Connect with us
Express news


Bundesliga

ስለ ቡንደስሊጋው 10 አስገራሚ እውነታዎች!

10 Fun Facts about the Bundesliga!
fcbayern.com

የመጀመሪያው ቡንደስሊጋ መች ነበር ከሚለው ጀምሮ በአንድ ጨዋታ ላይ የተገኘው ከፍተኛው የደጋፊ መጠን ድረስ ስለ ጀርመን ከፍተኛ ሊግ 10 እውነታዎች እነሆ።

የመጀመሪያው ቡንደስሊጋ

የቡንደስሊጋ የመጀመሪያው የውድድር ዘመን በ 1963-64 የነበረ ሲሆን በ ኮልኝ አሸናፊነት ነው የተጠናቀቀው።

በእድሜ ትንሹ ተጫዋች

ቱርካዊው ተጫዋች ኑሪ ሳሂን በቡንደስሊጋው ውስጥ ከታዩ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ነው። እ.ኤ.አ. በ 2005 ለቦርሲያ ዶርትመንድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ሲያደርግ 16 ዓመት ከ 335 ቀናት ነበር።

በእድሜ ትልቁ ተጫዋች

ክላውስ ፊቼቴል በቡንደስሊጋው ከተጫወቱ ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ተጫዋች ሆኗል። በ 1987/88 የውድድር ዘመን ለሻልክ 04 የመጨረሻ ጨዋታውን ሲጫወት 43 ዓመት ከ 184 ቀናት ነበር።

በአጠቃላይ ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ ተጫዋች

edition.cnn.com

ገርድ ሙለር እስካሁን በቡንደስሊጋው 365 ጎሎችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ነው።

በአንድ የውድድር አመት ብዙ ግቦች

በ 2020/21 የፖላንዱ አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በገርድ ሙለር የተያዘውን የቀድሞ ሪከርድ አሻሽሏል። 41 ግቦችን አስቆጥሮ የሙለርን ሪከርድ በአንድ ጎል በልጧል።

በተቀያሪ ተጫዋች የተቆጠሩ ብዙ ግቦች

እ.ኤ.አ. በ 2015 ከዎልፍስበርግ ጋር በተደረገው ጨዋታ ለባየር ሙኒክ ተቀይሮ ሲገባ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ይህንን ድንቅ ውጤት አሳክቷል። በ 9 ደቂቃዎች ውስጥ 5 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል!

ብዙ ጊዜ የተሰለፈው ተጫዋች

በአጠቃላይ 602 ጨዋታዎችን በማድረግ ካርል-ሄንዝ ‘ቻርሊ’ ኮርብል ብዙ የቡንደስሊጋ ጨዋታዎችን ያደረገው ተጫዋች ነው። በ 1972 እና 1991 መካከል ለኤንትራክት ፍራንክፈርት ተጫውቷል።

ብዙ ጊዜ ግብ ሳይቆጠርበት የወጣ ግብ ጠባቂ

fcbayern.com

የቀድሞው የባየር ሙኒክ ግብ ጠባቂ ኦሊቨር ካን ብዙ ጊዜ ግብ ሳይቆጠርበት በመውጣት ሪከርድ አለው። በ 557 ጨዋታዎች ውስጥ 196 ጊዜ ግብ ሳይቆጠርበት ወጥቷል!

በጣም ውዱ ፈራሚ

በአንድ የቡንደስሊጋ ክለብ የተከፈለ ከፍተኛ የዝውውር ክፍያ 80 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን ባየር ሙኒክ ሉካስ ሄርናንዴዝን በ 2019 ከአትሌቲኮ ማድሪድ ለማስፈረም ያወጣው ገንዘብ ነው።

ከፍተኛ የተመልካች ብዛት

እ.ኤ.አ. በ 1969 ሄርታ ቢኤስሲ ኮልኝን ሲገጥሙ 88,075 ሰዎች ወደ በርሊነር ኦሎምፒያስትድዮን አጨናነቁ። ይህ እስከ ዛሬ ድረስ በቡንደስሊጋ ጨዋታ ከፍተኛው የተመልካች ብዛት ነው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Bundesliga