Connect with us
Express news


European Leagues

በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ አስቂኝ ሪከርዶች!

Unbelievable Records in Football History!
bleacherreport.com

በእግር ኳስ ዓለም ውስጥ ፤ ከ በአለም ዋንጫ የተቆጠሩ ከፍተኛ ግቦች ፣ እስከ በአንድ አመት ውስጥ የተቆጠሩ ከፍተኛ ግቦች ድረስ ፣  በጣም አስገራሚ ሪከርዶችን እንመለከታለን።

በአንድ የዓለም ዋንጫ ውድድር በአንድ ተጫዋች የተቆጠሩ ከፍተኛ ግቦች (1958)

በ 1958 ጀስ ፎንታይን 13 ግቦችን በማስቆጠር ፈረንሳይን በስዊድን ሶስተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓል። አጥቂው በመክፈቻው ጨዋታ ሀትሪክ የሰራ ሲሆን ፣ ሁለት በዩጎዝላቪያ በተሸነፉበት ጨዋታ እና ከስኮትላንድ ጋር የማሸነፍያ ግብ በማስቆጠር የምድብ ደረጃውን አጠናቋል። ከዚያ በሩብ ፍፃሜው በሰሜን አየርላንድ ላይ ሁለት ግብ አስቆጥሯል እና በግማሽ ፍፃሜው በብራዚል 5-2 ሽንፈት ባስተናገዱበት ጨዋታ እንደገና አስቆጠረ። ከዚያ ለሦስተኛ ደረጃ በሚደረገው ጨዋታ አስደናቂ የሚባል ሪከርድ ለማስመዝገብ አራት ተጨማሪ ግብቦችን አስቆጥሯል። ይህንን በእንዲህ እንዳለ ሚሮስላቭ ክሉሴ ፣  በ 3 የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ውስጥ በአጠቃላይ 14 አስቆጥሮ ፣ በዓለም ዋንጫ ውስጥ የምንም ግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው!

ረጅሙ ያለመሸነፍ ጉዞ (1985-1989

uefa.com

የሮማንያው ቡድን ስቱዋ ቡካሬስት በጊዜው በጣም ትልቅ ቡድን ነበር ፣ ስለሆነም 104 የሊግ ግጥሚያዎችን እና የ 15 ኩባያ ጨዋታዎችን ጨምሮ በማይታመን ሁኔታ 119 ጨዋታዎችን ያለመሸነፍ ጉዞ አድርገዋል። ቡድኑ ከ 1985 እስከ 1989 በአገር ውስጥ እግር ኳስ አንድ ጊዜ ሳይሸነፍ አስደናቂ አምስት ተከታታይ የሊግ ዋንጫዎችን እና አራት የሮማኒያ ዋንጫዎችን አሰባስቧል። በዚህ ያለመሸነፍ ጉዞ በፍፃሜው በፍፁም ቅጣት ምት ባርሴሎናን በማሸነፍ በ 1986 የአውሮፓ ዋንጫን አንስተዋል።

በአንድ ጨዋታ ከፍተኛ የተመዘዙ ካርዶች (2011)

እ.ኤ.አ. በ 2011 በአርጀንቲና ውስጥ የመሃል ዳኛ ዳሚያን ሩቢኖ በክላይፖል እና በቪክቶሪያ አሬናስ መካከል በተደረገው ጨዋታ 36 ቀይ ካርዶችን ሰጥቷል። ጠብ ከተነሳ በኋላ አንድ ደጋፊ እንኳን ወደ ሜዳ በፍጥነት ሮጦ በመግባት አንድ ቡጢ ሰንዝሮ ፣ ከዚያም ተመልሶ ሸሽቷል። በአንድ ጨዋታ ውስጥ 36 ቀይ ካርዶች እንዴት ሊሰጡ እንደሚችሉ እያሰቡ ከሆነ ፣ ሩቢኖ ሁሉንም 22 ተጫዋቾች ፣ እያንዳንዱ ተቀያሪ ተጫዋች እና አንዳንድ የቴክኒክ ሠራተኞችን በ ቀይ ካርድ አሰናብቷል!

በአንድ ዓመት የተቆጠሩ ከፍተኛ ግቦች (2012)

በእርግጥ ይህ ሪከርድ በ 2012 ፣ 91 ግሩም ግቦችን ያስቆጠረው የሊዮኔል ሜሲ ሲሆን የጀርድ ሙለር ሪከርድን ሰብሯል። በዚያው ዓመት የባርሴሎና የምንም ጊዘም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል። በቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ (ሪከርድ) ከባየር ሌቨርኩሰን ጋርም 5 ግቦችን አስቆጥሯል። በዚያ ላይ በብራዚል አስደናቂ ሃትሪክ በመስራት 49ኛ ፣ 50ኛ እና 51ኛ ግቦቹን አስመዝግቧል። የ 25 ዓመቱ ሜሲ በ 2012 በ 69 ጨዋታዎች ለባርሴሎና 79 ግቦችን ለአርጀንቲና ደግሞ 12 ግቦች አስቆጥሯል!

ፈጣኑ ሃትሪክ (2013)

mirror.co.uk

እ.ኤ.አ. በ 2013 የእንግሊዝ አማተር እግር ኳስ ተጫዋች በ 70 ሰከንዶች ውስጥ ሀትሪክ ሰርቷል ፣ ይህም ፈጣኑ ሪከርድ ነው። በዚያን ጊዜ የ 20 ዓመቱ አሌክስ ቶር የመጀመሪያውን በ 11 ደቂቃ ከመረብ አሳርፎ ከዚያ በኋላ በ30 ሰከንዶች ውስጥ አስቆጥሯል። ተጋጣሚያቸው ዊን ጋርደንስ ጨዋታው እንደገና ለማስጀመር በሰራው ስህተት ተጠቅሞ ሶስተኛ ግቡ አስቆትሯል። ወደ ኳስ በመሮጥ ኳሱን ወደ ግብ ጠባቂው በሃይል በመምታት በ12 ደቂቃ ከ 10 ሰከንድ ላይ አስቆጥሯል። በ ሼፊልድ ሃላም ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስን ሲማር የነበረው ቶር ፣ ቡድኑ ራውሰን ስፕሪንግስ በሜዶሃልን እሁድ ሊግ 7-1 ባሸነፉበት ጨዋታ አንድ ተጨማሪ ግብ አክሏል።

ከፍተኛ ተከታታይ ሃትሪክ (2016)

በክሮኤሺያ ከሚገኘው የ ኤን.ኬ ድራሲስ ዳቫኮ ተጫዋች ስትጄፓን ሉቺጃኒክ ይህንን ሪከርድ በ 2016 ይዞታል። በተከታታይ አምስት ሃትሪክ ሰርቷል! አጠቃላይ ድምር በእነዚያ አምስት ጨዋታዎች 20 ግቦችን አስቆጥሯል። እ.ኤ.አ. በ 1998 ናሳሂማ ናካያሙ ፣ በአራት ተከታታይ ሃትሪኮች 16 ግቦችን በማስቆጠር ይዞት የነበረውን ሪከርድ መስበር ችሏል። ናካያሙ እንዲሁ በዚያ ዓመት በዓለም ዋንጫ ለሀገሩ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ጃፓናዊ ተጫዋች ነበር። እ.ኤ.አ. በ 1998 ናካያማ ምርጥ ተጫዋች ነበር ፣ ሉሲጃኒክ ደግሞ በ 2016 የክሮሺያ 7 ኛ የእግር ኳስ ዲቪዝዮን  ተቆጣጥሮ ነበር!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in European Leagues