Connect with us
Express news


Football

ሜሲ ወይስ ሮናልዶ?!

Messi or Ronaldo?!
insider.com

በፖርቹጋላዊው ክስተት እና በአስደናቂው አርጀንቲናዊ መካከል ማን የተሻለ ነው የሚለው ጥያቄ ላለፉት አስርት ዓመታት በሁሉም ቦታ የእግር ኳስ አፍቃሪያን አእምሮን ተቆጣጥሯል። ማን ይሻላል? ስታቲስቲክስ ሊነግረን ይችላል?

ለቡድንናቸው ያስቆጠርዋቸው ግቦች

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በአጠቃላይ 783 የቡድን ግቦች አስቆጥሯል እና ሊዮኔል ሜሲ በአጠቃላይ 748 አለው። እያንዳንዳቸው እስካሁን በሙያቸው ከ 740 በላይ የክለብ ግቦችን አስቆጥረዋል ፣ በተለይ በ 2009-10 እና በ 2014-15 መካከል ባሉት 5 የውድድር ዘመናት ፣ እርስ በእርስ ከፍ ወዳለ ከፍታ ሲገፉፉ ፣ እጅግ የላቀ ውጤት አሳይተዋል።

ሮናልዶ በአሁኑ ጊዜ በአጠቃላይ ብዙ ግቦች ሲኖሩት ፣ ሜሲ በ 2011-12 ውስጥ 73 ግቦች በማስቆጠር በአንድ የውድድር ዘመን ባማካይ (ከ 39.5 እስከ 35) ከፍተኛ ሪከርድ በማስመዝገብ አስደናቂ ግብ የማስቆጠር ችሎታ እንዳለው አሳይቷል።

ሮናልዶ በአንድ የውድድር ዘመን ያስቆጠራቸ ከፍተኛ ግቦች 61 ሲሆን ፣ በ 2014-15 ነበር ይህንን ማሳካት የቻለው ፣ በ 2010-11 እና 2015-16 መካከል ለ ተከታታይ 6 ዓመታት 50 እና ከዚያ በላይ ግቦችን አስቆጥሯል።

ለግብ የሚሆኑ ኳሶች

ሊዮኔል ሜሲ ሮናልዶ ካቀበላቸው 227 ለግብ የሚሆኑ ኳሶች ጋር ሲነጻጸር በአጠቃላይ ለክለቡ እና ለሀገሩ 315 ለግብ የሚሆኑ ኳሶች አቀብሏል። ባቀበሏቸው ለግብ የሚሆኑ ኳሶች አስፃር ስንመለከት ፣ ሜሲ እጅግ የላቀ ቁጥር አስመዝግቧል ፣ ይህም ከጊዜያት በኋላ በሜዳ ላይ ያላቸው ኢና መቀየሩ ያሳያል።

ሜሲ በጣም ብዙ የግብ እድሎችን መፍጠሩ እንዲሁም እነዚህን እድሎች ወደ ግብ መቀየሩ ፣ የትኛው ተጫዋች የምንጊዜም ጊዜ ታላቅ እንደሆነ ይወስናል እናም በዚህ ልዩ አካባቢ ያለው ልዩነት ግልፅ ነው።

የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ

cristianoronaldotabs.com

በቻምፒዮንስ ሊጉ 135 ግቦችን በማስቆጠር ሮናልዶ የውድድሩ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ከማንችስተር ዩናይትድ እና በተለይም ከሪያል ማድሪድ ጋር በውድድሩ ደምቆ ታይቷል።

ሆኖም ፣ ሜሲ 120 ግብ በማስቆጠር ብዙም አልራቀም እና በእውነቱ በእያንዳዱ ጨዋታ ያስቆጠርዋቸው ግቦች ስንመለከት በ (በጨዋታው 0.81 ግቦች በማስቆጠር ፣ ከ 0.76 ጋር ሲነፃፀር) የተሻለ ነው ፣ ስለዚህ በአዲሱ ቡድኑ ፒ.ኤስ.ጂ ላይ ጥሩ አቋም ማሳየት ከቻለ የማንችስተር ዩናይትድን ተጨዋች የመብለጥ ጥሩ ዕድል አለው።

አለም አቀፍ ግቦች

ሮናልዶ እና ሜሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ ሪከርድ አሏቸው ፣ ምንም እንኳን ሮናልዶ የተሻለ ቁጥር ያስመዘገበ ቢሆንም ፣ ከሜሲ 2 ዓመታትን ቀድሞ ዓለም አቀፍ ሥራውን ጀመሯል።

ሮናልዶ በዚህ ዓመት በአየርላንድ ላይ 2 ግቦችን በማስቆጠር በ 109 የዓለም አቀፍ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሪከርድ ከ አሊ ዴይል ወስዷል። ሜሲ ለአርጀንቲና 76 ግቦችን በማስቆጠር በዚህ ረገድ ከሮናልዶ በጣም ርቆ ይገኛል።

ዋንጫዎች

ሜሲ እና ሮናልዶ በጣም ተመሳሳይ የዋንጫ ክምችት አሏቸው ፣ ነገር ግን ከሊግ ዋንጫዎች አንፃር ስንመለከት ፣ ሜሲ  ላሊጋውን ከባርሴሎና ጋር 10 ጊዜ በማንሳት ከፍተኛውን ቁጥር ይዟል። ሮናልዶ 7 የሊግ ሻምፒዮናዎች አሉት ፣ ግን ከሜሲ በተቃራኒ በ 3 የተለያዩ ሀገሮች (እንግሊዝ ፣ ስፔን እና ጣሊያን) ሊጎቹን ማሸነፍ ችሏል።

ሮናልዶ በሻምፒዮንስ ሊጉ ከሜሲ በላይ ዋንጫዎችን አንስቷል። 5 ዋንጫዎችን በማንሳት ፣ 4 ካነሳው ሜሲ በልጦ ተቀምጧል።  የማንችስተር ዩናይትዱ ኮከብ እንዲሁ የአውሮፓ ዋንጫ እና የ ዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ በማሸነፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ አስደናቂ ስኬት አግኝቷል።

በሌላ በኩል ሜሲ ከአርጀንቲና ጋር ከፍተኛ ችግር አሳልፏል ፣ 3 የዋንጫ ጨዋታ ሽንፈት አክሎ 4 ያልተሳካላቸው የኮፓ አሜሪካ ውድድሮች አሳልፏል። ነገር ግን እ.ኤ.አ. በ 2021 ኮፓውን አሸንፏል። ሁለቱም የዓለም ዋንጫን ባያሸንፉም ፣ ሜሲ በኦሎምፒኩ የወርቅ ሜዳሊያ አለው።

የግል ሽልማቶች

barcauniversal.com

እ.ኤ.አ. በ 2019 ፣ ለ 6ኛ ጊዜ ባላንዶርን ሲያሸንፍ ሜሲ ከሮናልዶ በቁጥር በልጧል ፣ እናም ወደፊትም መሪነቱ የሚቀጥል ይመስላል። የ 2020 ሽልማት በዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ምክንያት ተሰርዟል ፣ ይህ ማለት ሮናልዶ ይህንን ሽልማት የማሸነፍ ቀጣዩ ዕድሉ በ 37 ዓመቱ በዚህ ዓመት ነው።

ሮናልዶ አዲሱን የፊፋ ‹ምርጥ› ተጫዋች ሽልማቶችን በበለጠ አሸንፏል እና በብዙ አጋጣሚዎች ‹የአመቱ የዩኤፋ ተጫዋች› ሆኖ ቆይቷል ፣ ነገር ግን ሜሲ የበለጠ ‹የሊጉ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች› ሽልማቶችን አሸንፏል። በእርግጥ ሮናልዶ በእንግሊዝ ፣ በስፔን እና በጣሊያን ‘የዓመቱ ተጫዋች’ ሽልማትን አሸንፏል!

ሜሲ የአውሮፓ ጎልደን ጫማ 6 ጊዜ አሸንፏል ፣ ይህም ከሮናልዶ በ 2 ይበልጣል እና በአጠቃላይ ከተፎካካሪው በጥቂት ይቀድማል ፣ ነገር ግን ሁለቱም በ ፊፋፕፕሮ ምርጥ አሰላለፍ (FIFPro World XI) 14 ጊዜ መካተታቸው ፣ በመካከላቸው ያለውን ፉክክር በጣም ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል።

ስለዚህ ያልተለመዱ አስደናቂ የውድድር ዘመናት ካሳለፉ በኋላ ማን የተሻለ ነው ብለው ያስባሉ? ሜሲ ወይስ ሮናልዶ?

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football