Connect with us
Express news


Football

ሜሲ ለፓሪስ ሴንት ጀርሜን የመጀመሪያ ጨዋታ አድርጓል ፣ ግን ሬምስን 2-0 ባሸነፉበት ጨዋታ ኮከብ የነበረው ምባፔ ነበር

Messi makes Paris Saint-Germain debut, but  Mbappé is the star of the show in a 2-0 win over Reims
bbc.com

ሊዮኔል ሜሲ ለረጅም ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የመጀመሪያ ጨዋታውን እሁድ ለፓሪስ ሴንት ጀርሜን ያደረገ ሲሆን ቡድኑ በሊግ 1 ሬሚስን 2-0 ባሸነፈበት ጨዋታ የድሮው ጓደኛውን ኔይማርንቀይሮ በሁለተኛ አጋማሽ ቀይሮ ገብቷል።

ይህ እንዳለ ሆኖ በሜሲ ልዩ ምሽት ትዕይንቱን የሰረቀው ኪሊያን ምባፔ ነበር ፣ የፒኤስጂን የውድድር ዘመን ፍጹም አጀማመር ለማስቀጠል ሁለቱንም ግቦች ማስቆጠር ችሏል። የፈረንሳዩ ኮከብ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በቅርቡ በከፍተኛ ውዝግብ ላይ ነው ፣ ሪያል ማድሪድ የ 22 ዓመቱን ከፓሪስ ለመውሰድ ሁለት ከ 180 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ የተለያዩ ውሎችን ማቅረቡ ተዘግቧል።

ምንም እንኳን የክለቡ ስፖርት ዳይሬክተር ሊዮናርዶ ምባፔ ለመልቀቅ እንደሚፈልግ ቢገልጽም ሁለቱም ውሎች በ ፒኤስጂ ውድቅ ተደርገዋል ተብሏል።

ሜሲ ከባርሴሎና ውጭ ለሌላ ቡድን የመጀመሪያ የክለብ ጨዋታው ነበር።

አለቃው ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ለአማዞን እንደተናገሩት “እሱ አሁንም ከምርጥ አቋሙ ላይ አልደረሰም ነገር ግን በጥሩ ሁኔታ ልምምድ እያረገ ነው እናም በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ዝግጁ ይሆናል።” እኛ ከእሱ የተሻለውን እየጠበቅን ነው። የመጀመሪያ ጨዋታውን በማድረጉ በጣም ተደስቻለሁ። ለእሱ በጣም አስፈላጊ ነበር።

“እሱ ጥሩ ነበር ፣ ከመጀመሪያዎቹ ንክኪዎቹ ጀምሮ ለቡድኑ የአእምሮ ሰላም ሰጥቷል። በአሸናፊነት መጀመሩም ለእሱ ጥሩ ነው። ደጋፊዎቹን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ሕዝቡ ሲደግፉት መስማት ጥሩ ነበር ፣ ለሊዮ የሚገባው ነገር ነው።”

የምባፔ የመጀመሪያ ግብ ከአንሄል ዲ ማሪያ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ሲያስቆጥር ፣ ለሁለተኛው ግብ ደግሞ አችራፍ ሀኪሚ ያሻማውን ኳስ በቀላሉ አስቆጥሯል።

ፖቼቲኖ “ኪሊያን የእኛ ተጫዋች ነው እናም በእግር ኳስ እና በንግድ ውስጥ ሁል ጊዜ ወሬ እና ጭምጭምታ እንደሚኖር ይታወቃል” ብለዋል።

ነገር ግን አርእስተ ዜናዎቹ ከሁለተኛ ግብ በኋላ ተቀይሮ ስለገባው የ 34 ዓመቱ ሜሲ ይሆናሉ።

ሬምስ በስታዴ አውጉቴ-ዴላውን ለሚደረገው ጨዋታ 20,000 ትኬታቸውን ከሸጡ በኋላ የጨዋታው ትኬቶች በ 6,000 ዩሮ እንደገና ሲሸጡ ነበር። ሜሲ ከመፈረሙ በፊት 6,000 ያህል ብቻ ትኬት ነበር የተሸጠው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football