡድን 2

thetimes.co.uk

የኬኒ ማክሌን አቻ የምታደርጋቸው ግብ ከተከለከሉ ብኋላ ማርክ አልብራይተን ያስቆጠራት ግብ ሌስተር ሲቲዎች በካሮው ሮድ በጠባብ ውጤት እንዲያሸንፉ አስችሏቸዋል። ቀደም ሲል በጄሚ ቫርዲ (ሌስተር) እና ቴሙ ፑኪ ለኖርዊች ከቅጣት ምት ግብ አስቆጥረዋል። ሌስተር አሁን በኤ.ፒ.ኤል. 8 ኛ ፣ ኖርዊች ሲቲ አርሰናልን ብቻ በልጠው በ 19 ኛ ደረጃ ላይ ጠቀምጠዋል፣ እንዲሁም እስካሁን ምንም ነጥብ መሰብሰብ አልቻሉም።

ዌስትሃም ዩናይትድ እግር ኳስ ቡድን 2 – ክሪስታል ፓላስ እግር ኳስ ቡድን 2

በአስደሳቹ ለንደን ደርቢ ኮኖር ጋላሀር ፣ የፓትሪክ ቬራ የክርስታል ፓላስ ዘመኑን የመጀመርያ ግብ በማስቆጠር ፣ የዌስትሃም የማሸነፍ ጉዟቸውን በሚያሳዝን ሁኔታ አብቅቷል። ከፓብሎ ፎርናልስ እና ሚካኤል አንቶኒዮ የተገኙ ግቦች የጋላገርን ሁለት ግቦች ሰርዘው ሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ተካፍለው እንዲወጡ አድርገዋል። ዌስትሃም ዩናይትድ በኢ.ፒ.ል የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ ተቀምጦ ወደ ኢንተርናሽናል ዕረፍት የሚያመራ ሲሆን ክሪስታል ፓላስ አሁን በ 14 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሊቨርፑል እግር ኳስ ቡድን 1 – ቼልሲ እግር ኳስ ቡድን 1

liverpool.offside.sbnation.com

ቼልሲዎች በአንፊልድ በተደረገው ፈጣን እና ከባድ ጨዋታ ፣ ሬይስ ጀምስ የመጀመሪያ አጋማሽ በእራሱ ግብ መስመር ላይ ኳስ በእጁ ነክቶ በቀይ ከሜዳ በመሰናበቱ ወደ 10 ተጫዋቾች ቢቀነሱም ፣ ሊቨርፑልን አስቸግረው ነጥብ ይዘው መውጣት ችለዋል። ካይ ሃርቨርትዝ በ22ኛ ደቂቃ በጭንቅላቱ ለቼልሲ ግብ አስቆጥሯል ። በ45ኛው ደቂቃ ሞሃመድ ሳላህ ባስቆጠራት ፔናሊቲ ሊቨርፑልን አቻ ማድረግ ችሏል። ይህ ማለት ደግሞ ሊቨርፑሎች በ3ኛ ደረጃ ሲከመጡ ፣ ቼልሲዎች 2ኛ ደረጃን ይዘዋል ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football