Connect with us
Express news


Football

የላሊጋ ፍጥጫ; የስፔን ከፍተኛ ተፎካካሪ ቡድኖች እና ደርቢዎች

War in La Liga; Spain’s Top Rivalries and Derbies
the18.com

በስፔን ከፍተኛ ሊግ ላይ ተፎካካሪ ቡድኖች እነማን ናቸው? በጣም ከፍተኛ ፉክክር የሚታይባቸው የከተማ ደርቢዎችስ የትኞቹ ናቸው?

የሴቪላ ደርቢ – ሪያል ቤቲስ ከ ሴቪላ

የሲቪያ ደርቢ በስፔን ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበት የከተማ ደርቢ መሆኑ ጥያቄ የለውም። በስፔን ውስጥ የአንድ ቡዱን የበላይነት ያላቸው የከተሞች ታሪካዊ ደርቦች አሉ ፣ ነገር ግን የ ሴቪላ እና ሪያል ቤትስ ደርቢ አብዛኛዉን ጊዜ በተቀራራቢ ውጤት የሚያልቅ ጨዋታ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሲቪያ 6 የአውሮፓ ሊግ ዋንጫ ማንሳታቸው በሻምፒዮንነት ደረጃ ከ ቤትስ የታሻሉ ስኬታማ ቡድን ሆነው ታይተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤቲስ ደጋፊዎች ከፍተኛ የደጋፊ ብዛት እና ሰፊ ስታዲየም እንዲኖራቸው ከድመው ጥያቄ ያቀርባሉ ፣ ቤኒቶ ቪላማሪ ይህንን ጥያቄ የመለሰ ስታድየም ነው። ሪያል ቤቲስ ከከተማ ተቀናቃኞቻቸው በጨዋታ በአማካይ በ10,000 ደጋፊ ይበልጣሉ። ቤቲስ እራሳቸውን ከሴቪላ የበለጠ ደረጃ ያላው ቡድን አድርገው ይመለከታሉ እና ይህ ሁል ጊዜ በሜዳ ውስጥ እና ከሜዳ ውጪ የሚያደርጉት ፍኩክር ፣ በጣም አስደሳች ደርቢ ያደርገዋል።

የማድሪድ ደርቢ – ሪያል ማድሪድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

marca.com

ይህ ደርቢ ለረጅም ጊዜ በሪያል ማድሪድ በላይነት ተይዞ ነበር ።  ሆኖም የአትሌቲኮ ደጋፊዎች ዝነኞቹ ጎረቤቶቻቸውን ማሸነፍ በጣም ያስደስታቸዋል ። እ.ኤ.አ. በ 2010 በዲያጎ ሲሞኔ የሚመራው አትሌቲኮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ፣ ጨዋታው ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈላጊ እና የበለጠ ፉክክር ያለው ውድድር ሆነ።

ይአትሌቲኮ አስደናቂ ጉዞ እንደዚህ ነበር ፣ በሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ 2 የማድሪድ ደርቢ ነበሩ፣ ሁለቱም በሪያል ማድሪድ አስደናቂ ድል ተጠናቅቀዋል። ይህ ጨዋታ ከኤል ክላሲኮ ይበልጣል የሚለውን ሀሳብ ቢያከራክረንም ፣ ከቡድኖቹ ጥራት አንፃር ፣ በዓለም እግር ኳስ ውስጥ ካሉ እጅግ በጣም ጥሩ የከተማ ደርቢዎች አንዱ ነው።

ኤል ክላሲኮ – ባርሴሊና ከ ሪያል ማድሪድ

ይህ በእውነቱ ምንም ማስታወቂያ አያስፈልገውም። የክላሲኮን ፖለቲካ እና ውስብስብነት በአጭሩ ለማጠቃለል መሞከር ሞኝነት ነው ፣ ነገር ግን ይህ በፕላኔታችን ላይ ያሉትን 2 ትልልቅ ቡድኖችን የሚያሳየው በዓለም እግር ኳስ ውስጥ ትልቁ የቡድኖች ጨዋታ ሆኖ ይቆያል ብሎ መናገር ምንም ችግር የለውም። ከብዙ ታላላቅ ፉክክሮች እና ደርቢዎች በተቃራኒ ፣ ብዙውን ጊዜ ጨዋታው በቅድመ-ግጥሚያው ጩኸት እና የማጥቃት እግር ኳስ ፣ የላቀ ችሎታ እና ብዙ ግቦች የሚታይበት ደርቢ ነው።

ካለፉት ታላላቅ እና በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ኤል ክላሲኮዎች አንዱ በ2014 ማድሪድ ባርሴሎናን ያስተናገዱበት ጨዋታ ነው። ባርሴሎና 3 ለ 4 ባሸነፈብእት ጨዋታ ፤ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ሊዮኔል ሜሲ ሀትሪክ ፣ ዘግይቶ የተቆጠረ የማሸነፊያ ግብ ፣ 3 ፍጹም ቅጣቶች ምቶች እና ሰርጂዮ ራሞስ ቀይ ካርድ የተመለከተበት ነበር። የዚህ ጨዋታ ትኬቶች ርካሽ አይሆኑም ፣ ነገር ግን በሕይወትዎ ውስጥ ሊመለከቱት የሚገባ አንድ ጨዋታ ካለ ፣ በእርግጥም ይህ ደርቢ ነው!

ደርቢ ዲ ላ ኮሙኒታት – ቫሌንስያ ከ ቪላሪያል

sportingpedia.com

በ20 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፣ ቫሌንሲያ በስፔን ውድድር ውስጥ በራሳቸው መንገድ የተወሰኑ ነገሮችን ሰርተዋል። የከተማ ተፎካካሪቸው ሌቫንቴ አንዳንድ ጥሩ አቋሞች ቢያሳዩም ፣ ቪላሪያል በ 21 ኛው ክፍለዘመን በቫሌንሺያ ክልል ውስጥ ዋና ተቀናቃኝ ሆነው ብቅ ያሉ ቡድን ሆኗል። ቪላሪያል ፣  በአንዳንድ ጉልህ የገንዘብ ድጋፍ በመታገዝ ከምንም ተነስተው ከቫሌንሲያ ጋር ለመፎካከር ችለዋል።

እንዲያውም ተጫዋቾቻቸውን መስረቅ ጀምረው ነበር ፣ ዳኒ ፓሬጆ ፣ በወቅቱ የቫሌንሺያ ምርጥ ተጫዋች ፣ በ 2020 ወደ ኢስታዲዮ ዴ ላ ሴራሚካ አዘዋውረዋል። ባለፈው የላሊጋ የውድድር ዘመን ቫሌንሲያ በ14 ደረጃ እና ቪላሪያል በ7ኛ ደረጃ ሆነው አጠናቅቀዋል ። ቫሌንስያዎች ይህንን ውጤት ለማሻሻል ተስፋ ያደርጋሉ እና የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች ጥሩ ናቸው ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ በ 3 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ፣ ቪላርሪያል ደግሞ በ 11 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። እነዚህ 2 ቡድኖች በ 2021/22 ውስጥ ሲገናኙ ፣ ከፍተኛ ፉክክር እንደምንመለከት ጥርጥር የለውም።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football