Connect with us
Express news


Football

የዝውውር መስኮቱ የመጨረሻ-ቀን ፤ የመጨረሻ ሰአት ዝውውሮች!

Transfer Deadline-Day; Last Minute Transfers!
teamtalk.com

ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ሪያል ማድሪድን ከፈረንሳዩ ክለብ ሬንስ ተቀላቀለ። ፓሪስ ሴንት ጀርሜን (ፒኤስጂ) ፣ ሪያል ማድሪድ ለ ኪሊያን ምባፔ ያቀረበውን ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም እና አንትዋን ግሪዝማን በአስገራሚ ሁኔታ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ተመልሷል።

ሪያል ማድሪድ ለፒኤስጂው ኪሊያን ምባፔ በመጨረሻ ቀን ያቀረቡት የ 200 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ክፍያ ሳይሳካ ቀርቷል ነገር ግን ሌላ አስደሳች የፈረንሣይ ተሰጥኦ የሆነውን ኤድዋርዶ ካማቪንጋን ማስፈረም ችለዋል።

የ 18 ዓመቱ አማካይ ካማቪንጋ ከሬኔስ በ 6 አመት ኮንትራት እና በ 31ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ክፍያ ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሏል ፣ ተጨማሪ ክፎያዎችም ወደ 9 ሚሊዮን ዩሮ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ማድሪድ ፒኤስጂ ለቅርብ ጊዜ ጥያቄው ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ምባፔን በማሳደዱ ላይ ሽንፈትን ለመቀበል ተገደደ።

psgtalk.com

የማድሪድ የዝውውር ጥያቄ ፒኤስጂን 200 ሚሊዮን ዩሮ ሊያስገኝ ይችል ነበር ፣ ይህም ከሞናኮ ካስፈረሙበት 180 ሚሊዮን ዩሮ አነስተኛ ትርፍ ነበረው ፣ ያውም ደግሞ ምባፔ በውሉ ላይ ከ 12 ወራት ያነሰ ጊዜ ነው እየቀረው።

ሆኖም የፈረንሳዩ ክለብ እሱን ለማቆየት ቆርጦ የተነሳ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ከማድሪድ የ 160 ዩሮ እና የ 170 ሚ ጥያቄዎችን ውድቅ አድርገዋል። የፒኤስጂ ስፖርት ዳይሬክተር ሊዮናርዶ ተጫዋቹ ለመልቀቅ ፍላጎት እንዳለው አምኗል እና ምባፔ በጥር ወር ከሌላ ክለብ ጋር የቅድመ-ውል ስምምነት የመፈረም አማራጭ አለው።

 ፒኤስጂዎች ኑኖ ሜንዴስን ከስፖርቲንግ ሊዝበን ለማምጣት ባለቀ ሰአት ከስምምነት ደርሰዋል። የ 19 ዓመቱ የግራ መስመር ተከላካይ በአንድ የውድድር ዘመን የውሰት ውል ተቀላቅሏል ፣ በ 7 ሚሊዮን ዩሮ የውሰት ክፍያ ፣ በ 40 ሚሊዮን ዩሮም ለመግዛት አማራጭ አለው።

youtube.com

ቼልሲ በማንችስተር ዩናይትድ ሲፈለግ የነበረውን ሳኦል ንጉዌዝን ከአትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት ውል ማስፈረሙን አረጋግጧል። ስምምነቱ 4 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን ሰማያዊዎቹ በሚቀጥለው አመት በ 35 ሚሊዮን ዩሮ የመግዛት አማራጭ አላቸው።

ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ የተመለሰው ደግሞ አንትዋን ግሪዝማን ነው። ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ለግሪዝማን ለአንድ የውድድር ዓመት የውሰት ዝውውር ስምምነት ላይ ደርሰዋል ፣ ለተጨማሪ የውድድር ዘመን ማራዘምም አማራጭ አለው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football