Connect with us
Express news


Football

የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ; ኔዘርላንድስ በቀላሉ ሞንቴኔግሮን 4-0 አሸነፈች

World Cup Qualifiers; Netherlands Ease Past Montenegro 4-0
postregister.com

ኔዘርላንዶች ወደ አሸናፊነት በተመለሱበት ጨዋታ ሜምፊስ ዴፓይ ሁለት ግቦች አስቆጥሯል። ማክሰኞ ሁሉም ዓይኖች ወደ አምስተርዳም ይመለሳሉ!

ኔዘርላንድ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሞንቴኔግሮን በማሸነፍ ወሳኝ ድል ስታገኝ ሜምፊስ ዴፓይ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል። የባርሴሎናው አጥቂ በ 38 ደቂቃዎች ውስጥ በዱዛን ላጋተር ሳጥን ውስጥ ጥፋት ከተፈጸመበት በኋላ በፍፁም ቅጣት ምት ግብ አስቆጥሯል። ፍፁም ቅጣቱ አሳማኝ ነበር። ዴፓይ ግብ ጠባቂው ማቲጃ ሳርኪች በማታለል ፣ ኳሱን ወደ መረብ ላይኛው ቀኝ በመምታት አስቆጥሯል።

ከእረፍት በኋላ በ70ኛው ደቂቃ ጀርጊኒዮ ዋንያልደም 3ኛ ግብ ከማስቆስቆጠሩ በፊት ፣ ዴፓይ በ 62ኛ ደቀቃ በጠባብ አንግል የላከዉን ኳስ ሳርኪክን በማሸማቀቅ 2ኛ ግቡ አስቆጥሯል ። ዴፓይ አሁን ካለፉት 9 ጨዋታዎች 9 ግብ በማስቆጠር የአለም አቀፍ ግቡን 30 አድርሷል።

ኔዘርላንዶች በምድብ ጂ ወደ 2ኛ ደረጃ እንዲመጡ ባስቻላቸው ጨዋታ ፣ ኮዲ ጋክፖ ከሳጥን ውጪ ኳሱን በመምታት የምሽቱን ምርጥ ግብ ከመረብ አሳርፏል ። ማክሰኞ በሜዳቸው ከሚጫወቱት ከመሪዎቹ ቱርኮች በአንድ ነጥብ ርቀው በ2ኛ ደረጃ ተቀምጠዋል ። የጋክፖ ለቡድኑ ፒ.ኤስ.ቪ. አይንድሆቨን በሚጫወትበት ሜዳ ላይ ለሀገሩ የመጀመርያ ግብ አስቆጥሯል።

ከሜዳቸው ውጪ ከኖርዌይ ጋር ባደረጉት የመጨረሻ ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ከተለያዩ በኋላ ፣ በኢንድሆቨን ውስጥ ኔዘርላንዶች ጨዋታውን በቀላሉ ለማሸነፍ ጥሩ ብቃት አሳይተዋል። የኔዘርላንድ ጥሩ የኳስ ቅብብል እና ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ በቀላሉ እንዲያሸንፉ አስችሏቸዋል። አሰልጣኝ ሉዊስ ቫን ሃል ለሀገሩ ካደረጋቸው 3 ጨዋታዎች ይህ የመጀመርያ ድሉ ነበር።

ሞንቴኔግሮ አንዳንድ ጥሩ ዕድሎችን አግኝተው ነበር። እነዚህ እድሎች በአብዛኛው የተገኙት በኔዘርላንዶች ደካማ የመከላከል እንቅስቃሴ ናቸው ፣ ነገር ግን ስቴፋን ሙጎሳ እድሎች ሲያባክን ነበር ፣ በተለይም ኔዘርላንዳዊው ተጫዋች ቲሬል ማላሲያ የሰራው ስህተት ወደ ግብ መቀየር አለመቻሉ ትልቅ ስህተት ሰርቷል።

marca.com

ሞንቴኔግሮ አሁን በ 7 ነጥቦች በምድቡ 4 ኛ ደረጃ ላይ ሲሆኑ ፣ ወደ አለም ዋንጫ የሚያሳልፍ ደረጃ ማሳካት ከባድ ይመስላል። ማክሰኞ በአምስተርዳም የሚደረገው ጨዋታ ይህንን ደረጃ ማን እንደሚያሳካ የሚያሳይ ይመስላል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football