Connect with us
Express news


Football

ተወርቶላቸው ያልተሳካላቸው! በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በጣም ያልተሳካላቸው ተጫዋቾች – ክፍል አንድ

All Hype, No Hope! The Biggest Flops in Football History – Part I
footballtransfers.com

ትልልቅ ስሞች ከአንዱ ክለብ ወደ ሌላ ሲዘዋወሩ ሁልጊዜ የስኬት ታሪክ አይደለም። በአመታት ውስጥ እጅግ አስከፊ የሆኑ ዝውውሮችን እንመለከታለን።

ሁዋን ሴባስቲያን ቬሮን – ከላዚዮ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ – 28 ሚሊዮን ፓውንድ (2001)

ማንቸስተር ዩናይትድ በ2001 ሁዋን ሴባስቲያን ቬሮንን ከላዚዮ ለማስፈረም የእንግሊዝ ሪከርድ ክፍያ ከፍሎ ነበር ፤ በመጀመሪያዎቹ 4 የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች 3 ግቦችን ሲያስቆጥርም የወጣው ብር ማያስቆጭ ይመስል ነበር። ሆኖም የእንግሊዝ እግር ኳስ ፍጥነት ብዙም ሳይቆይ ከፍተኛ ጫና ያሳደረበት ሲሆን የቬሮን አቋም ከጊዜ ወደ ጊዜ መቀነሱን ቀጠለ።

ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ለመገናኛ ብዙኃን ሲናገሩ “[ቬሮን] ታላቅ ተጫዋች ነው ፣ እና ሁላችሁም ደደቦች ናችሁ” ብለዋል። ሆኖም ፈርጉሰን እንኳን በ 2003 ሽንፈትን አምነው ዩናይትድ ለላዚዮ ከ 2 ዓመት በፊት ከከፈለው በግማሽ ቬሮንን ለቼልሲ ሸጠዋል። ለጉዳት ተጋላጭ የነበረው አርጀንቲናዊ በስታምፎርድ ብሪጅም እንዲሁ መጥፎ ነበር ፣ 7 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ብቻ አድርጎ ወደ ጣልያን ተመልሷል ፣ በ ኢንተር ሚላንም በ 49 ጨዋታዎች 3 ግቦችን ብቻ ማስቆጠር ችሏል።

ካካ – ከኤሲ ሚላን ወደ ሪያል ማድሪድ – 68.5 ሚሊዮን ፓውንድ (2009)

thesun.co.uk

ብራዚላዊው ተጫዋች ከትውልዱ ምርጥ ተጫዋቾች አንዱ ነበር ፣ ቄንጠኛ የአጥቂ አማካዩ ችሎታው እና ሃይሉ የተስተካከለ ነበር።ከሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ 10 ዓመታት የበላይነት በፊት የባሎን ዶርን ያሸነፈ የመጨረሻው ተጫዋች ነበር።

ሆኖም እ.ኤ.አ. በ 2009 ሪያል ማድሪድን ሲቀላቀል በዓለም ላይ በጣም ውዱ የእግር ኳስ ተጫዋች ቢሆንም ፣ ቀደም ሲል የነበረው ተጫዋች አለመሆኑ ግልፅ እየሆነ ሄደ። ጉዳቶች በበርናባው የመጀመሪያዎቹን 2 ዓመታት አደናቅፈው ያዙት ከዛም ሜሱት ኦዚል በቡድኑ ውስጥ ቦታውን ወሰደ። ካካ በ 2013 መልሶ ወደ ሚላን ነፃ በሚባል ዝውውር ተሸጠ። እስከ ዛሬ ድረስ ከእግር ኳስ ትልቅ የዝውውር ኪሳራዎች አንዱ ሆኖ ቆይቷል።

ማሪዮ ባሎቴሊ – ከኤሲ ሚላን ወደ ሊቨርፑል – 16 ሚሊዮን ፓውንድ (2014)

ማሪዮ ባሎቴሊ በአንድ ወቅት እንደ አውሮፓ ታላቅ ወጣት ተጫዋች ተቆጥሮ ነበር። ከዛም ወደ ባርሴሎና ያቀናው ሉዊስ ሱዋሬዝን ለመተካት ሊቨርፑል አስፈረመው። በ 2013/14 የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ሱዋሬዝ በ 33 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 31 ጊዜ ጎል ያስቆጠረ እና ብቻውን ቡድኑን የተሸከመ ሰው ነበር።

ባሎቴሊ ግን 1 የፕሪሚየር ሊግ ጎል ብቻ ያስቆጠረ ሲሆን የብሬንዳን ሮጀርስ ቡድንም በጠረጴዛው መካከለኛ ደረጃ ላይ ወደቀ። ባሎቴሊ ከዛ በብድር ወደ ሚላን ከተመለሰ በኋላ በነፃ ተለቀቀ።

አንሄል ዲ ማሪያ – ከሪያል ማድሪድ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ – 60 ሚሊዮን ፓውንድ  (2014)

talksport.com

ማንችስተር ዩናይትድ ከሁዋን ሴባስቲያን ቬሮን ከ 13 ዓመታት በኋላ የአርጀንቲናዊውን አማካይ ለማስፈረም የእንግሊዝን የዝውውር ሪከርድ ሰብሯል ፣ አንሄል ዲ ማሪያ በጥሩ ሁኔታ ከሪያል ማድሪድ ቢመጣም በኦልትራፎርድ የመክሸፍን ልማድ ቀጠለ።

በመስከረም 2014 የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች እና የወሩ ምርጥ ጎል ሽልማቶችን በማሸነፍ በሚያስደንቅ ሁኔታ ተጀምሯል ፣ ግን አቋሙ ብዙም ሳይቆይ ወረደ እና የ 2014/15 የውድድር ዘመን የቴሌግራፍ አስከፊው ዝውውር ተብሎ ተሰየመ። ከዛም በ 15 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ኪሳራ ከ1 የውድድድር አመት በኋላ ብቻ ለቆ ወጣ። ለቀይ ሰይጣኖች በጣም የሚናድደው ደግሞ ፣ አሁን ለፓሪስ ሴንት ጀርሜን እና ለአርጀንቲና ቁልፍ ተጫዋች መሆኑ ነው ፣ በእንግሊዝ ውስጥ ከእዚያ አንድ ዓመት ዝቅተኛ አቋም በስተቀር በጣም ስኬታማ የሆነ የተጫዋችነት ዘመን ነው ያለው።

ኤደን ሃዛርድ – ከቼልሲ ወደ ሪያል ማድሪድ – 146 ሚሊዮን ዩሮ ከተጨማሪዎች ጋር (2019)

ሪያል ማድሪድ ሃርዛድን በበርናባው የክሪስቲያኖ ሮናልዶን ተተኪ አድርጎ አስፈርሟል። እንግዳው ነገር ማድሪድ በቀላሉ አንድ ዓመት ጠብቆ ሃዛርን በነፃ ማግኘት ይችል ነበር። ሆኖም እነሱ በ 2019/20 የውድድር ዘመን ላስቆጠረው አንድ ግብ ከ 100 ሚሊዮን ዩሮ በላይ አከፍለዋል። ከ 2021/22 አመት መጀመሪያ ላይ ለሪያል በአጠቃላይ 5 ግቦች እና ከዚያ የበለጠ ጉዳቶች ነበሩት።

አሁን የ 30 ዓመቱ ተጫዋቹ በሳምንት 400,000 ፓውንድ እንደሚያገኝ ተዘግቧል ፣ በ 2019 ለቅድመ ውድድር ስልጠና 7 ኪሎ ከመጠን በላይ ክብደት ሆኖ የመጣ ሲሆን እና በኋላም በ 2021 ሪያል ማድሪድን ከቻምፒየንስ ሊጉ ሲያስወጡ ከቼልሲ ተጫዋቾች ጋር ሲስቅ ታይቷል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football