Connect with us
Express news


Football

ቅድመ እይታ እና ግምት – ማንቸስተር ሲቲ ከ ሳውዝሃምፕተን

Prediction and Preview: Manchester City v Southampton
mancityfc.com

ማንችስተር ሲቲዎች ቅዳሜ ዕለት ሳውዝሃምፕተንን ይገጥማሉ ፣ ሰማያዊዎቹ በኢትሃድ ስታድየም ዘ ሴንትስ በሚያስተናጉድበት ጨዋታ በሁሉም ውድድሮች አምስተኛውን ተከታታይ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ።

እንደ ጋብሬል ጀሱስ እና ጃክ ግሪሊሽ የመሳሰሉት የአሸናፊነት ጉዛቸውን መቀጠል የሚፈልጉ ተጫዋቾች የያዘው ሲቲ ብዙ ግቦችን ማስቆጠር እንደሚችሉ ምንም ጥርጥር የለውም። ረቡዕ ምሽት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከ አርቢ ሌፕዚግ ጋር ሲጫወቱ ስድስት ግብ አስቆጥረዋል ፣ በሊጉ ደግሞ ከኖርዊች እና ከአርሴናል ጋር ባደረጉት ጨዋታ እያንዳንዳቸው ላይ አምስት ግብ አስቆጥረዋል። ባለፈው ሳምንት ሌስተርን 1-0 በማሸነፍ ፣ ባለፉት አራት ጨዋታዎች 17 ግቦች አስመዝግበዋል!

ያ ማለት ሳውዝሃምፕተን አያሰጋም ማለት አይደለም። እነሱም በተደጋጋሚ የማስቆጠር ችሎታ አላቸው ፣ እና በቅርቡ ባለፈው ወር በሊግ ካፕ በኒውፖርት ካውንቲ ላይ ስምንት ግብ አስቆጥረዋል።

sada.com

ሆኖም የፔፕ ጋርዲዮላ ‹ጋላክቲኮስ› በእርግጥ ከሊግ ሁለት ቡድኖች በጣም ይለያሉ እና የሳውዝአምፕተን አሰልጣኝ ራልፍ ሀሰንህትል ከዚህ ሻምፒዮና ቡድን የሚቻለውን ሁሉ ለመውሰድ ይጫወታል። በነሐሴ ወር ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በሜዳው አቻ ተለያይቶ ነበር እናም ይህንን እንደገና መድገም ይፈልጋል።

ሁለቱ ቡድኖች ካደረግዋቸው 35 ጨዋታዎች ፣ ሲቲ 20 ጊዜ ሲያሸንፍ ሳውዝሃምፕተን 7 ጊዜ አሸንፏል። ለመጨረሻ ጊዜ ከሜዳቸው ውጪ ማንቸስተር ሲቲን ያሸነፉት በ 2004 ኬቨን ፊሊፕስ በሜይን ሮድ ላይ ሁለት ጎሎችን ባስቆጠረበት ጊዜ ነበር።

ግምት

ማንችስተር ሲቲ ሳውዝሃምፕተንን እንደሚያሸንፍ ጠብቁ። የዓለማችን ምርጡ ቡድን ለመባል እየተገዳደረ ያለ ቡድን ነው። የሲቲ ሁለተኛ ምርጥ 11 የሁሉም የአውሮፓ አገራት ሊግ ዋንጫ ማንሳት ይችላል ማለት ይቻላል። በጠንካራነት ፣ ቆራጥነት እና በራስ መተማመን የሚታወቁት ሳውዝሃምፕተኖች አሁንም በዚህ የውድድር ዘመን አንድም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አላሸነፉም።

ማንቸስተር ሲቲ 3-0 ሳውዝሃምፕተን

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football