Connect with us
Express news


Football

የተከፋፈለ እንግሊዝ ፤ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ውስጥ ከፍተኛ ተፎካካሪ ቡድኖች -ክፍል 1

Divided England: The Biggest Rivalries in The English Premier League (EPL) -Part I
skysports.com

እርስ በርሳቸው በጣም የሚጠላሉት ክለቦች የትኞቹ ናቸው? በሜዳ ላይም ሆነ ከሜዳው ውጭ ትልቅ ብልጭታዎች የሚፈጠሩባቸው የ ኢፒኤል ጨዋታዎች የትኞቹ ናቸው?

 ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል

የሊቨርፑልን ስኬታማነት ለማየት የሚፈልግ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ የለም እንዲሁም የሊቨርፑል ደጋፊ ዩናይትድን ስኬታማ ሲሆን ማየት አይፈልግም። በእነዚህ ክለቦች ከአንዱ ወደ ሌላኛው መዘዋወር እንደ ኃጢአት ይቆጠራል። እ.ኤ.አ. በ 1964 ፊል ቺስናል ጀምሮ በክለቦቹ መካከል በቀጥታ የተዘዋወረ ተጫዋች የለም። በፕሪምየር ሊጉ ዘመን ለሁለቱም ክለቦች የተጫወቱት ማይክል ኦወን እና ፖል ኢንስ ብቻ ናቸው። ለእንደዚህ ዓይነቱ ድፍረት የተሞላበት ስራቸው ፣ ጫማ ከሰቀሉም በኋላ እስከ አሁን ድረስ በእነሱ ላይ ቂም የያዙ አሉ። በሁለቱ መካከል የሚደረጉ ጨዋታዎች በየዓመቱ ከባድ እና አስደሳች ነበሩ። በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ ትልቁ ፉክክርም መባል ይችላል እና በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ፉክክሮች ውስጥ ይካተታል።

በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ቡድኖች 7 የኢፒኤል ነጥቦች ሲኖሯቸው በግብ ልዩነት ማንችስተር ዩናይትድ በ 3 ኛ ደረጃ ሊቨርፑል ደግሞ በ 5 ኛ ላይ ተቀምጧል። እነዚህ ሁለት ተቀናቃኞች በሚቀጥለው ጥቅምት 24 ላይ ይገናኛሉ። ብዙ ግቦችን ፣ ውዝግብን እና ምርጥ እግር ኳስን ይጠብቁ!

አርሰናል ከቶተንሃም ሆትስፐር

bleacherreport.com

ይህ የደርቢ ጨዋታ በእንግሊዝ ውስጥ በጣም ጥንታዊ እና ከባድ ከሆኑ ደርቢዎች አንዱ ነው። በሁለቱ ክለቦች መካከል የመጀመሪያው ጨዋታ የተከናወነው በ 1887 ነበር። ሆኖም ግን ፣ በእነዚህ ሁለት ክለቦች መካከል የነበረው ፉክክር በእውነቱ የተቀጣጠለው ግን አርሴናል በ 1913 በሰሜን ለንደን ወደ ሀይበሪ ከተዛወረ ነበር።

በእነዚህ ሁለት ባላንጣዎች መካከል በአጠቃላይ 199 ጨዋታዎች ተካሂደዋል ፤ አርሰናል 82 አሸንፎ ብልጫውን ይዟል። ይህ እየተጻፈ ባለበት ጊዜ ቶተንሃም በ ኢፒኤል ውስጥ በ 1 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ አርሰናል ደግሞ በመጨረሻው ቦታ ላይ ይገኛል። ስለዚህ ፣ ይህ ወቅት ለ ስፐርስ በታላቅ ተቀናቃኞቻቸው ላይ ሁለት ድሎችን ለማግኘት ጥሩ ዕድል ይመስላል! ቀጣዩ ጨዋታቸው በቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም ጥር 16 ቀን 2022 ነው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football