Connect with us
Express news


Football

የፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል.) ማጠቃሊያ; እሑድ በእንግሊዝ ውስጥ የነበሩ ሁሉንም ክንውኖች

Premier League (EPL) round-up; All the Action from Sunday in England
telegraph.co.uk

ትናንት በኢ.ፒ.ኤል. ውስጥ የተደረጉትን ጨዋታዎች እና ግቦች እንመልከት። ምን ተፈጠረ ፣ ማን አስቆጠረ እና ዋናዎቹ የመነጋገሪያ ነጥቦች ምንድናቸው?

በርንሌይ 1 – ሊድስ ዩናይትድ 1

በ ኢ.ፒ.ኤል. ለመጀመሪያ ጊዜ በደጋፊዎች ፊት የተደረገው የበርንሌይ እና የሊድስ ዩናይትድ ጨዋታ ከባድ ፉክክር የታየበት ሲሆን 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። ፓትሪክ ባምፎርድ የመጀመሪያውን የእንግሊዝን ጥሪ አግኝቶ አዲስ ኮንትራት የፈረመበትን የሕልም ሳምንት አጠናቆ ሊድስ ዩናይትድ በቱር ሞር አንድ ነጥብ እንዲያገኙ ያስቻላቸውን ግብ አስቆጥሯል። ባምፎርድ 86 ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኒውዝላንዳዊው ክሪስ ዉድ በ 61 ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ለመሻር በቂ ነበረች። ውጤቱን ተከትሎ ሊድስ እና በርንሌይ በ ኢ.ፒ.ኤል. የደረጃ ሠንጠረዥ በቅደም ተከተል 15 ኛ እና 16 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ቶትንሃም ሆትስፐር 1 – ዋትፎርድ 0

thesun.co.uk

በቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም የተደረገው ይህ ጨዋታ ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶ የመጀመሪያውን 3 የሊግ ጨዋታዎች በቡድኑ የበላይነት ያሸነፈ 2 ኛ የቶተንሃም አሰልጣኝ ሆኗል። ይህንን ድንቅ ሥራ መፈጸም የቻለ የመጨረሻው ሰው አርተር ሮው በ 1949 ነበር! ሆኖም ሶን ሄንግ-ሚን በፍፁም ቅጣት ምት ግብ ጠባቂውን ዳንኤል ባችማን አታሎ በስተቀኝ ከታች ጥግ በመምታት ግብ ቢያስቆጥርም ፣ እድለኛ ባልሆኑት ዋትፈርዶች በጣም ተፈትነው ነበር ።  ስፐርሶች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብቸኛው 100% የማሸነፍ ጉዞ የያዘው ቡድን በመሆን በደረጃ ሰንጠረ አናት ላይ ተቀምጠዋል ፣ ዋትፎርድ በ 12 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ 0 – ማንቸስተር ዩናይትድ 1

shropshirestar.com

የዩናይትድ የቅርብ ሜጋ ፈራሚ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በዎልቨርሃምፕተኑ ጨዋታ አልተሰለፈም ፣ ነገር ግን የቀያይ ሰይጣኖች ደጋፊዎች ስሙን እያነሱ ሲዘምሩ በሜዳ ውስጥ የተሰለፈ ይመስል ነበር።  ዎልቭሶች ለረጅም ጊዜ የበላይ ሆነው ነበር ፣ ነገር ግን ሜሰን ግሪንዉድ ለዩናይትድ በ 80 ደቂቃዎች የማሸነፊያውን ግብ ማስቆጠር ችሏል። ዎልቭሶች በሩበን ኔቨስ ጥፋት ተሰርቷል በማለት ግቡን ውድቅ ለማድረግ ጥያቄ ቢያቀርቡም ፣ ግቡ ግን ጸድቋል። ውጤቱ ዎልቭስን ያለ ምንም ነጥብ በ 18 ኛ ደረጃ ሲያስቀምጣቸው ፣ ማንቸስተር ዩናይትዶችን ግን ወደ 3 ኛ ደረጃ ከፍ እንዲሉ አስችሏቸዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football