Connect with us
Express news


Football

ሊቨርፑሎች በሻምፒዮንስ ሊጉ ከመመራት ተነስተው አሸነፉ!

Liverpool Come from Behind to Win a Champions League Thriller!
skysports.com

ሊቨርሎች ጨዋታውን በበላይነት ተቆጣጥረው ነበር ፣ ነገር ግን ኤሲ ሚላን በአንፊልድ 3-2 ለማሸነፍ የጆርዳን ሄንደርሰን ድንቅ ግብ እስክትቆጠር መጠበቅ ነበራቸው።

የርገን ክሎፕ የሊቨርል ቡድን የሚላንን ጎል ከመጀመርያው ጀምሮ ጫና አሳድሮበታል። በመጀመሪያዎቹ 5 ደቂቃዎች ውስጥ ሁለቱም ዲዮጎ ጆታ እና ዲቮክ ኦሪጊ ለቀዮቹ ጥሩ ዕድሎችን አባክነዋል። ሆኖም ፊኪዮ ቶሞሪ ከትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ የተሻማዉን ኳስ በሚላን ግብ ክልል ውስጥ በመግጨት ማይክ ማይግናን በማለፍ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሯል።

ሊቨርፑል ሞሃመድ ሳላ ፍፁም ቅጣት ምት ማይግናን ባዳነበት ጊዜ መሪነቱን ወደ እጥፍ የማሳደግ እድሉን አምክኗል። ከግብ ጠባቂው አስደናቂ ድርብ ማዳን ነበር። በመጀመሪያ የኳሱን አቅጣጫ በትክክል በመገመት ወደ ቀኝ በኩል በመውደቅ ፍፁም ቅጣት ምቱን አድኗል ፣  ከዚያ ወዲያውኑ በመነሳት የ ጆታ የጭንቅላት ኳስ አድኗል።

ሚላኖች በ 30ኛው ደቂቃ በሰከንዶች ልዩነት ሁለት ግቦች አስቆጥረው የእንግሊዙን ቡድን አፍዝዘዋል። በመጀመሪያ ፣ አንቴ ረቢች በሊቨርፑል የግብ ክልል ውስጥ በግራ በኩል የተቀበለውን ኳስ በእርጋታ ወደ ታች ጥግ በመምታት አስቆጥሯል። የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ አሊሰን ፣ ረቢች ባሻማው ኳስ ሙሉ በሙሉ ከተሸወደ በኋላ ፣ ብራሂም ዲያዝ ግብ አስቆጥሮ ውጤቱን 1-2 አድርሷል።

sempremilan.com

ሊቨርፑሎች በእረፍት ጊዜ እንደገና ተሻሽለው ፣ የስቴፋኖ ፒዮሊን ሚላን ቡድንን በአስቸኳይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር ጀመሩ። ሳላህ ከ 48 ደቂቃዎች በኋላ ከቅርብ ርቀት አቻ በማድረጉ ቅጣት ምቱን በማካካስ ውጤቱ አቻ እንዲሆን አድርጓል። ውጤቱን 2-2 ለማድረስ ኦሪጊ በአስደናቂ ቺፕ ኳሱን አቀብሎታል።

ከዚያ በአስደሳቹ የምድብ ሁለት የመክፈቻ ጨዋታ ጆርዳኖስ ሄንደርሰን ፣ ሚላኖች ሙሉ ለ ሙሉ ያላወጡትን የሊቨርፑል የመአዝን ምት ተጠቅሞ ፣ ከ 7 አመታት በኋላ የመጀመሪያውን የሻምፒዮንስ ሊግ ግቡ በ 69 ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

thetimes.co.uk

በምድብ ሁለት ሊቨርፕሎች አንደኛ ደረጃን ሲይዙ ሚላን በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛው ነው። አትሌቲኮ ማድሪድ እና ፖርቶ በማድሪድ 0-0 ከተለያዩ በኋላ እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ አላቸው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football